በ2012 ከነበሩት 46 ሺህ በላይ መምህራን አሁን ላይ ከ14ሺህ በላይ የሚሆኑት ከስራ ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የትምህርት ቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ በጦርነት ሳቢያ መምህራን ሞተዋል። ራሳቸውን ለማኖር ተሰደዋል። የኑሮ መመሳቀል ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በጦርነቱ ምክንያት የተሰደዱ ፣ የተፈናቀሉ ፣ አካላቸው የጎደለ እንዲሁም የሞቱ መምህራን መኖራቸውን አንስተው፤ ከ 2 ዓመት በላይ ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ህይወታቸውን ለማትረፍ የተለያዩ ስራዎች ውስጥ የተሰማሩ መኖራቸውንም ሃላፊውን ጠቅሶ የዘገበው ኢትዮኤፍ ኤም ነው።ሃላፊው የተቀሩት መምህራንም ቢሆኑ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ የስነልቦና ጉዳትን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ችግር እንደደረሰባቸው አመልክተዋል።
በክልሉ የነበረው ጦርነት በትምህርት ዙሪያ ሶስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷልም ነው ያሉት ሃላፊው። የት/ቤቶች መቃጠል ፣መፍረስ፣ መውደም አንደኛው ሲሆን ፤ በሰው ሃይሉ ላይ ያደረሰው ጉዳት ቀጥሎ የሚነሳ ጉዳይ ነው።
በሶስተኛነት የተነሳው ጉዳይ ደግሞ ስርዓተ ትምህርቱ ሲሆን ብዙ ተማሪዎች በእድሜያቸው ልክ ማግኘት ያለባቸውን ትምህርት ባለማግኘታቸው አሁን ላይ 5ኛ ክፍል እና ከዛ በላይ መሆን የነበረባቸው ልጆች ገና የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በ2012 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቢወስዱ ምናልባት አሁን ላይ የ4ኛ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሚሆኑ ከ9ሺህ በላይ ተማሪዎች ከ4 አመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰዳቸው የሚታወስ ነው።
በሌላ ዜና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ቁመና እንደሌለ ተገልጿል። ክልሉ በከፍተኛ ሁኔታ በተጎዳበትና ዜጎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዉ በርካታ ቦታዎች በወራሪ ሀይሎች በተያዙበት ሁኔታ፣ ምርጫ ማካሄድ የማይታሰብ ነው ሲሉ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል። ዜናው “ወራሪ” ያላቸውን አላብራራም።
ክልሉን እየመራ የሚገኘዉ ግዚያዊ አስተዳደር ምርጫ ለማካሄድ ዝግጁነት የለዉም የሚሉት የዉድብ ናፅነት ትግራይ ዉናት ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገቦ፣ አስተዳደሩ ወደ ምርጫ ገብቶ ለዉጥ እንዲመጣ ፍላጎትም ዝግጁነትም የለዉም ብለዋል።
በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ጥሩ ቅርርብ መኖሩን የሚናገሩት የዓረና ሉአላዊነትና ዲሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ አንዶም ገ/ስላሴ ፣ በሳልሳይ ወያኔ ትግራይ፣ውድብ ናፅነት ትግራይ እና ባይቶና አባይ ትግራይ ጥምረት ፈጥረዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፣ አረናም ጥሩ መቀራረብ ስላለዉ ምን አልባት መልካም ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫ ከተካሄደ በጋራ ለመወዳደር ዉይይት ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ዓመት በ2016 ምርጫ ከሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች አንደኛዉ የትግራይ ክልል መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም። የትግራይ ክልልን ጨምሮ የስድስተኛው ዙር ቀሪ ምርጫዎችን በተለያዩ ጊዜያት ለማከናወን ዝርዝር ዕቅድና በጀት አዘጋጅቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳቀረበም አስታውቋል፡፡
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል።… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”