Site icon ETHIO12.COM

የ”በጀት ይለቀቅልን ቅድመ ሁኔታና” ክተት በትግራይ! የአሜሪካ አማራን ማሳደድ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መንግስት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም በማድረግ ትግራይን ለቆ ሲወጣ ወደ ነበረበት ቁመና ተመልሷል። ይህንኑ አጋጣሚ በድል አዋጅ አጅቦ ደጋፊዎቹን በአዲስ አበባ፣ በመላው ዓለምና በትግራይ አስጨፍሯል። የድሉ ዓይነትና ይዘት፣ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ ሴራዎች ላይ መግባባት ባይኖርም፣ ትህነግ አሁን ትግራይን እጁ አድርጓል።

ትህነግ የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ተከትሎ ሰባት ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠ ሲሆን አብዛኞቹ አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረትና በርካታ ታዋቂ ሚዲያዎች ላይ ሲባሉ የነበሩ ቢሆንም አዲስ የተሰማው ” በጀት ልቀቁ” የሚለው፣ የታሰሩ በሙሉ ይፈቱና ዓለም ዓቀፍ በረራ በቀጥታ ወደ መቀለ የሚሉት ናቸው። መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁሙን ከሰብአዊነት መርህ አንጻር ሲያውጅ በህግ የሚፈለጉ የአገር መከላከያ ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙና ያዘዙ ላይ እንደማይላዘብ ይፋ ቢያስታውቅም ጫናው እንዳየለበት ከበቂ በላይ ምልክቶች አሉ። መንግስትም በይፋ እየገለጸ ነው።

የበጀት መለቀቅ ጉዳይን አስመልክቶ የተለያዩ አስተያየቶች፣ ፍርሃቻ፣ እንዲሁም ገንዘቡን የሚያስተላለፉ ተቋማትየሉም። የገንዘብ ሚኒትር አሕመድ ሸዴን የጠቀሰው ሪፖርተር “መንግሥት የትግራይ ክልል በጀት እንዴት መለቀቅ አለበት የሚለው አዲስ ክስተት በመሆኑ፣ አሁን ላይ ሁኔታውን ማንም መገመት አይችልም” ማለታቸውን አስነብቧል።

የ2014 ዓ.ም. ካፀደቀው በጀት 203 ቢሊዮኑ ለክልሎች ድጋፍ የሚውል ነው። በዚሁ የድልድል ሰሌዳ መሰረት ኦሮሚያ 69 ቢሊዮን ፣ ለአማራ 43 ቢሊዮን፣ ደቡብ32 ቢሊዮን፣ ሶማሌ 20 ቢሊዮን፣ ትግራይ 12 ቢሊዮን፣ ሲዳማ 8 ቢሊዮን ፣ አፋር 6 ቢሊዮን ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ 3.6 ቢሊዮን ፣ ጋምቤላ 2 ቢሊዮን ፣ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3.3 ቢሊዮን ፣ ሐረሪ 1.5 ቢሊዮን ፣እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 1.7 ቢሊዮን ብር  የድጎማ በጀት ተሰፍሮላቸዋል።   

በጀቱ ድርሻዋን ያስቀመጠላት ትግራይ ዛሬ ምንም ዓይነት የገንዘብ ተቋማት የላትም።የግልም ሆኑ የመንግስት ባንኮችም ነቅለው ወጥተዋል። በክልሉ የገንዘብ ችግር መኖሩ ቢጠቆምም አቶ ሬድዋን በአሁኑ ወቅት መንግስት ማንንም አስገድዶ ትግራይ መመደብ ወይም ባንኮች ስራ እንዲጀምሩ መግፋት እንደማይችል አመልክተዋል። ነገር ግን ትግራይ ገብቶ አገልግሎት መስጠት የሚወድ ካለ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ሪፖርተር አስተአየት የተየቃቸው አቶ የገንዘብ ሚኒስትሩ ” የበጀት አለቃቀቅና አፈጻጸሙ ገና ውይይት አንደሚፈልግና በሒደት እንደሚታወቅ ገልጸዋል፡፡ በጀትን አስመልክቶ ያለው የመጨረሻው ጉዳይ የህግም ትንተና የሚያስፈልገው ቢሆንም፣ የትግራይ ክልል ህገ መንግስቱን በሚጻረር መልኩ በራሱ ውሳኔ ምርጫ ማካሄዱን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጀት መከልከሉ ይታወሳል። ያ ክልከላ ስለመነሳቱ የተባለ ነገር የለም።

ከዚህ ውጭ ግን አሁን አስጊ የሆነው ትህነግ በወልቃይት መስመር ውጊያ ለመክፈት ሰፊ ቁጥር ያለው ሚሊሻ በክተት መልክ ማንቀሳቀሱ ነው። ሰሞኑንን በወልቃይት በኩልና በራይ የማጥቃት ሙከራ ማድረጉና መክሸፉ ቢሰማም በሚመከታቸው አካላት ማረጋገጫ አልተሰጠበትም። ሆኖም ግን “አፍሪካ ሕብረት መንግስትን አላወገዘም” የሚለውን ሃረግ ለማሰማት ሲል አምነስቲ፣ ለትህነግ ቅርብ የሆኑ የእንግሊዝን ሚዲያዎች፣ የአሜሪካ ደጋፊ ሚዲያዎችና ባለስልጣናት ትህነግ ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ወደ አማራ ክልል ግንባሮች ማዝመቱን አረጋግጠዋል።

የህዳሴው ግድብ ሙሌት ይፋ በሆነበት ቅጽበት የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አይሁዳዊው አንቶኒ ብሊንከን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልክ ደውለው የኤርትራና የአማራ ሃይሎች እንዲወጡ ማዘዛቸውን አስታውቀዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ለተፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጭካኔ የተሞላባቸው አድራጎቶች የሚጠየቁትን ወደ ህግ የመውሰዱ ተግባር እንዲጀመር ማሳሰባቸው አመልክተዋል። አሜሪካንን ጨምሮ የትህነግ ሃይል ወደ አማራ ክልል ድንበሮች ለውጊያ እያመራ ባለበት ሰዓት ይህን ማለታቸው በሌሎች ወገን እሳት እይፈጠረ ነው።

የአማራ ክልል መሪ አቶ አገኘሁ ” በርበሬና ገጀራ ይዞ አማራ ክልል ለመጨፍጨፍ መሞከር አይቻልም። ከተሞከረ የዛኔ የከፋው ይሆናል” ሲሉ ክልላቸው ማናኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኑንን አመልክተዋል። በሌላ በኩል ከትግራይ ክልል ” ደጀን ወዳለበት” ማፈግፈጉ የተገለጸለት የአገር መከላከያ ሰራዊት ” ቁስላችን ተጠገነ፤ በወገን ኮራን” ሲል ዝግጅቱን እያስታወቀ ይገኛል።

የትህነግ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ” እምቢ ካሉ በጠብ መንጃ” እናናግራቸዋለን ሲሉ ለጀርመን ድምጽ ተናግረዋል። በዚህ ሃይለኝነታቸውን በገለጹበት አንደበታቸው በጀት እንዲለቀቅ ጠይቀዋል። በይፋ ባይነገርም ለጦርነት እየተዘጋጀ ያለ ሃይል እንዴት በጀት ይለቀቅለታል? የሚለው ጉዳይ በመንግስት በኩል ለውጭ ዲፕሎማቶች የሚቀርብ ሆኗል።

አንቶኒ ብሊንከን ” ትግራይን ለቆ ይውጣ” ያሉት የአማራ ሃይልን ሲሆን ከማይካድራ ጭፍጨፋ በሁዋላ በስጋት ያለውን ህዝብ ” ዳግም ትህነግ ያስተዳድርህ” ሲሉ ማወጃቸው አጀንዳቸው የተለየ እንደሆነ አመላካች ስለመሆኑ በተደጋጋሚ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

ትህነግ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት የፈጸሙ መኮንኖች እንዲፈቱ መጠየቁና፣ አሜሪካ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የያዘችው አቋምና አሜሪካ ከጀርባ ሆና የተዘጋጀው አዲስ የሽግግር መንግስት አዋጅ ምንም እንኳን ኦነግና ኦፌኮ አዘጋጁት ቢባልም፣ ሁሉም የተያያዘላቸው ክፍሎች ከወዲሁ ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። እንደ እነዚህ ሃይሎች ግምት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በሃይል የማንሳት ሙከራ ሊደረግ ይችላል።

