Site icon ETHIO12.COM

የተረሳው የኢሬቻ ግፍና ከህወሓት ጋር የተዘለቀው ፍቅር እሽሩሩ

የዛሬ አራት ዓመት የኢሬቻን በዓል ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ ያኔ ምኒልክ ቤተመንግሥት የነበረው አሁን መቀሌ ሆቴል የመሸገው ሕወሓት የተሰኘው የበረኻ ወንበዴዎች ቡድን ያደረሰው እጅግ ሰቅጣጭ ግፍ ፈጽሞ የሚዘነጋ አይደለም።

ዓመት ባለፈ ቁጥር ይህንን የግፍ ናዳ ስናስብ ተመሳሳይ ዕልቂት በአገራችን እንዲፈጸም የሚሹ የዚህ ዓመቱን ኢሬቻ ክብረበዓል በሰላም መጠናቀቁን በፍጹም የፈለጉት አልነበረም። ሆኖም ፍጹም ሰላም በሰፈነበት መልኩ በዓሉ ተጠናቅቋ።

ዓመታት አልፈው ያኔ የደረሰውን ግፍ ዘንግተው፤ ለኦሮሞ እንታገላለን የሚሉ ከህወሓት ጋር “ፍቅር እሹሩሩ” ማለታቸው ሕዝብን መናቅና መስደብ ብቻ ሳይሆን በቁሙ መግደልም ነው።

ከሁሉ በላይ ለኦሮሞ ሕዝብ እታገላለሁ የሚለው በቀለ ገርባ ህወሓት ያደረሰበት ግፍና ስቅየት (ቶርቸር) ረስቶ መቀሌ በመሄድ ከህወሓት ሹሞች ጋር ስብሰባ መቀመጡ ሳያንስ ስላሳለፈው ዘመን ሲጠየቅ “ህወሓት (እንኳን ቶርቸር ሊያደርገኝ አይደለም) ዝንቤን እንኳን እሽ አላለም” ሲል መደመጡ አሁን ያለበት ቦታ የሚንሰው ነው ያሰኛል።

ለማንኛውም ለትውስት፣ ለኅሊና ፍርድ፣ ሰከን ብሎ ለማሰብ ያመች ዘንድ የዛሬ አራት ዓመት “በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ” በሚል ርዕስ ያወጣነውን አሁን ደግመን አትመነዋል።       

በሕዝብ አቆጣጠር አሁን ሁሉም ነገር አበቃ

ዛሬ ጨለሞ ዋለ። ዛሬ አገር ማቅ ለበሰች። ዛሬ የሆነውን ማመን ይከብዳል። ቄጤማና ቅጠል ይዘው የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በጅምላ ተረሸኑ። “Down! Down! Woyane … Down! Down TPLF! …” በማለት ቁጣውን የገለጸ ሕዝብ እገዛሃለሁ በሚለው የትግራይ ህዝብ ተገንጣይ ቡድን (በህወሃት) ተጨፈጨፈ። ከአየርና ከምድር ጭስና ጥይት የተረጨበት ህዝብ፣ የሚገባበት ጠፍቶት የውሃ ራት ሆነ። ሞተ። ቆሰለ። በውሃ ተበላ።

“Down! Down! Woyane … Down! Down TPLF! …” የሚለውን ቀስቃሽ ንግግር ያደረገው ወጣት

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሚባለው የወንበዴው ቡድን መሪ መለስ ሞት በድንገት እንደ ቡሽ ክዳን አፈናጥሮ ሲወስደው ጥቁር ለበሶ ሳግ እየተናነቀው ዜና ያወጀው ተመስገን በየነ፣ ዛሬ ነጭ በነጭ ለብሶ አኻዝ ባይጠቅስም የሰው ህይወት ማለፉን የተናገረው “ሰፊውና የተከበረው የኦሮሞ ህዝብ” በማለት ነበር።

ተመስገን ከጌታቸው የተላከለትን ሰዎች “በመረጋገጥ” ሞታቸውን ሲተፋ ቢያመሽም ህወሃትና ወኪሎቻቸው የዘነጉት ነገር ቢኖር የኢሬቻ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ዛሬ አይደለም፤ እስካሁን በተደረገው የበዓሉ አከባበርም ሁከት ሲነሳና ሰዎች በመረጋገት ሲሞቱ አልተሰማም፡፡

ብዙዎች እንዳሉትና፣ በማህበራዊ ገጾች እንደታየው ከኖረው ሃዘን ጋር ተዳምሮ የዛሬው ሃዘን በሕዝብ አቆጣጠር ሁሉም ነገር መጠናቀቁን ነው፡፡

የማህበራዊ ድረ ገጾች ምስል አስደግፈው እንዳሰራጩት ዜናና የውጭ መገናኛዎች እንዳሉት ቢሾፍቱ የኢሬቻን በአል ለማክበር የተሰባሰቡት ዜጎች ብዛት እስከ አራት ሚሊዮን ተገምቷል። ቢቢሲ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሲል ሌሎች ከዚያም ያስበልጡታል።

እንግዲህ እዚህ ህዝብ መሃል ነበር መርዝ የተተኮሰው። ጭስ የተተኮሰው። ህዝብ አየር አጥቶ እንዲታፈን የተፈረደው። ከዚያም በላይ ከባድ መሳሪያ ሲተኮስ የተቀረጹት ፊልሞች አረጋግጠዋል። ታንክ ሲጠቀሙም በምስል ተይዟል። በአየር ላይም ሄሊኮፕተር ተባባሪ ነበር።

