የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የባንክ አገልግሎቶች፣ የስልክ መስመሮችና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ችግር መኖሩን አስመልክቶ ከዓለም ዓቀፍ አካላት ለቀረበለት ጥያቄ የባክን አገልግሎቶችን በትግራይ መስልሶ እንደማይከፍት ማስታወቁ ተገለጸ። ቀደም ሲል የትህነግ ሃይል አፍርሶት የነበረውን የኤሌክትሪክና የስልክ መስመር ሲጠግኑ የነበሩ መገደላቸውን አስታወሶ አገልግሎቶችን ማስጀመር እንደሚቸግረው ገልጿል።
ይህ የተባለው ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ከሆነ ዲፕሎማቶችና የዓለም ዓቀፍ ተቋማት አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት ወቅት ጥያቄ ቀርቦ ነው። ድርጅቶቻቸውና ወኪሎቻቸው በሪፖርታቸው የጠቆሙትን ችግር አንስተው የባንክ፣ የስልክና የኤሌክትሪክ ችግር መኖሩን ጠቅሰው አገልግሎቶቹን መንግስት እንዲያቀርብ ላቀረቡት ጥያቄ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬድዋን ናቸው።
አቶ ሬድዋን ” ባንኮች አትራፊ ተቋማት ናቸው” ብለዋል። ተቋማቱ ብር ተሸክመው ሄደው ለመስራት የጸጥታ ማስተማመኛ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር መንግስት አሁን ባለው የትግራይ ወቅታዊ ቁመና ሃላፊነት አይወስድም።
“በትግራይ መንግስት የለም” ሲሉ ያስታወቁት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲህ ባለው ሁኔታ በየትኛውም ዓለም የገንዘብ ተቋማት ሃብታቸውን ተሸክመው ባንካ ከፍተው ሲያገለግሉ ታይቶ እንደማያውቅ ሁሉ በኢትዮጵያም ሊሆን እንደማይችል አመልክተዋል። አቶ ሬድዋን ” በሌላ ዓለም ያልሆነና የማይደረግ ጉዳይን አትጠይቁን” ሲሉ በሰጡት ምላሽ መግባባት መደረሱንና ጉዳዩ በአመክንዮ ሲመዘን ትክክል ስለመሆኑ ጠቅሰዋል። “ይህም ሆኖ ” አሉ ሚኒስትሩ ” ይህም ሆኖ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ባንክ ካለ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል” ሲሉ ተደምጠዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በትግራይ ክልል የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት መከሰቱን አመልክቶ ነበር። ኦቻ የስልክ፣ የትራንስፖርትና ነዳጅ እንዲሁም የኤሊክትሪክ ሃይል ችግር አሳሳቢ መሆኑንን ማመልከቱ አይዘነጋም።
አቶ ሬድዋን ” ቡድኑ በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ሲባረር እንደ ልማዱ መሰረተ ልማት አውድሞ ነበር” ሲሉ ነው ማብራሪያቸውን የጀመሩት። እሱ ያወደመውን የቴሌኮሙኒኪሽንና የኤሌክትሪክ መስመር ለመጠገን በተሰማሩ ባለሟዎች ላይ ጥቃት መድረሱን አስረድተው ፤ ” አልታጠቁም። ባለሟዎች ናቸው ግን ገደሏቸው” ሲሉ ከአስር በላይ መሃንዲሶችና ተጨማሪ ተባባሪ ሰራተኞች በትህነግ ሃይል እንደተገደሉ አስታውቀዋል። ለጥያቄው ልክ እንደ ባንክ አገልግሎቱ ” አናደረገውም” ሳይሉ ” ማን ሄዶ ይጠግናል? ካሁን በሁዋላ ለልማት እያሰራ የሚገደል ሰራተኛ ተቋማቱም መመደብ እንደማይችሉ አመልክተዋል። አያይዘውም የስልክ ጉዳይን አስመልክቶ ” ያላቸውን መጠቀም ይችላሉ” ሲሉ በዕርዳታሰጪነት ስም ገብተው የሳተላይት መስመር ማደላቸውን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብና ዲፕሎማቶች አዙረው ነግረዋቸዋል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው።… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት