Site icon ETHIO12.COM

በመለስ ዕቅድ መቃብር ላይ – ኮንፌዴሪሽን፣ አሰብና የባህር ሃይል ግንባታ – የኢሳያስና አብይ የጥምር ክንድ

Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed (C), Eritrea's President Isaias Afwerki (2ndL) and Somalia's President Mohamed Abdullahi Mohamed (R) cut the ribbon during the inauguration of the Tibebe Ghion Specialized Hospital in Bahir Dar, northern Ethiopia, on November 10, 2018. - Presidents of Somalia and Eritrea met Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed on November 9, 2018 to cement regional economic ties as relations warm between the once-rival nations. (Photo by EDUARDO SOTERAS / AFP) (Photo credit should read EDUARDO SOTERAS/AFP via Getty Images)

“አሰብን ከኢትዮጵያ ይልቅ ከኤርትራ ላይ መንጠቅ ይቀላል” በሚለው የመለስ ስሌት አሰብ ለኤርትራም ሆነ ለኢትዮጵያ በሚገባው ደረጃ ሳይጠቅም ኖረ። መለስ ” የግመል መፈንጫ ይሆናል” እንዳሉት ሳይሆን እንዲሆን አድርገውት አለፉ። ዛሬ እሳቸው ዕቅድ መቃብር ላይ አዲስ ችቦ መለኮሱ ሲሰማ የቀጣናው ፖለቲካ ከሙት እሳቤ ተላቀቀ። ዓለም በሙሉ ትክረቷ ወደ ቀይ ባህር ሆነ።

የኢትዮ 12 ዝግጅት ክፍል ተባባሪዎች ከአሜሪካና ከአዲስ አበባ ባሰባሰቡት መረጃ በኢትዮጵያና ኤርትራ አየር ስር ታላቅ ተስፋ ሊጎመራ ዳር ላይ ነው። ሆኖም ግን ይህን የተረዱ ብርሃኑ ሳይበራ መቃብር ሊያሳዩ እየታተሩ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይና የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የመጀመሪያ ግንኙነት ዓለምን ካስደመመ በሁዋላና ይኸው አድናቆት ዓለምን አዳርሱ የሰላም ኖቤል ሽልማት ደጅ ከደረሰ በሁዋላ አፍታም ሳይቆይ ኢትዮጵያ ላይ እንደ አገር፣ ኢሳያስ ላይ በግል ያነጣጠሩት ዘመቻዎች ዋና ዒላማቸው ከሁለቱ መሪዎች ግንኙነት በሁውላ የተሰሙት ዜናዎች ናቸው። እነሱም የባህር ሃይል ግንባታ፣ የአሰብ ወደብ ጉዳይና የኮንፌዴሬሽን ጥምረት።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር እሽቅድምድም ውስጥ የከተተው መለስ ድሮ ያቀዱት እቅድ ነበር። ዕቅዱ በኤርትራና በኢትዮጵያ መቃብር ላይ አሰብን ወስዶ
ታላቋን ትግራይ” እውን ማድረግ። በዚህ ዓላማ ስሌት የኤርትራ ደጋማ አካባቢዎችን አካሎ ” ተጋሩ” በሚል መለያ አገር ለመምስረት ያካበተውን ሲረጭ የከረመው ትህነግ፣ ኮንፌዴሬሽኑን ቀድሞ ማጨናገፍ ዋና እቅዱ እንደነበር የአሜሪካ ተባባሪያችን ከታማኝ የትህንግ ሰዎች የቁጭት ወሬ መስማታቸውን ያረጋግጣሉ።

ትህነግ ከማዕከላዊ መንግስት በራሱ ውሳኔ አፈንግጦ ወደ ትግራይ ሲያመራ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ ያተኮረ የማጠልሸት ዘመቻውን ያፋፋመው እሳቸውን ከሕዝብ ነጥሎ ይህን ዓላማ ለማኮላሸት መሆኑንን ጉዳዩን የሚከታተሉ ይናገራሉ።

በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ አንድ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለነጃዋር ” ሃሳባችን ትልቅ ነው። ትህነጎች በመጠኑም ቢሆን ያውቁታል። እናንተ ግን አልተረዳችሁም። እባካችሁን ለነሱ አጀንዳ መጠቀሚያ አትሁኑ። የእኛ ችግር ይፈታል። ይህ የጀመርነው ጉዳይ ግን እንደ አገር ታላቅ ነው” ሲሉ እንደተማጸኗቸው አንጋፋው የኦሮሞ ፖለቲከኛ ስማቸውን እንዳንተቅስ ገልጸው ነግረውናል።

