ETHIO12.COM

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሶስት ባልደረቦቹ ትግራይ ክልል ውስጥ መገደላቸውን ሪፖርት አደረገ

ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) ሶስት ባልደረቦቹ ትግራይ ክልል ውስጥ መገደላቸው ሪፖርት አደረገ።

#Ethiopia : MSF የባልደረቦቹን ሞት ማረጋገጫ ከሰማ በኃላ ሃዘን ላይ መሆኑ ገልጿል።

የደንገተኛ ጊዜ አስተባባሪ ማሪያ ኸርናዴዝ ፤ ረዳት አስተባባሪ ዮሀንስ ሃለፎም ረዳ፣ ሹፌር ቴድሮስ ገብረማርያም ገ/ሚካኤል ትላንት ከሰዓት ጉዞ እያደረጉ እያለ ግንኙነታቸው ተቋርጦ ነበር።

ዛሬ ጥዋት ባዶ መኪናቸው ተገኝቷል፤ ከመኪናው በትንሽ ሜትር ርቀት ደግሞ ህይወታቸው አልፎ አስክሬናቸው ተገኝቷል።

MSF ጥቃቱን ያወገዘ ሲሆን ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመ ግን በሪፖርቱ ላይ ያለው ነገር የለም።

ማሪያ ፣ ዮሃንስ እና ቴድሮስ ትግራይ ክልል ውስጥ ለሰዎች ድጋፍ በመስጠት ላይ ነበሩ፤ ለዚህ ስራ ክፍያቸው ይህ (ነፍሳቸው መንጠቅ) መሆኑ ሊታሰብ የማይችል ነው ብሏል MSF።

ስለሰራተኞቹ ፦

• ማሪያ ኸርናዴዝ – ከማድሪድ (ስፔን ሀገር) የመጣች የ35 ዓመት ሴት ስትሆን ከMSF ጋር በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ በየመን ፣ ሜክሲኮ፣ በናይጄሪያ ሰርታለች።

• ዮሃንስ ሃለፎም ረዳ – ዕድሜው 31 ሲሆን ከኢትዮጵያ ነው ፤ ድርጅቱን የተቀላቀለው የካቲት ወር ላይ ነበር።

• ቴድሮስ ገብረማርያም ገብረሚካኤል – ዕድሜው 31 ሲሆን ከኢትዮጵያ ነው ፤ ከግንቦት ወር ጀምሮ የድርጅቱ ሹፌር ነበር።.

Exit mobile version