Site icon ETHIO12.COM

የምርጫውን ሂደት ለማወክ የሞከሩ 123 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ! ፀረ ሰላም ሃይሎች ተመደምስሰዋል

የምርጫውን ሂደት ለማወክ የሞከሩ 123 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ 42ቱ ላይ ቀላል ቅጣት ተላልፎባቸዋል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል ምርጫውን በማስመስከልት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። የምርጫውን ሂደት ለማደናቀፍ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሙከራ መደረጉን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ ይሁን እንጅ ሙከራው በፀጥታ ሃይሉ መክሸፉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች በተፈጠረ ሁከት ፀረ ሰላም ሃይሎችን መደምሰስ መቻሉንም ነው የተናገሩት፡፡

በህግ ማስከበር ሂደቱ የፀጥታ አስከባሪ አካል ህይወት ማለፉንም አንስተዋል፡፡

በአጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ለማወክ የሞከሩ 123 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ 42ቱ ላይ ቀላል ቅጣት ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት የህዝቡ ትብብር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድር ብቻ ተዘጋጅቶ መውጣት፣ በቴክኖሎጅ የታገዘና የተጠናከረ የፀጥታ ስራ መሰራቱ አስተዋጽኦ አበርክቷልም ነው ያሉት፡፡

ኮሚሽኑም በድህረ ምርጫ ሊከሰት የሚችል የፀጥታ ችግርን ለከመከላከል ሙሉ ዝግጅት አድርጌያለሁ ብሏል፡፡

የፀጥታ ስራው የፌደራል ፖሊስ፣ የደህነት ተቋማትናና የክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version