Site icon ETHIO12.COM

የተከዜ ድልደይ መፍረስ- አጫጭር መረጃዎች

የተከዜ ድልድይ ፈረሰ

የተከዜ ድልድይ መፍረሱን ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅት አስታውቋል። የዕርዳታውን አቅርቦት ከበፊቱ በበለጠ እንደሚያደናቅፈው መናገሩን የዘገበው ሮይተርስ ነው። የዓለም የምግብ ድርጅት ቃል አቀባይ ፒተር ስሜርደን ድልድዩ መፍረሱን አረጋግጠዋል። ሮይተርስ የጠየቃቸው የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መፍረሱን እንደሚያውቁ ጠቅስው በዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥበት አመልክተዋል።

ፒተር ስሜርደን የድልድዩ መፍረስ በዕርዳታ አቅርቦቱ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ እየተጠና መሆኑን ገልጸዋል። ከጎንደር ሽሬ ወደ ሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በአስቸኳይ የሚፈለግ የምግብ አቅርቦት ለማድረስም አማራጭ መንገድ እንዳለም እያጠኑ መሆኑንም አመልክተዋል።

ካምፓላ፤ ከ800 በላይ ሰዎች የሀሰት የኮቪድ ክትባት ተከተቡ

የዩጋንዳ ፖሊስ በሀገሪቱ ሀሰተኛ የኮሮና ተሐዋሲ ክትባትን በመስጠት የተጠረጠሩ ሁለት ነርሶችን ማሰሩን አስታወቀ። ዶክተር ነኝ ብሎ ይኽንኑ የሀሰት ክትባት ለበርካቶች ሲያዳርስ የነበረ ግለሰብንም እየፈለገ መሆኑን ገለጸ። በፖሊስ የሚፈለገው ግለሰብ በርካታ ኩባንያዎች ለሠራተኞቻቸው የሀሰት ክትባቱን እንዲሰጡ ማግባባቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ለአንድ ክትባትም ከ28 እስከ 56 ዶላር ድረስ ማስከፈሉም ተገልጿል።

ግለሰቡ ለገንዘብ ብሎ ተራ ወንጀል መፈጸሙን የገለጹት የሀገሪቱ የጤና ጉዳይ ተከታታይ ተቋም ኃላፊ ዶክተር ዋረን ናማራ ምናልባትም ቀለምም ሆነ ሽታ ስለሌለው ሰዎችን ውኃን መድኃኒት ነው ብሎ ሳይከትም እንዳልቀረም አመልክተዋል። የኮሮና ክትባት ነው የተባለውን የሀሰት ክትባትብ ቢያንስ 812 ሰዎች ሳይከተቡ እንዳልቀሩም ተገልጿል። ወረርሽኙ ዩጋንዳ ውስጥ መስፋፋቱ በርካቶች ክትባቱን ለማገኘት ቀኑን ሙሉ ረዥም ሰልፍ እንዲጠብቁ አስገድዷል። የዩጋንዳ የጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ ከ79 ሺህ በላይ ሰዎች በተሐዋሲው መያዛቸውን መዝግቧል። 900 የሚሆኑ ደግሞ በዚሁ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። 843 ሺህ ሰዎች እስካሁን የኮቮድ 19 ክትባት ያገኙ ሲሆን የክትባት እጥረት መኖሩን ዘገባው ጠቅሷል። DW

ቤጂንግ፤ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ መቶኛ ዓመት

ቻይና የኮሙኒስት ፓርቲዋን መቶኛ ዓመት ዛሬ ስታታከብር ከማይቀለበስ ደረጃ ላይ እንደምትተኝ ፕሬዝደንቷ ተናገሩ። ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ዕለቱን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ቻይና በተጠቀጡት ዓመታት ከቅኝ ገዢዎች ውርደት ተላቃ ኃያል ለመሆን መብቃቷን አስታውሰዋል። ቀድሞ የሀገሪቱ ኮሚኒስታዊ መሪ ማኦ ዜዱንግ ንግግር ያደርጉበት በነበረው መድረክ ቆመው ንግግራቸውን በመቀጠልም «ከእንግዲህ ቻይናን እየተገነባቸው የሚባልበት ዘመን አበቃ» ሲሉም ሀገሪቱ የዜጎችን ገቢም ሆነ ብሔራዊ ኩራት በማስጠበቅ በኩል የደረሰችበት ስኬት አወድሰዋል። የቻይና ሕዝብ ማንኛውም የውጭ ኃይል እንዲያዋርደው አይፈቅድም ያሉት ፕሬዝደንቱ የሚሞክር እንደ ታላቅ ብረት ግንብ በቆመው 1,4 ቢሊየን ሕዝብ የከፋ ጉዳት እንደሚደርስበትም አስጠንቅቀዋል። አያይዘውም፤«እኛ ቻይናውያን ፍትህን የምናከብር እና የማንም ኃይል እና ጉልበት ማስፈራሪያ የማያዋክበትን ሕዝብ ነን። የቻይና ሕዝብ ጠንካራ ኩራትና በራስ መተማመን ያለው ሕዝብ ነው። በማንም ተዋርደን፤ ተጨቁነን ወይም በባርነት ተገዝተን አናውቅም፤ ባለፈው ታሪካችንም አልነበረም፤ ዛሬም የለም ወደፊትም አይኖርም።»ማኦ እና የማርክስ ሌኒናዊ ርዕዮተ ዓለም አራማጆች በጎርጎሪዮሳዊው 1921 ዓ,ም በዚህ ወቅት ነበር የኮሚኒስት ፓርቲን በቻይና የመሠረቱት። በዓለም ጠንካራ ከሚባሉ የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ 95 ሚሊየን የሚደርሱ አባላት አሉት። DW

