ETHIO12.COM

መቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁኔታ አሳስቧል፤

መቀለ ዩኒቨርስቲ ያሉ የሌላ ክልል ተማሪዎች የደህንነት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተሰማ። የትህነግ ሃይል መቀለን ሲቆጣጣር የስክል መስመሩን ስላቋረጠ ቤሰቦች ልጆቻቸውን ማግነት አልቻሉም። “ባንዳ” በሚል ጥቃት መቀተሉም እየተሰማ ነው።

May be an image of 4 people, people standing and outdoors
ማይጨው የሚገኘው የራያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ግቢውን ለቀው በአማራ ክልል ራያ ከተማ አላማጣ አድርገው ወልዲያ ገብተዋል::

በመቀለ ስልክ ባለመስራቱ ተማሪዎችን ማግነት እንዳልተቻለ ቤተሰ እየጠቆመ ነው። በመቀለ ምን ያህል የሌላ ክልል ተማሪዎች እንዳሉ እስካሁን ይፋ መረጃ አልወጣም። በጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ የሚመላከታቸው እስካሁን ያሉት ነገር የለም።

ለውጡ ተከትለው ወደ አገር በመመለስ ሰፊ መግለጫ ሲሰጡና ትህነግን ሲያጋልጡ ቆይተው፣ ወደ ትውልድ መንደራቸው እንደርታ በመመልስ የማረጋጋት ስራ ሲሰሩ የነበሩት አቶ ሊላይ ሃይለማርያም (የብላታ ሃይለማርያም ልጅ) “መከላከያ ከትግራይ ከተሞች መውጣቱ ተከትሎ ዘር ተኮርና የአመለካከት ልዩነት ኣላቸው በተባሉ የእንደርታ ተወላጆችና ከብልፅግና ጋር ግኑኝነት አላቸው በተባሉት ላይ የኣድዋው ነፃ አውጪ ግድያና አፈና በመቐለ እያካሄደ ነው። በ3 ሲኖ ትራክ ጭኖም ወደ ተንቤን አቅጣጫ ወስዳቸዋል” የሚል መረጃ በግዕዝ ሚዲያ በኩል አሰራጭተዋል።

ይህ መረጃ ከመውጣቱ በፊት ከሰላሳ በላይ ሰዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩን ደግፋችኋል በሚል መገደላቸው ተሰምቶ ነበር። ትህነግ መከላከያ ከወጣ ብሁዋላ ወደ ከተማ ሲገባ ተውሰደ የተባለው እርምጃ ” ርሸና ነው” ሲሉ የጠሩትም አሉ።

አብዣኛው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካላት ትግራይን ለቀው ሲወጡ፣ አራቱ “መቀለ እንቆያለን” ብለው ከበረሃ ከገባው ሃይል ጋር ስ ራ መጀመራቸውም ተሰምቷል።

ማይጨው የሚገኘው የራያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ ግቢውን ለቀው በአማራ ክልል ራያ ከተማ አላማጣ አድርገው ወልዲያ ገብተዋል::

Exit mobile version