ETHIO12.COM

ነዋሪው ሀጫሉ! “ስሙን ባልተገባ መንገድ አትጠቀሙ” ቤተሰብ

“ጀዝመኛው” ሃጫሉ ደፋርና አሳቡን በገሃድ የሚገልጽ የሕዝብ አፍ፣ ስሜትና ወኪል እንደሆነ ስራዎቹን የሚከታተሉ ይመሰክራሉ። ለሕዝብ ቅርብ የሆነ በመሆኑ የሕዝብ ስሜት ለማንጸባረቅ አይቸገርም። የሚያውቁት የቅርብ ባልደረቦቹና ቤሰቦቹ በተለያየ ወቅት እንዳሉት እጅግ ደግና ለጋስ መሆኑ የህዥብ ስሜት ባሪያ ያደረገው አርቲስት ነው።

ለውጡ አፋፍ ላይ በደረሰበት ወቅት በሚሌኒየም አዳራሽ ” ኦሮሞ እስር ቤቱን ሞላው” እያለ በጊሬርሳ የወቅቱ ፈለጭ ቆራጮች ፊት እንደ ዋላ እየዘለለ ሲተገትጋቸው የነበረውን ስሜት ላስተዋለ ሃጫሉ የህዝብ አፍና ልብ መሆኑ ከመረዳት ውጭ ሌላ ማድረግ አይቻለወም። እሳት እየተፋ፣ ትንታግ ሆኖ የህዝብን ስሜት ሲያሰማ የሚያለቅሱ፣ በስሜት ከተቀመጡበት ሊነሱ የከጀሉ፣ አንገታቸውን የደፉ … ብዙ ዓይነት ሰዎች ይታዮ ነበር።

በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ህይወታቸው ያለፈው አቶ ዘርዓይ ስገዶም ይህን ድንቅ ትዕይንት ” እንዴት በመንግስት ሚዲያ ይተላለፋል” በሚል ቅሬታ ማሰማታቸው የውቅቱ መልዕክት ሃያልነት የትህነግን ሰዎች እንዴት እንዳራዳቸው ማሳያ ነበር። ለዚህም ይመስላል ሃጫሉ የአንዳንድ የኦሮሞ አክቲቪስትና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ነን ያሉ ከትህነግ ጋር መቀለ አዲስ ፍቅር መጀመራቸውን ” ሞት ይሻላል” ሲል የተቃወመው።

የሃጫሉ ባለቤትና ወላጅ አባት

የታሰረው፣ የተገረፈውና ማስፈራራት ሲከተለው የነበረው ሃጫሉ በሁሉም ውስጥ ሆኖ የህዝብ ድምጽ ሆኖ ያሸለበ ልዩ የኪነት ሰው ነው። ሃጫሉ ካለፈ አንድ ዓመት ሆነው። በሙት ዓመቱ ዳግም ያበራ ዘንዳ ቤተሰቦቹ ታላቁን ስጦታ አቀረቡ። ሃጫሉ በህይወት እያለ ያዘጋጀውን አልበም አስመረቁ። በዚሁ ስነስርዓ ላይ ቤተሰቦቹ ሃሳባቸውን አሰምተዋል።

በዚሁ አዲስ አበባ በተካሄደ ዝግጅት ”…ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው” ሲሉ አባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ መናገራቸው ከላይ የተባለውን ሃሳብ የሚያጸና ነው።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ የዘፈን አልበም ምርቃትና የአንደኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተው ነበር።

አርቲስቱ በህይወት እያለ ያዘጋጀው ሶስተኛው የዘፈን አልበም፤ ‘ማል መሊሳ’ በሚል ርዕስ ታትሞ ለአድማጮች ቀርቧል።የዘፈኑ 300 ሺህ ቅጂ በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጀ ሲሆን አልበሙም 14 ዘፈኖችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ለአርቲስቱ ሙት ዓመት መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአርቲስቱ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ”ሀጫሉ በህይወት ቢለይም ትውስታውና ስራዎቹ ህያው ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። ይህንኑም በተግባር አሳይተዋል።

ከአርቲስቱ ህልፈት ቦኃላ ከቤተሰቡ ጎን ሆነው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉላቸው ሁሉ ምስጋና ያቀረቡት ወይዘሮ ፋንቱ “የአርቲስቱን ስም ባልተገባ መንገድ ለመጠቀም የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ” የሚል ጥሪ አሰምተዋል።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ”ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው” ብለዋል።”የልጄ ገዳዮች ህግ ፊት ቀርበው ፍትህ እንዲያገኙ ሁሉም እንደየ ሀይማኖቱ ጸሎት ያድርግልኝ” ሲሉም ጥ አቅርበዋል።በመርሃ-ግበሩ የጥበብ ስራዎችን የሚያግዝና በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመ ፋውንዴሽን ተቋቁሟል።አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ 22 በአዲስ አበባ በክፉዎች ውጥን መቀጠፉ ይታወሳል።

Exit mobile version