ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አደም ፋራህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን መልዕክት ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ሚሼል እና ለአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዩርሱላ ቮን ደር ላየን አድርሰዋል፡፡
አፈጉባኤው ከአውሮፓ ህብረት አመራሮች ጋር ኢትዮጵያ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ እና ፍትሓዊ ምርጫ ለማድረግ እያደረገች ያለው ጥረት፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በትግራይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ ድጋፎችና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በዚህ ወቅትም የአውሮፓ ህብረት የስራ ሃላፊዎች በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ በአግባቡ እንዲደርሳቸው የሚደረገው ጥረት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
የስራ ሃላፊዎች በትግራይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ጋር በጋራ የጀመረው የምርመራ ሂደት የሚበረታታ ነው ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩቴ የተላከ ደብዳቤን አደረሱ፡፡
ደብዳቤውን ለሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ አስረክበዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ከሚኒስትሯ ጋር በተለያዩ ጉደዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር እና በኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡ via . FBC
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው።… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው