ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ የምታደርገው ተሳትፎ የሚደነቅና ሊቀጥል የሚገባው ተግባር መሆኑን የተለያዩ ሃገሮች ወታደራዊ አታሼዎች ገለጹ።
መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የተለያዩ ሃገሮች ወታደራዊ አታሼዎች ማህበር አባላት ዛሬ የመከላከያ የሠላም ማስከበር ሥልጠና ማዕከልን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የሦስት አገሮች ወታደራዊ አታሼዎች እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሠላም ለማስፈን እያደረገች ያለው ተሳትፎ የሚደነቅ ነው።
“ኢትዮጵያ እ.አ.አ ከ1950ዎቹ ከኮሪያ የሠላም ማስከበር ተሳትፎ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለዓለም የጋራ ሠላም የበኩሏን አስተዋጽኦ አድርጋለች” ያሉ ሲሆን፥ የተመድ የሠላም ማስከበር ተልዕኮ የሚያበረታታውን የሴቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያ በተግባር ማሳየቷንም ገልጸዋል።
ይህንንም ኢትዮጵያ ከሌሎች ተሳታፊ አገሮች ጋር በትብብር መንፈስ ማከናወኗን የገለጹት ወታደራዊ አታሼዎቹ፥ ተሳትፎዋን አጠናክራ ልትቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የዛምቢያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ብርጋዴር ጄኔራል ሙሶንዳ ሴንጋ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ለዓለም ሠላም ብዙ መስዋዕትነት የከፈለች አገር ናት።
“በርካታ ሠራዊቷን ለዓለም እንዲሁም ለአፍሪካ ሠላም ስትል ገብራለች” ያሉት ጄኔራሉ፥ ለሠላም በተደረገ ተጋድሎ ኢትዮጵያ ሴት የሠራዊት አባላትን ጭምር አሰልፋለች ብለዋል።
ይህም የተመድ በሠላም ማስከበር ተልዕኮ የሴቶች ተሳትፎ 30በመቶ ይሁን ከሚለው የመርህ ውሳኔ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ነው ያረጋገጡት።
በኢትዮጵያ የኮንጎ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ሊዊስ ሮላንድ በበኩላቸው፥ “የኢትዮጵያ የሠላም ማስከበር ተሳትፎ የረጅም ዓመት ልምድ ያለው ነው” ብለዋል።
በሠላም ማስከበር ተሳትፎዋ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ አገር መሆኗን የሚበረታታ እንደሆነም ጠቁመዋል።
የመከላከያ የሠላም ማስከበር ሥልጠና ማዕከል ኢትዮጵያ በሠላም ማስከበር እያደረገች ያለው ተሳትፎ ለማሻሻል የሚያደርገውን የአቅም ግንባታ ሥራ አድንቀዋል።
በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ግሩፕ ካፒቴን አንድሪው ጊልበርትም በተመሳሳይ፥ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ያላትን ተሳትፎ አድንቀው፥ የሃገራቸው ሠራዊት በተመድ የአፍሪካ ሠላም ማስከበር ተልዕኮ ሥር ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጋር አብሮ መሥራቱን ጠቁመዋል።
ይህ አጋርነቱ እንደሚቀጥልና በሰላም ማስከበር ተልዕኮ አቅም ግንባታ ሥልጠና ረገድ በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ውስጥ ተመድ ባለው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ኢትዮጵያ በአራት ሥፍራዎች ተሳታፊ መሆኗን የዘገበው ኢዜአ ነው።
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?