“የህግ የበላይነት ለማስከበር እየተወሰደ ያለዉን እርምጃ መቋቋም የተሳናቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪዉ ሸኔ አባላት ለመንግስት እጅ ሰጡ” ሲል የዘገቡት መገናኛዎች እንዳሉት ድርጅቱ ቁመናው ፈርሷል።
በቅርቡ በታንዛንያ ለስምምነት ብዙ ርቀት ከተኬደና ከንግገሩ መልካም ዜና የተጠበቀ ባለበት ወቅት ስምምነት ላይ እንዳልተደረሰ መንግስት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በሰላም ንግግሩ የተኩስ ማቆም ስምምነት ተደርሶ እንደነበር፣ አነጋጋሪ የነበረው የስምምነቱ ቴክኒካል አፈጻጸም ጉዳይና ታጣቂዎችን አስመልክቶ እንዴት ይስተናገድ የሚል እንደነበር ውይይቱን የሚከታተሉ አስታውቀው መግለጻችን ይታወሳል።
በሁሉም ረገድ እጅግ ተስፋ ሰጪ ስምምነት ላይ እየተደረሰ ቆይቶ በመጨርሻው ቀን ሙሉ የአቋም ለውጥ በማድረግ ከአመክንዮ ውጭ የሆነ ጥያቄዎችን በማቅረቡ ውይይቱ መጨናገፉ ይፋ ቢሆንም፣ ቀጣይ ንግግር እንደሚኖር ተጠቁሞም ነበር።
በታንዛንያ ንግግሩ እየተደረግ ባለበት ወቅትም ቢሆን ወታደራዊ ኦፕሬሽኑን ያላቋረጠው መንግስት በተለያዩ ቀናት ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ ጉዳት እያስተናገደና ታጣቂዎቹ በተለያየ መጠን እጅ መስጠታቸው ሲገለጽ ስንብቷል። ብዙ ባይባልም መሳሪያ መማረኩንም በምስል የሚያሳዩ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።
ዛሬ ኦቢኤን እንዳለው ከሆነ በሺህ የሚቆጠሩ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እጅ ሰጥተዋል። እጃቸውን የሰጡት መከላከያ የሚያሳርፈውን ድብደባ መቋቋምና መመከት ባለማቻላቸው ነው።
“የተወሰደባቸዉን እርምጃ መቋቋም ተስኗቸዉ የተማረኩት ታጣቂዎች እንደ ተናገሩት ሸኔ ክፉኛ ተመትቶ በመፍረስ ላይ ይገኛል:” ያለው ሚዲያው “የሸኔ ኃይል በዉስጡ በተፈጠረዉ መከፋፈል እርስ በራሱ ወደ መጠፋፋት የተሻገረ በመሆኑ ለመንግስት እጅ ሰጥተናል” ሲሉ ታጣቂዎቹ ተስፋ መቁረጣቸውን አስታውቋል።
“ሸኔ የፍትህና የህዝብ ጥቅም ጠላት በመሆኑ እየፈረሰ ነው” ሲሉ እነዚህ የተማረኩትና በሰላም እጃቸዉን ለመንግስት የሰጡ የሸኔ ታጣቂዎች መናገራቸውን ዘገባው አክሎ ገልጿል። ይህን አስመልክቶ ኦነግ ሸኔ ይህ እስከታተመ ድረስ ማስተባበያ አልሰጠም።
- ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?ያለፈውን ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ሥነ መንግሥት ታሪክ በጥሞና የተከታተለ ኢትዮጵያዊ የግዛት አንድነቷን እና የፖለቲካ ነጻነቷን በአንጻሩ ጠብቃ የኖረች ሀገር፤ ከአሁን… Read more: ምን ያክል ተዘጋጅተናል? ጥድፊያ አገር አልባ ለመሆን !! ህጻናቱ ምን አጠፉ?
- የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስአንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነ እና በጊዜው ሕክምና ካላደረገ ለከፍተኛ የልብ በሽታና በደም ዝውውር ማነስ ምክንያት ለሚከሰት የአዕምሮ ሥራ መታወክ (ስትሮክ)… Read more: የደም ግፊት በመለካትና ክትትል በማድረግ የስትሮክ ተጋላጭነትን መቀነስ
- የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶችየስኳር ህመም በደም ውስጥ የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ሆኖ በሚገኝበት ሰዓት የሚከሰት ተላላፊ ያልሆነ የህመም አይነት ነው። በዋናነት አራት የስኳር ህመም አይነቶች አሉ፤… Read more: የስኳር ህመም አይነቶች እና ምልክቶች
- ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ማንኮራፋት ከሚያንኮራፉት ሰዎች ጎን በሚተኙ ሰዎች አካላዊ እና አእምሮ ጤና ላይ ጉዳት ያስከትላል። ትዳርንም ሊያፈርስ ይችላል። “ስለ… Read more: ማንኮራፋትና ትዳርን እስከ ማፍረስ የሚያደርሰው መዘዙ ? ማንኮራፋት መፍትሄ አለው?
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership