Site icon ETHIO12.COM

በኦሮሚያ ክልል 75 ሺህ 583 መምህራን ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ይወስዳሉ

ግንቦት 30/2013 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል የመምህራን ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጥ የኦሮሚያ ትምህት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ለነባር መምህራን እና የትምርት ቤቶች ሀላፊዎች የሚሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቆ ለከተሞች እና ዞኖች መፈተኛ ጣቢያዎች መሰራጨታቸውን ቢሮው ገልፀዋል፡፡

47 ሺህ 785 በዲፕሎማ እና 26 ሺህ 785 በድግሪ ማዕረግ የተመረቁ መምህራን እንዲሁም 1ሺህ 73 አንደኛ ደረጃ እና 388 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮች የብቃት ማረጋገጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፈተናው በ193 የፈተና ጣቢያዎች የሚሰጥ ሲሆን በአጠቃላይ 75 ሺህ 583 ባለሙያዎች ፈተናውን ይወስዳሉ፡፡ via OBN

Exit mobile version