Site icon ETHIO12.COM

“ለመከለከያ ሰራዊት ስጋ አብልተሃል” የተባለው ወጣት ተገደለ

የትህነግ ሃይል ወደ መቀለ ከተመለሰ በሁዋላ ” ከድታችሁናል” በሚል የረሸናቸው ነጹሃን ቁጥር ከአርባ በላይ መዝለቁ ቢጠቆምም እስካሁን ያወገዘ ዓለም ዓቀፍ ተቋም የለም። ትናንት እንደተሰማው በመቀለ ስጋ ቤት ከፍቶ የሚሰራ ወጣት ” ለምን ለመከላከያ ስጋ አበላህ” በሚል መገደሉ ተሰምቷል። ግድያውን አስመልክቶ አቶ ጌታቸው እስካሁን አልተጠየቁም ወይም አላስተባበሉም።

“ሕሸ አዲሱ በመቐለ ኩሓ ክፍለ ከተማ የሚኖር ወጣት ነበር። አዲሱ ስጋቤት ከፍቶ ብዙ ደንበኛም ነበረው። መከላከያ ከትግራይ ለቆ ከወጣ ቦሃላ ጁንታው መቐለ ገብቶ ንፁሃን ሰዎች እጅግ በሚዘገንን መልኩ እየገደለ ይገኛል ለአዲሱም “በስጋ ቤትህ መከላከያ ይበሉ ነበር” በሚል ሰበብ በጣም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ገድለው አካላቱ ቆራርጠው መንገድ ላይ ጥለውታል” ሲል የዘገበው ግዕዝ ሚዲያ ነው።

ይህ ሃይል መቀለ ከገባ በሁዋል በርካታ ሰዎች መገደላቸውና በጭነት መኪና እየተጫኑ ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዳቸውን እየገለጹ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ቢሆንም ከክልሉ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

Exit mobile version