Site icon ETHIO12.COM

ኢዜማ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹና የጋራ ከተማ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታወቀ


የዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነችና የጋራ ከተማ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታወቀ።

‹‹የጋራ ህልም የጋራ ከተማ›› በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ላይ ትናንት ከነዋሪዎቿ ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለችበት ወቅት የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆንና የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን እድል የሚሠጥና ዴሞክራሲ የሚጠናከርበት ነው ።

ኢዜማ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የከተማው ባለቤት መሆን አለበት የሚል ጠንካራ አቋም አለው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሀኑ፣ በከተማዋ የሚስተዋሉ በርካታ ችግሮችንና የመሬት ወረራን ማስቆም የሚቻለው የከተማው ህዝብ በመረጠው እንዲተዳደር ማድረግ ሲቻል ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ፓርቲው አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች የሁሉም የጋራ ከተማ ለማድረግ ይሰራል ያሉት ፕሮፌሰር ብርሀኑ፤ በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ሲደርስ ቆይቷል። በከፍተኛ ደረጃ የመሬት ወረራ በማካሄድ ነዋሪዎቿን ከከተማ ውጭ የማስፈር ሥራ ሲሰራ እንደቆየ አመልክተዋል።

Via – EPD

Exit mobile version