Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ መቀለን ለቋል፤”አማራ ከክልሌ ይውጣ” ዘመቻ ተጀምሯል

የፌስ ቡክና የዩቲብ ገበያ ያበደባት፣ የሚሰማውን መምረጥ ያማይችል መንጋ ወደ ነዱት የሚነዳባት፣ ድልና የበላይነትን በወጉ መያዝ የማይችሉ አመራሮች በሞሉባት፣ ማንም እየተነሳ ተንታኝ ሆኖ በሚፈነጭባት፣ ዓለመውና አቅደው የሚራመዱ ዜጎች በጠፉባት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ የተሸነፈው ትህነግ ” የአማራ ጦር ከክልሌ ይውጣ” የሚል ቅደም ሁኔታ በማስቀመጥ ይደራደር ሲሉ ደጋፊዎቹ ዘመቻ ጀምረዋል። መንግስት ያለው ይህ የክረምት ወር እስኪያልቅ ድረስ የተናተል የተኩስ አቁም ብቻ ነው። በሌላ በኩል ” ችጋር አሸነፈ” ሲሉ አስተያተ የሚሰጡም አሉ።

የትህነግ ቋሚ ደጋፊዎች እንዳሉት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበውን የተኩስ ማቆም ጥሪ ተከትሎ ትህነግ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ አለበት። ይህን ያሉት ወገኖች እንዳሉት የትህነግ ሰራዊት ወደ መቀለ እየገባና ቀድሞ ሲቪል መስሎ ከተማ የገባው ሃይል በቅንጅት እየሰሩ ነው። የመከላከያ ሰራዊት መቀለን ለቆ ወደ አፋር ክልል እየተጠጋ ይገኛል። በከተማዋ አልፎ አልፎ ዝርፊያ የሚስተዋል ሲሆን መከላከያ ለቆ ሲወጣ የሚተናኮሉ ሃይሎች ካጋጠሙት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ መታዘዙ ተሰምቷል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ የአማራ ክልል በሙሉ ሃይሉ በተጠንቀቅ ቁሟል። በመረጃና በሎጅስቲክ በመናበብ ቀድሞ በተሰራ ስራ በውልቃይት ህዝብ ተደራጅቶ ታጥቋል። ልክ በትግራይ ልዩን ሃይል ሲቪል ለብሶ ከመኖሪያ ቤት እንደሚዋጋው፣ በወልቃይት ህዝቡ ትህነግ ሊወር ካሰበ ከቤቱ ሆኖ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ይገመታል። ከዚህም በላይ እስከ ሱዳን ድንበር በተዘረጋው ግንባር መከላከያና የአማራ ልዩ ሃይል፣ እንዲሁም ኤርትራ ድንበሯ ላይ ጥብቅ ጥበቃ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

የዓለም አገራት በተለይም አሜሪካ የመራችውን ጫና ከድህነት ጋር መሸከሙ ከወኔና ከሽለላ በላይ በመሆኑ ኢትዮጵያ በሚስጢር ጫናውን እንደተቀበለች የሚያሳይ ውሳኔ መሆኑ ተመልክቷል።

በስተመጨረሻ በደረሰን ዜና መከላከያ ሰራዊት መቀለን ለቆ እንዲወጣ የተደረገው ዛሬ ንጋቱ ላይ ሲሆን ለቆ ሲወጣ አስገዳጅ ነገር አጋጥሞት አልነበረም። የፌደራል ፖሊስ አባላትም ለቀዋል። ከባድ መሳሪያዎችና አስፈላጊ የጦርነት ቁሶች ተጓጉዘዋል። ባንክችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለጊዜው አይሰሩም። መንግስት ለውጊያ የሚውሉ ቁሶችን አጽድቶ ማውጣቱ ተመልክቷል።

የትህነግ ደጋፊዎችን ቀጣይ ዘመቻ የሰሙ የአማራ ልሂቃንና ጠቅላላ ተወላጆች እንዲሁም ዜጎች በመናበብ ከፉከራና ካደባባይ ሽለላ በመውጣት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ፣ መንግስታቸውን እንዲያግዙ አስተያየት እየተሰጠ ነው። አሁን ክልሉን የሚመራውን መንግስት በመደገፍ እንጂ በመግፋት ለክልሉ የተሻለ ነገር ማምጣት እንደማይቻልም አመላክተዋል።

በየቀኑ ስድብና ትችት ላይ ተመርኩዘው ፕሮፓጋንዳ የሚነዙትን ማስቆም ካልቻለ ክልሉም ሆነ በትግራይ አዋሳኝ ያለው የአማራ ሕዝብ አጉል ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ስጋታቸውንም አስቀምጠዋል።

Exit mobile version