Site icon ETHIO12.COM

ዓለም ጆሮ የነፈገው ዳግም እልቂት በትህነግ እየተፈጸመ ነው

ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች አስጨናቂ ናቸው። ዓለም በተለይም “ዕርዳታ እንሰጣለን” የሚሉና የመረጃ ሰዎች መሆናቸውን የሚናገሩ ሚዲያዎች ዛሬ ላይ ጆሯቸው መደፈኑ፣ ብዕራቸው መንጠፉ አነጋጋሪ ሆኗል። በትግራይ ጭፍጨፋ ስለመፈጸሙ በተደጋጋሚ ስምና ቦታ እየተጠቀሰ መረጃ ቢወጣም በትግራይ ያሉ ሚዲያዎችም ሆኑ ችጋር ላይ የሚሰሩ የሚመለከታቸውን ጠይቀው ያሰራጩት ነገር የለም። አዲስ አበባን፣ አማራ ክልልንና አስመራን እንደሚይዝ እያስፈራራ ያለው ትህነግም ማስተባበያ ሲሰጥ አልተሰማም።

ከትግራይ አላማጣ አርባ ኪሎሜትር ርቃ ትገናለች በምትባለው መኾኒ ዳግም የማይካድራ አይነት ጭፍጨፋ መፈጸሙን የመሸሽ እድል ያጋጠማቸውና መጠለያ ጣቢያ ለመግባት የቻሉ መናገራቸው ተጠቁሟል። መንግስትም በይፋ ስምና ቁጥር ጠቅሶ ባይጠቅስም ዜጎች ለምን ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር አበራችሁ በሚል እየተገደሉ መሆናቸውን አመክቷል። ለነብስ ያሉ የውጭ ድርጅቶችም የሚሰማውን ጭፍጨፋ ያክል ባይሆንም ሹክሹክታ እያሰሙ ነው።

በትግራይ ስልክና ኢንተርኔት አለመኖሩ ደግ ሆነ እንጂ ጉዳቱ እጅግ የከፋ እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች እየበዙ ነው። አንዳንድ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በትግራይ አሁን ያለው መገዳደል እያደገ ወደ ሽብር እንዳይቀየር ሰግተዋል። የፈረንሳይ ሚዲያ ትግራይን የሽብረተኛ መፈልፈያ እንደምትሆን ምልክት መታየቱን ዘግቧል። ከትግራይ በተደጋጋሚ መረጃ የሚያወጣው ዞባ ተምቤን የሚከተለውን አሰራጭቷል።

የንጥቂያ_ዘመን  መኾኒ_ዳግም_ማይካድራ

ከስፍራው ተገኝ ተብሎ ዞባ ተምቤን ሚዲያ ያሰራጨው ምስል ነው

ከትግራይ ክልል መከላከያ አይውጣ፣ ከተመለሱ የአማራ እርስቶች የአማራ ልዩ ሃይል አይውጣ የምንለው የማልቀስ አባዜ ኖሮን ሳይሆን ማይካድራን እያሰብን ሌላ ማይካድራ እንዳይፈጠር ነው።

በህይወት ዘመኔ የማይረሳኝ ሀዘን ስሜት ያየሁት ማይካድራ ነው። የሰው ልጅ በጅምላ ተገድሎ በጅምላ የተቀበረበት፤ የአስከሬኑ ሽታ የምድር ሲኦል ሲኦል ያሸተተበት ቦታ አረሳውም። ትዝ ባለኝ ጊዜ የማላውቀው ሃዘን ስሜት ይወረኛል። ዛሬም መሆን ማይካድራ ሆናለች።

#መኾኒ ከትግራይ አላማጣ 40 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ነች።

በአለም መንግስታት ጫና በፓለቲካ ውሳኔ መከላኪያ ሠራዊታችን ትግራይን ለቆ በወጣ በሁለት ሰዓት ልዩነት በህዋሃት አሸባሪዎችና ታጣቂዎች መሆኒ ላይ ወረራ አድርገው ህዝብ ጨፍጭፈዋል። መሆኒን ዳግም ማይካድራ አድርገውት በደም አጥበዋታል። ከሞት ያመለጡ ወገኖቻችን መጠለያ ጣቢያ እንዳሉ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ #አንደርታ ተወላጆች እና ኩናማዎች እየተጨፈጨፉ ነው። ይህን እና መሰል የማያባራ ሞት እየሰማ ዘመናችንን መርገም ላይ ነን። ይህ ያለንበት ዘመን ጭንቀት፣ ጩኸት፣ ፍርሃት የነገሠበት ጊዜ፣ የታሪክ መፍለስ፣ የነገሮች እርስ በእርሣቸው መቃወስ፣ የአገር መበታተን፣ ማንነትን የመዘንጋት አባዜ በትውልዱ ላይ በስፋት የታየበት ነው።

