Site icon ETHIO12.COM

በጅግጅጋ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእርዳታ ስንዴ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ከሰኔ 12 እስከ ሰኔ 18/2013 ዓ.ም ድረስ ከ56 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

ከነዚህ የኮንትሮባንድ እቃዎች አንዱ 33 ሚሊየን 100 ሺህ ብር ግምት ያለው ለዕርዳታ እንዲውል ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወደ ሀገር ገብቶ በጅግጅጋ ሲንቀሳቀስ የተያዘ ስንዴ ነው፡፡

በሳምንቱ ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች

• የገቢ ኮንትሮባንድ 54 ሚሊዮን 211 ሺህ 562 ብር
• ወጪ ደግሞ 2 ሚሊዮን 722 ሺህ 916 ብር ግምት አላቸው፡፡

ከእቃዎቹ መካከል ስንዴ፣ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ መድኃኒትና ሌሎች ናቸው፡፡ 32 ያህል ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ ተይዘዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ለኮንትሮባድ እቃዎቹ መያዝ ኅብረተሰቡ ብሎም የጸጥታ አካላት ላደረጉት ትብብር ምስጋናውን ገልጿል፡፡ በቀጣይም ኮንትሮባንድ ለመከላከል በሚከናወነው ሥራ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስቴሩ ጠይቋል፡፡

ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ

Exit mobile version