ቤት ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተቀምጦ ሲታቀፍ ሲታጠብ የነበረ አንበሳ በማህበራዊ ድር አምባ ቪዲዮዎች በመታየቱ የካምቦዲያ ባለሥልጣናት ወርሰው ወስደውታል።

አንድ ቻይናዊ አንበሳውን ከውጭ አስገብቶ በዋና ከተማዋ ፐኖም ፔን በሚገኝ አንድ ቪላ ውስጥ እያሳደገው ነበር ብለዋል ባለስልጣናቱ። ምርመራ በሚያዝያ ወር የጀመሩት 70 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን አንበሳ ቲክ ቶክ ላይ ከተመለከቱት በኋላ ነበር፡፡ የ 18 ወሩ እንስሳ ወደ ዱር እንስሳት አድን ማዕከል እንዲዛወር ተደርጓል። ባለቤቱ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበት እንደሆነ ባለስወልጣናቱ አላሳወቁም።

የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኔት ፒክትራ ለኤ ኤፍ ፒ ዜና ወኪል እንደገለጹት በቲክ ቶክ ላይ በተጋሩ ምስሎች አንበሳው ታይቷል፡፡ “ሰዎች ብርቅዬ የዱር እንስሳትን እንደ የቤት እንስሳት የማሳደግ መብት የላቸውም” ብለዋል።

መንግሥታዊ ያልሆነው ዋይልድ አኒማል አሊያንስ የተባለ የእንስሳት አድን ድርጅት በፌስቡክ ገጹ ላይ “በመኖሪያ ቤት ያለው ሁኔታ ለዱር እንስሳ ተገቢ አይደለም” ሲል ጽፏል። በተጨማሪም “የአንበሳው የውሻ ጥርሶች እና ጥፍሮቹ በመነቀላቸው የኑሮውን ጥራት በእጅጉ የሚቀንስ ነው” ብሏል – ቢቢሲ

የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ስማርት ከተሞችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አንዱ ግብዓት መሆኑን ስማርት ሲቲ ፕረስ ያትታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ኢትዮ ቴሌኮም ደምበኞች የዳታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን ስማርት ምሰሶ በእንጦጦ ፓርክ ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ

የስማርት ምሰሶ ቴክኖሎጂ ከተለመዱት የመንገድ ዳር ምሰሶዎች ጋር የሚመሳሰል ነገር ግን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን የያዘ ነው፡፡

ከሚሰጠው አገልግሎት መካከል አንዱ፥ ሰፊ አካባቢን መሸፈን የሚችል እጅግ ፈጣን የአራተኛ ትውልድ (4ጂ)፣ አምስተኛ ትውልድ ( 5ጂ) እና የዋይፋይ አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ሌላው መኪና እና ታርጋን በቀላሉ መለየት የሚችሉ፣ የፊት ገፅታ ልየታን የሚያከናውኑ፣ ከፍተኛ የሆነ የቀለም ጥራት እና አጉልቶ የማሳየት አቅም ያላቸው የደህንነት ካሜራዎች ይኖሩታል፡፡

በተጨማሪም የአየር እና የድምፅ ብክለትን የሚለዩ፣ አደጋዎችን እና ወንጀሎችን በፍጥነት ለይቶ በመጠቆም የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ አሰጣጡን የሚያቀላጥፉ መጠቆሚያዎችን ይይዛል፡፡

እንዲሁም የመንገድ መጨናነቅ እና አደጋን የመሰሉ እንዲሁም ሌሎች የድንገተኛ ጊዜ መልዕክቶች የሚሰራጩበት ዲጂታል ስክሪንም የሚኖረው ይሆናል፡፡

የስማርት ምሰሶ አገልግሎቶች በዚህ ብቻ የተገደበ ሳይሆን “ሁሉን በአንድ” በሚለው የቴክኖሎጂው መርህ መሰረት ሰዎች ከያዙት መሳሪያ ጋር በቀላሉ ተናቦ ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሚውል ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Exit mobile version