በኢትዮጵያና ኤርትራ ፍርስራሽ ላይ አገር ሊገነባ እላይ ታች ሲል የነበረው ትህነግ በንፋስ ፍጥነት ከመንግስትነት ወደ ክልል፣ ከክልል፣ ወደ ጫካ፣ ከጫካ ደግሞ ወደ ስርቻ ሲሸጋገር፣ ዋና ዋና ሴራ ጠንሳሾቹ፣ እንዲያጣ ሆኗል። ከጦርነቱ በሁዋላ የሚዲያውን ዘመቻና ችግሩን አግዝፎና አንድ ወገንን ተጠያቂ በማድረግ፣ ከችግሩ መነሻ ምክንያት በመሸሽና አዲስ ትርክት በመፍጠር በትግራይ የተፈጠረውን ቀውስ እግረመንገዳቸውን የሚጠቀሙበት ሃይሎች የገፉት በዋናነት ሁለቱ አገሮች ሊፈጥሩ የሚችሉትን ጡንቻ ከወዲሁ ለማሟሸሽ እንደሆነ ስምምነት አለ።

በትግራይ የተፈጠረው ቀውስ አሳሳቢ መሆኑንን የሚስማሙት ወገኖች፣ ችግሩን ለመፍታት የሚደረገው ርብርብ እንዳለ ሆኖ ኢትዮጵያና ኤርትራ የጀመሩትን ክንድን የማተንከርና የቀይባህር ሃያል የመሆኑ ጉዟቸውን እንደማያቋርጡ አውቀናል። አንዳንድ አገሮችም ይህንን እየተረዱና አቋማቸውን የማለሳለስ አካሄድ ሲከተሉ፣ ሆን ብለው የቤት ስራ ወስደው ከሚበጠብጡት ውጪ ትዮጵያዊያን ጉዳዩን በወጉ ያጤኑት እንደማይመስል አስተያየት ይሰማል።

ለታዋቂው ዲፕሎማት ዴቪድ ሺን ቅርብ የሆኑ ተባባሪያችን ከቀን በፊት ከእሳቸው ጋር ቆይታ ካደረጉ በሁዋላ አንድ የተረዱትን ቁም ነገር አጋርተውናል። ሺን “ኢትዮጵያዊያን አሜሪካ ምን እንደምትቃወምና ምን እያደረገች እንደሆነ በቅጡ አልተረዱም” ብለው እንደነገሯቸው በማስታወስ ነገሮችን በሰከነ ዲፕሎማሲ ማስኬድ እንደሚገባ ያመለክታሉ።

ቀኑን በውል መቁረጥ ባይቻልም ኢትዮጵያ የባህር ሃይሏ የሚታጠቃቸው ሰርጓጅ መርከቦች ወደ ቀይ ባህር የሚገቡበት ቀን መቃረቡን ምንጮች አመክተዋል። የአሰብ ወደብ የንግድ ንግግርም ወደ መገባደዱ ተቃርቧል። አንዳንድ የጸጥታ ጉዳዮችን የሚተብቅ ጉዳይ ነው። ከሆሉም በላይ የኮንፌዴሬሽን ጥምረቱ ጉዳይ እየተጣደፈ ነው። በትህነግ ሴራ የተለያዩት የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ዳግም ወደ ነበረበትና መከባበር ላይ የተመሰረት ጥምረት ከመዛወሩ በፊት ሩጫው ሁለቱን መሪዎች ማሰናከል ነው።

ብልጽግና ከኈለት ሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ” ወደ ቀይ ባህር ፖለቲካ መመለሳችን ነው” ሲል ይህ ሁሉ ችግር ኢትዮጵያ ላይ የተደፋበትን ምክንያት ማስታወቁ አይዘነጋም። ዘግይተው የፈረንጆች አዲስ ዓመት ንግግር ያሰሙት ኢሳያስ አፉወርቂም ኢትዮጵያን አንስተው በቀይ ባህር ፖለቲካ ልትገለል የማትችል አገር እንደሆነች ያስረዱት ፖለቲካውን ከስሩ በመበለት ነበር።

ይህ የቀይ ባህር ሃያልነት ጉዳይ እስከ ሶማሌ ድረስ መዘርጋት ስላለበት ፕሬዚዳንት ፎርማጆን አካቶ የተገነባ ስለሆነ እሳቸውንም ከሶማሌ ላይ ለመንቀል ሩጫው የፈጥነበት ምክንያት ሌላ እንዳልሆነ አስተያየታቸውን የሰጡን ባለሙያ አመልክተዋል። ኤርትራ ብቻዋን ወይም ሶማሊያ ብቻዋን በባህር በራቸው ላይ ተደራዳሪ ሆነው ይህ ነው የሚባል ሕዝብቻውን የጠቀመ ውጤት አላመጡም። አሁን ግን ሶስቱ ከላይ ቀይ ባህር ጀምሮ እስከ ታች የሶማሌ ጭፍ ድረስ ሃይላቸውን ከገነቡ የመደራደር፣ ከፍተኛ ጥቅም የማግኘት፣ ተቀራራቢ አገልግሎቶችን በተመሳሳይ የማግነትና እነ ግብጽ ያላቸውን አይነት የፖለቲካ የበላይነት መገንባት ይቻላል። “ፖለቲከኖቻችን ይህን ሊረዱና ትልቁን ምስል ሊመለከቱ ይገባል” ሲሉ ሃሳባቸውን ያጋሩን እንዳሉት ለኤርትራና ኢትዮጵያ ሕዝብ ብርሃን ሊፈነጭ በጫፍ ነው።


Exit mobile version