Site icon ETHIO12.COM

የትግራይ የተቆላለፈ እጅ፤ እየቀለበች የምትደማ አገር

በትግራይ የተጀመረው ጦርነት ማንም ጤነኛ አዕምሮ ባላቸው ዘንድ የተፈጠመው ሶስት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር። ምቱ፣ ፍጥነቱ፣ ስትራቴጂው፣ ውጤቱ በሙሉ ስኬት የተደመደመ እንደነበር ባለሙያዎች መስክረውታል። የቀድሞው ጀነራል ጻድቃንም ” ማሰባና መደራጀት እንዳንችል ሆነን …” ሲሉ የጥቃቱን ክብደት፣ ” ሜካናይዝድ የነበረው ሃላችን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ተራ ተዋጊ ተቀየረ” በማለት ክስረቱን በይፋ መስክረዋል።

በጦርነቱ የነበረው ዝግጅት ሲተን ሁለተኛው ዓማራጭ ” የተቆላለፈ እጅ ” መዘርጋት ነበር። ከድሉ በሁዋላ በየአቅጣጨው የጭፈራ ተስካር ሲበዛ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” ጭፈራ ይቁም” ሲሉ የሚሰማ ጠፋ። ድሉን በጥብቅ ዲሲፒልን የማጀብ አቅም ስላልነበር ለስውር እጆች በር ከፈተ። ይህንኑ ክፍተትና በትግራይ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የተፈጸሙ ግድፈቶችን፣ ጦርነት በባህሪው የሚወልዳቸውን ሰንካዎች በማጉላት ውስብሰቡ እጅ ጦርነቱን አናረው።

የተቆላለፈው እጅ

የተቆላልፈው እጅ የሚባሉት አብዛኛው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደ መዋቅር፣ የዕርዳታ ድርጅቶች፣ የውጩ ዓለም ሚዲያዎች፣ በሁለቱ ጫና በስውር አጀንዳ ” ሆ” ብሎ የተነሱት መንግስታት በዋናነት አክተር የሆኑበት ነው። ስዩም ዘበነ እንደሚለው የእርዳታ ድርጅቶች ኢትዮጵያን ወግተዋታል። አስወግተዋታል። ገና ያስወጉዋታል። ስዩም ይህን ሲል አስቀድሞ የሚገልጸው ዋና ምክንያት ዕርዳታ ድርጅቶች ወደ ትግራይ ሲገቡ ቅድሚያ የጠየቁት ” የራሳችን የግንኙነት መሳሪያ ካላስገባን እርዳታ ስራው ላይ አንሰማራም” የሚል ነበር። የቀደመው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ድጋፍ ታክሎበት ጥያቄያቸው ” እሺ” በሚል ምላሽ ፈቃድ ሲሰጥ በሳምንታት ውስጥ የትህነግ የበረሃ ክንፍ ዓለምን ማግኘትና መግለጫ መስጠት ጀመረ። በዛም የተነሳ መንግስት እጁን ያስጠመዘዝ ጀመር። ውጭ ያሉትን ክንፎቹን በመጠቀም ጭምር …

መንግስት የሰራውንም ያልሰራውንም እያቀነባበሩ ከበረሃ ወደ ዓለም እንዲያሰራጩ በተፈጠረው አጋባብ መንግስት ላይ ጭና ተፈጠረ። መንግስት ለመቆጣጠር ሲሞክር ” አደናቃፊ” በሚል ከተባበሩት መንግስታት ጀምሮ መግለጫ እንዲረጭ፣ የውጩ ሚዲያዎች ቀድመው በሪፖርታቸው ዓለምን እንዲያዳርሱ የስዕል መረጃና የመነሻ ሃሳብ በፍጥነት እንዲያሰራጩና በፕሮፓጋንዳው የበላይ እንዲሆኑ አስቻሏቸው። በየአቅጣጫው መንግስት ላይ የሚወርደው ጫና ስለበዛ፣ ማዕቀቡም እየጠበቀ በመሄዱ መንግስት ሰዶ ማሳደዱን ገታ። እንደውም ሃይሉን ተፋዞ ቁጭ አለ። ትህነግ እረፍት ወስዶ ተደራጀ። እነ ጊታቸውን ጭምር የልጆች አልሚ ምግብ እየበሉ፣ እንደ ወፍጮ አስፈጪ ኩንታል ላይ እየተኙ ተመልሰው አበጡ። ስዩም እንደሚለው ዳግም አገነገኑ።

ዕርዳታ

ስሙን ለመጠቀስ የማይፈልገውና በዓለም አቀፍ የዕርዳታ ተቋም ውስጥ የሚሰራ እንደሚለው ” መንግስት ገዳዮቹን ይቀልባል” ሲቀጥል እርዳታ ሰጪዎች ምግባራቸውን ያትታል። የመገናኛ መሳሪያዎችን እንዲያስገቡና ከቴሌ ሰርቨር ውጭ እንዲጠቀሙ ፈቃድ ካገኙ በሁዋላ ያደረጉት ነገር ቢኖር ” መታጀብ አንፈልግም” የሚል ጥብቅ ውሳኔያቸውን ነው።

