Site icon ETHIO12.COM

“ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ፤ የጃፓኑ ሱምቶም ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት አደርጋለሁ አለ

በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ ያሸነፈው “ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ።በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ያገኘው ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ኩባንያ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

የስምምነት ፊርማው የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኬኒያው ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት ነው።የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳሪ ኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ኢድግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።ኩባንያው ጫረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ከሚዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ ይታወቃል።

በዛሬው እለት ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ፈቃድ ያገኘበት መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።ግሎባል ፓርትነር ፎር ኢትዮጵያ የኬኒያው ሳፋሪ ኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎንና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካውን ቮዳኮም የጃፓኑን ሲሚቶምና ዲኤፍሲን በጥምረት የያዘ ኩባንያ ነው።ኩባንያው በቀጣይ አስር ዓመታት ከ8 ቢሊዮን
ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።በዚህም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ ዜና የጃፓኑ ሱምቶም ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ በቴሌኮም ዘርፍ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ገለጸ በቴሌኮም ዘርፍ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መንግስት በወሰደው ውሳኔ መሠረት ጨረታውን ያሸነፈው ‘የግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ ‘ ድርጅት አንዱ የሆነው የጃፓኑ ሱምቶም፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ከሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ቶሽካዙ ናምቡ የኢንቨስትመንት ዕቅዳቸውን ያስታወቁት፤ በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ረ አምባሳደር ካሣ ተክለብርሃን ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። ምክትል ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽናቸው ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የኢትዮጵያ መንግስት በግልጸኝነት ባካሄደው የጨረታ ሂደት በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡አምባሳደር ካሣ ተክለብረሃን በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ በጃፓን፣በኤሽያ እና በአፍሪካ ያለው የካበተ ልምድ በኢትዮጵያ ኢንቬስት በማድረግ እንዲደግመው ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።


Exit mobile version