Site icon ETHIO12.COM

የርቲዎች የጋራ ም.ቤት ምርጫ ቦርድ ውጤት ሳይገልጽ ፓርቲዎች መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ አሳሰበ፤ ቆጠራ ተጀመረ

ፓርቲዎች የድምፅ መስጠት ሂደት እና ቆጠራ ተጠናቆ በቦርዱ ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት አሳሰበ።የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፌ ፓርቲዎች የድምፅ መስጠት ሂደት እና ቆጠራ ተጠናቆ፣ በቦርዱ ውጤት እስከሚገለፅ መግለጫ ከመስጠት እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።በተጨማሪም ቦርዱ ከፓርቲዎች እየቀረቡ ላሉ ቅሬታዎች ተገቢና ወቅታዊ እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ሂደቱን ማጠናከር አለበት ብለዋል።

ምክር ቤቱ መንግስት የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጡን ስራ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቆ ህዝቡም ለሰላሙ ቅድሚያ በመስጠት በአንድነት እንዲቆም ጥሪ ማቅረቡን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ የምርጫ ዜና ምርጫ ቦርድ መግለጫ አውጥቷል።

መራጭ ዜጎች፣ ለምርጫ አስፈፃሚዎች ፣ ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ እንደሚታወቀው የ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ እየተከናወነ ይገኛል።

1, የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዘግይቶ የተጀመረባቸው ቦታዎች በመኖራቸው

2, የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቁሳቁስ ስርጭት የዘገየባቸው ቦታዎች በመኖራቸው

3, ድምፅ ለመስጠት ረጅም ሰልፉች ላይ ያሉ ዜጎች በመኖራቸው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እስከ ምሽቱ ሶስት ሰአት ድረስ መራዘሙን ቦርዱ ያሳውቃል። በዚህም መሰረት የምርጫ አስፈፃሚዎች እስከ 3 ሰአት ድረስ የሚመጣ ማንኛውንም መራጭ እንዲያስተናግዱ ጥሪ እናስተላልፋለን። ነገር ግን የመራጮች መዝገባቸው ላይ ያሉ ዜጎች መርጠው ያጠናቀቁባቸው እና ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋት እና የቆጠራ ስራ መጀመር ይችላሉ። በድምፅ አሰጣት ሂደት ወቅት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች 778 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድሰኔ 14 ቀን 2013 አ.ም

Exit mobile version