ህዝቡ የተረጨውን አዚም ባያውቅም ከመሃል ልጆቹ አፍንጫቸውን አውዶ በል በል እያለ የሚገፋፋቸው ነገር ቢኖር፤ የአውሬነት ባህሪ ተላብሰው እርስ በእርስ መተራረድ፣ መጨፍጨፍ መገዳደልን የሚናፍቁ፣ ነፋሻው ንፋስ የሚያናፍሰው ዓየር ቢኖር ቀባሪ ያጣ የአስከሬን ሽታ፣ ታዳጊ ያጣ ትውልድ፣ አፋሸ ያጣ ደም በጥቅሉ  የአኬልዳማ_ጩኸት በርክቷል፡፡

ነገሩ ከወዲሁ የገባቸው እንስሳት ይህን ክፉ ወቅት ላለማየት በየዋሻው የተደበቁ ቢኖሩም አብዛኛዎቹ ደግሞ የሰው ሳይበቃ ጭራሽኑ ከአገር የሚሰደዱበት ጊዜ፣ ጨረቃ በፍርሃት የተደበቀችበት፣ ሠማይ በቁጣ በደረቅ ነጐድጓድ ያስገመገመበት፣ የሞት ጥላ በአገራችን ዙሪያውን ያጣለበት፣ ወንድም ከወንድሙ፣ እናት ከልጇ በዋይታና በለቅሶ የተለያዩበት፣ አብሮ አደግ በሀዘን ከንፈር የመጠጠበት፣ ባለትዳሮች፣ ፍቅረኞች በመሪር እንባ መራጨት የተለያዩበት የምፅዓት ቀን ….

 የንጥቂያ_ጊዜ …. ረግቶ የማያውቅ ለይምሰል የቆመ በየጊዜው የሚለዋወጥ ግራ የገባው ፖለቲካ፣ ህልም የሌለው ከራዕይ የራቀ የማያስተውል ትውልድ፣ የጨለማ ዘመን፣ ፈች ያጣ በቅዠት የተሞላ ህልም… ግን ይች አገራችን መች ይሆን ህዝቧ በአንድነቱ አምኖ፣ በአራቱም አቅጣጫ የሚኖረው? ነዋሪው በሰላም ተረጋግቶ፣ ለአንድነቱና ለአገሩ ተቆርቋሪ ዜጋ ሆኖ የሚኖረው መቼ ነው?

በፖለቲካው ዓለም የሚኖሩት ዜጎቿ ሁሌ በውጥረት፣ በወንበር ጥማት፣ በግዞት፣ በምቀኝነት፣ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በብሔር፣ በቋንቋ በቀለም፣ በዘር ክፍፍል… ዳግማዊት ባቢሎን ካደረጎት ውለው አድረዋል፡፡ መቼ ነው ግን ለአገሬ ማለትን የሚጀምሩት? በይምሰል መኖር ጉራ ብቻ…. የእፍኝት ሽንት፣ #የራስ_እዳ/#ለራስ_ቀሎ_መገኘት….. በቃ ይህ ነው የዜጎቿ ጩኸት፣ ይህ ነው ዝማሪያቸው? ታሪክ አጥፊ ትውልድ፣ በአጉል ሙገሳ የሚኖር፣ ራሱን እየዋሸ እየሸነገለ የሚኖር አስመሳይ ትውልድ፣ በቃ ይህ ነው የአገራችን እጣ ፋንታ ሁሌ ጦርነት፣ ሁሌ የልጆችዋን ደም የምትጠጣ ምድር፣ ሠላም የናፈቀች አገራችን….ኢትዮጵያ ።።።።።/።/።።/

በግፍ የተገደላችሁ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር!

ሔቨን ዮሐንስ


Exit mobile version