ዕርዳታ ላይ የተሰማሩት ድርጅቶች የሚያሰራጩት 70 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያ የምታቀርበውን እህልና ቁስ ነው። ይህን እህል ሲያከፋፍሉ ለማን፣ ምን ያህል፣ የት፣ መቼ እንደሚያከፋፍሉ ሪፖርት ሲጠየቁ በዝርዝር አያስረዱም። ወይም ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም። 97 በመቶ ሰራተኞቻቸው የትግራይ ልጆች ሲሆኑ መከላከያ ፍተሻ ሲያደርግ ” እርዳታውን አሰናከሉን” በሚል ባላቸው የግኙነት መሳሪያ ሪፖርት አድርገው መኪናውን ጥለው ይሄዳሉ። መንግስት በሪፖርትና በመግለጫ ይደበደባል። ሚዲያዎች እነሱን እየጠቀሱ መንግስትን “ረሃብን ለፖለቲካ ተጠቀመ” እያሉ ይቀጠቅጡታል።

ሌላው አስገራሚው ጉዳይ በሚል ይኸው ለዕርዳታው ስራ ቅርብ የሆነ እንደሚለው ሰራተኛ ሲቀትሩ ለአንድ ዕርዳታ ስርጭት፣ በጊዜያዊ ወይም በኮንትራት ነው። ለአንድ ስርጭት ሰራተኞችን ሲቀጥሩ ለምሳሌ 200 ከቀጠሩ ስማቸውንና አድራሻቸውን ለመነግስት ወይም ለጊዚያዊ አስተዳደሩ አይገልጹም። በቀጥታ የሚያደረጉት ለአንድ ጊዜ እደላ 200 ሰዎች መቅጠራቸውን ማሳወቅ ብቻ ነው። ከዛም እነዚህ ተቀጣሪዎች የይለፍ ታግ ይዘጋጅላቸዋል። ሳይፈተሹ እንዳሻቸው ይገባሉ ይወጣሉ። ሄደውም ይቀራሉ። ይህ ለትህነግ ታላቅ ድጋፍ አድርጓል።

የዕርዳታ እህል፣ ዱቄትና አልሚ ምግብ እየወሰዱ ማስረከብ፣ ተሻከርካሪ ውስጥ ነዳጅ ጭኖ ማቀበል፣ ተሽከረካሪ አስረክቦ በመምጣት ” ተወሰደብን” ማለት የተለመደ ሲሆን አንድም ሪፖርት አይቀርብበትም። መንግስት በዚህ መልኩ ትህነግን በረሃ ድረስ ቀለብ እየላከ እንዲቀልብ ሆኗል።የዓለም አቀፉ ጫናና ” ድርቅን ለፖለቲካ አዋለ” የሚለው የተጠና ቅስቀሳ መንግስትን አቅም አልባ ያደረገውም በዚህ ምክንያት ነው።

መድሃኒት

የፌደራል መንግስት መድሃኒት በብዛት ከላከባቸው ክልሎች ቀዳሚዋ አሁን በንፅፅር ትግራይ ናት። ይኸው ለእርዳታ ስራው ቅርብ የሆነ ወገን እንደሚለው መድሃኒት ወደ ዞን ሲላክ ሃላፊዎች ይዘው ወደ በረሃ የሚሄዱበት አግባብ የተለመደ ነው። ለምሳሌ ምዕራብ ዞን ትግራይ ይህ የተለመደ በመሆኑ አራት ጊዜ ሃላፊ ተቀይሯል። ዕርዳት እህል ብቻ ሳይሆን መድሃኒትም ከሕዝብ ላይ እየተነጠቀ ወደ ጫካ ሲላላክ ይታወቃል። ግልጽ ነው። ማንም ግን ተቃውሞ አያሰማም። ልክ መንግስት እንደሚወቀሰው ” ትህነግ መድሃኒትና እህል ከተረጂዎች ጉሮሮ እየነጠቀ ይወስዳል” አይባልም። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያልጸዳ በመሆኑ ይህን በመቃቅወም እንኳን መግለጫ ሲሰጥ ታይቶና ተሰምቶ አያውቅም። እንደውም በተቃራኒው መንግስትን ነበር የሚያወግዙት።

እና ምን ይሁን?

በትግራይ የአገር መከላከያ ሰራዊት የሚዋጋው ውጊያ እጅግ ውስብስብና የተቆላለፉ እጆች ከፈጠሩት ጥምረት ጋር ነው። ስዩም ዘበነ እንደሚለው ያደጉት አገሮች እያራመዱ ካለው ልዩ ፍላጎታቸው የተነሳ ስልት ነድፈው እየሰሩ ነው። በትልቅ ክበብ ከተውን የጀመሩትን ዘመቻ እያጠበቡት ነው። ሰሞኑንን ማንም ሊክደው በማይችል ትህነግ አገግሞ በወገን ሃይሎች ጥፋት ጭምር ጥቃት አድርሷል። ይህ ሊቀጥል ይችላል።

ትህነግ ሰላማዊ ዜጎች አስመስሎ ሃይሉን ወደሚፈልገበት ስፍራ ያዟዙራል። ይህን የሚሰሩ ዕርዳታ ድርጅቶች አሉለት። ካሻው 500 እለታዊ እርዳታ የሚያከፋፍሉ እፈልጋለሁ ብሎ ይለፍ ሰጥቶ የትህነግን ሃይል በክብር ወደሚፈለገው ቦታ ይላክል። የኢትዮጵያ ሰርቨር የማያውቀው የሳተላይት መስመር ስለቀረበለት በዛው መስመሩ ይገናኛል። ስዩም በርካታ ጉዳዮችን ዘርዝሮ ” ሲመታ ጀግና ሲመታ ሲቪል” የሚሆን ጎሬላ፣ በውስብስብ እጆች የሚደገፍ ጎሬላ፣ ማሸነፍ ከባድ ነው።

እንደ ስዩም አባባል የትህነግ መርዛማው አናቱ ተመቷል። ትህነግ እንደ ድርጅት ለሌሎች ስጋት የመሆን እድሉ በርክታ ዓመታትን ይፈጃል። ስለዚህ ከኤርትራ ግራ ድንበርን አጥሮ፣ በሱዳን በር ዘግቶ፣ ለውልቃይትና ለራያ ሕዝብ ከለላ በመሆን ትግራይን ለቆ መውጣት የሚሻል አማራጭ ነው።

ድንቁ ሃይሌ የስዩምን ሃሳብ ይደግፋል። እሱ እንደሚለው ዛሬ ላይ 47 ዓመቱ ነው። እድሜውን በሙሉ ስለትህነግ ሲሰማ ነው የኖረው። ” እድሜዬን በሙሉ በነሱ ክፋት ስጨነቅ ለምን እኖራለሁ” ይላል። እሱ ብቻ ሳይሆኑ በነሱ ምክንያት ቤተሰቡን ያጣው ጥቂት አይደለም። ስልጣን ላይ ከወጡም በሁዋላ በአድልዎ አገሪቱን ዘርፈዋታል። ስለሆነም እንዲህ ካለ ቡድን ጋር መቀጠል አግባብ እንዳልሆነ ይገልጻል።

ድንቁ እንደሚለው መከላከያ በደንብ አጥንቶ የአጭር ቀን ሙሉ ጥቃት አካሂዶ ከቻለ ዋናዎቹን በመደምሰስ፣ ካልሆነም አሁን የገነቡትን ሃይላቸውን አመናምኖ ትግራይን ለቆ ሊወጣ ይገባል። ከዛ የትግራይ ሕዝብ ያሻውን ይወስን ሲልም ሃሳቡን ያጠቃልላል።

የሃምሳ አለቃ በቃሉ ሳህሌ ” ከድሮ ጀምሮ ትህነግ ኢትዮጵያን ሲወጋ የኖረበት ምክንያት አይገባኝም” ይላሉ። ኢትዮጵያም ለዚህ ለሚያደማት ሃይል ሃብቷን ለምን እንደምታባክን መረዳት አልቻልኩም” ባይ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት መገላገል መፍትሄ ነው። መገላለገሉ ግን አንድ እግር እዚያ አንድ እግር እዚህ ሳይሆን ተጠቃሎ በመሰላማዊ መንገድ መለያየት ነው። ሁለት ቦታ መብላትን ኢትዮጵያዊያ እንደማትፈቅድ ካሁኑ በአደባባይ መነገር መጀመር እንዳለበ አክለው ገልጸዋል። ” እኛ እንደሰለቸን በአደባባይ መናገርና መለያየቱ እንዴት መፈጸም እንዳለበት በገሃድ ውይይት መጀመር አለበት። መደባበቅ አያስፈልግም”

በአብዛኛው የትግራይ አንቂዎችና አሁን እየተካሄድ ያለውን ጦርነት በድል ለመወጣት እየተንቀሳቀሱ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ” ከኢትዮጵያ ጋር በቃን፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አናውቅም፣ ለትግራይ የማትሆን ኢትዮጵያ ትፍረስ… ” ሲሉ መስማት እጅግ የተለመደና መሪ ቃል ሆኖ እያገለገል ነው።

የኢትዮያጵያ መከላከያ ሰራዊት የታረደ እለት ነገሮች እንዳከተመላቸው የሚናገሩ ያሉትን ያህል ሕዝብና ድርጅት ሊለይ እንደሚገባ የሚከራከሩ ጥቂት አይደሉም።

በዚህ አሳብ ዙሪያ አስተያየት፣ የመፍትሄ አሳብ፣ ያላችሁ ብትጠቁሙን ወይም ብትጽፉልን እናትማለን

Exit mobile version