ይህ ሁሉ የመሳሪያ አይነት የተሰለፈው ለወገን መሆኑ አገርን በድፍን አሳዝኗል። በዚህ ሁሉ ዝግጅት በተካሄደ የጅምላ ጭፍጨፋ ንጹሃን ዜጎች ሞቱ። ዜናው ከተሰማበት ደቂቃ ጀምሮ የሚወጡት መረጃዎች አስደንጋጭ ናቸው። ለጎልጉል መረጃ የሰጡ እንዳሉት “ሕዝብ ሲቃወም ዝም ቢሉ ምን ችግር ነበረው? ሲቃወም ውሎ ሲመሽ ወደቤቱ ይሄዳል!” እኚህ ሰው እንዳሉት በዓሉ በሚካሄድበት ስፍራ ህወሃትን የሚያሰጋው ነገር የለም። ቀድሞውኑ ህዝቡ ተከቦ ነበር። የተከበበና ከመንገድ ጀምሮ ተልብጦ ሲፈተሸ የዋል ህዝብ ምንም አደጋ ሊያስከትል እንደማይችል የታወቀ ነው። “ሲጀመር ፍርሃቻ የያዘው ህወሃት ህዝብ ሲሰበሰብ ስለሚታመም ከበሽታው በመነጨ ምላጭ ስቦ ህዝብን ረሸነ። ጨፈጨፈ። አቆሰለ። ይህ የማይሽር ጠባሳ በየትኛውም ጊዜ ሙሉ ዋጋ ያስከፍላል። ይቅርታ የለውም። አሁን የይቅርታን ገመድ በጠሷት። አለቀ። ካሁን በኋላ …”

እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ ጎረምሶች … በያይነቱ በህወሃት መጨፍጭፋቸውን ህዝቡን አገንፍሎታል። በስፋት እንደሚባለው “አሁን ጊዜው ወያኔን በምትችለው ሁሉ ታገለው። ቦታ አትምረጥ፣ ጊዜ አትምረጥ … ወዘተ” የሚሉ ናቸው። የጅምላ ጭፍጨፋውን ተከተሎ አምቦ ህዝብ ቁጣውን አሰምቷል። በይፋ ባይነገርም እዚያም የህወሃት አንጋቾች ነፍስ አጥፍተዋል። ህዝቡም ንብረት አውድሟል። በሌላ በኩል ከቢሾፍቱ ወደደቡብ የሚወስደው መንገድ በበርካታ ቦታዎች ተዘግቷል፡፡

በጥልቀት መታደስ እያለ ሲፎክር የነበረው ህወሃት አመራሮችን ቀይሬአለሁ ብሎን ነበር፡፡ በመለስ ትዕዛዝ የአዲስ አበባ ንጹሃንን የጨፈጨፈው ወንጀለኛው ወርቅነህ ገበየሁን የኦሮሞ ህዝብ መሪ አድርጎ ከሾመ በኋላ የዛሬውን ዓይነት ጭፍጨፋ በማድረግ ወርቅነህ ለራሱና ለለማ መገርሣ “ሹመት ያዳብር” የሚያሰኝ ታማኝነቱን አሳይቷል፡፡

ህወሃት ጠርንፎ የያዛት አገራችን ጉዳይ አሳሳቢ ከሚባልበት ደረጃ አልፏል፡፡ በርካታ በሰላማዊ ትግል የሚያምኑ ሰላማዊ ሰዎች በዛሬው ዕለት ጠአቅጣጫ ለውጥ ሲያደርጉና ሲያሰሙ ማድመጥ የወንበዴው ቡድን ህወሃት ጉዳይ በሕዝብ አቆጣጠር ሁሉም ነገር ያበቃለት መሆኑን ያመላከተ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ጥቂት የሕዝብ አስተያየቶችን ከዚህ በታች አቅርበናል፤

#IrreechaMassacre

በርካቶች ኢሬቻ ሊያከብሩ ወደ ሆራ ሲሄዱ እንዲህ እያሉ ነበር …
“Nuti shororkessa miti, wayyaaneen shororkessadha”
“እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፤ አሸባሪው ወያኔ ነው”
ዋሹ?

Ye Kebede Yetnayet And here is the evidence . A highly trained government commando covering his face as a terrorist. Also a heavily armored “Zilla” (a heavily armored technical vehicle recently assembled at Beshoftu Armament industry of METEC). The picture says it all- the killing was planned well in advance.

Mahlet Fantahun

የኢሬቻን በአል እያከበሩ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰው ነገር እጅግ አሰቃቂ ነው። ለወትሮው ደብረዘይት/ቢሾፍቱ ከተማ ኢሬቻ በሚከበርበት ቀን፤ ወደ ሆራ በሚሄድ እና በሚመለስ ሰው ይጨናነቅ ነበር። ዛሬ ግን ከግማሽ ቀን በላይ አልቆየም። ወታደሮቹም ከየመንገዱ ያገኙትን እየደበደቡ ሲሰበስቡ ነበር። መንገዶቹ ጭር ብለዋል። ቢሾፍቱ ሆስፒታል በጣም በርካታ ህዝብ ተሰባስቧል። ግቢው ለቅሶ ቤት ነው የሚመስለው። እራሳቸውን ጥለው እያለቅሱ ወደ ሆስፒታሉ የሚሄዱ እናቶችን ማየት ይረብሻል። የሬሳ ሳጥን ይዘው የሞተባቸውን ቤተሰብ ሬሳ ለመውሰድ ሆስፒታሉ በር ላይ የሚጠብቁም አሉ።

READ THE FULL STORY ON GOOLGULE

Exit mobile version