በሰሞኑ የፓርላማ ንግግራቸው ” ውረዱ የሚሉን ሃይሎች አሉ” ማለታቸው፣ ጉዳዩ የግለሰብ መውረድና አለመውረድ ሳይሆን በኢትዮጵያ ተላላኪ መንግስት የመትከል እቅድ መሆኑን መጠቆማቸውን የሚያነሱ ” አሜሪካ ጠ/ሚ አብይን የፈራችው ምን አልባትም በአፍሪካ ፓን አፍሪካኒዝም ዳግም ሊያቀጣጥሉ ይችላሉ” ከሚል ስጋት የተነሳ እንደሆነ ይገልጻሉ።

“ምርጫ አይካሄድም፣ የኔቶ ሃይል ትግራይ ይገባል፤ የሽግግር መንግስት ይቋቋማል” ሲሉ የትህነግ አውራ ሚዲያዎችና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም እነ 360፣ ርዕዮት፣ መረጃና አባይ ሚዲያ ይህንኑ ሃሳብ ሲደጋግሙ ነበር። በደርግ ጊዜ የተካሄደውንና ኢትዮጵያ አሉኝ የምትላቸውን ጀነራሎች እንድታጣ የተደረገችበትን ሆን ተብሎ እንዲከሽፍ ተደርጎ የተሰራውን መፈንቅለ መንግስት የመሩት ሻለቃ ዳዊት ( ራሳቸው ናቸው ሱዳን ድረስ በሄድ መፈንቅለ መንግስቱን እከታተል ነበር” ያሉት ሁሉም ይህን አሳብ በተደጋጋሚ ሲያነሱ ይሰማ ነበር።

ሁሉም ወገኖች ዛሬ ትህነግ ስለሚያዘጋጀው ጦርና ክተት፣ የአማራ ክልልም ጥቃቱን ለመመከት የሚያደርገው ዝግጅት ወደ እልቂት እንዳያመራ ውሎ አድሮ ምን እንደሚሉ ባይታወቅም በርካቶች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

ስጋታቸውን እየገለጹ የሽግግር መንግስት የሚሉ ወገኖች ከ100 በላይ ፓርቲ ሰብስበው ለመሸጋገር መስማማት ቢችሉ እንኳን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ካረደ ሃይል ጋር ማበራቸው በዜጎች ዘንድ የተወደደ አይመስልም። ትህነግ ግን በዚህ ግርግር ተመልሶ ደህንነቱንና መከላከያውን ለመያዝ እንዲያስችለው በልዩ ድጋፍ እየሰራ ነው። ድጋፍ የምታደርገለትም በግንባር ቀደምትነት አሜሪካ ናት። የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ሙሌት አሁን ስለሚጠናቀቅ ፖለቲካውን የሚቀይረው ይሆን?

ጀነራል ጻድቃን ” ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልጋል” ሲሉ ከማይታወቅ ቦታ ሆነው ለሮይተርስ በሳተላይት ስልክ አስታውቀዋል። ፖለቲካዊ መፍትሄው ከቅድመ ሁኔታው በዘለለ ምን እንደሆነ በደን ብ አልተብራራም። ቀና አሳቢዎች የኢትዮጵያ ጉዳይ በድርድር እንደሚፈታ ያምናሉ። ችግሩ ግን “ፍትህስ” የሚለው ነው። የአገር መከላከያ ሰራዊትን ያረዱ፣ ጡት የቆረጡ፣ የከዱ፣ የጨፈለቁ … ሁሉም እንዲሆን ያዘዙ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ መሪ ሆነው እንደገና የሚመጡበትና የሚፏልሉበት ዘመን እንዲመጣ ልብ ያላቸው አይፈቅዱም ። እርቅ መልካም ቢሆንም እንዲህ ያለ ወንጀል ይድበስበስ ማለት ከባድ እንደሆነ ግራ በመጋባት የሚናገሩ ብዙ ናቸው። ለዚህ ይመስላል “ትግራይ ትሂድ” የሚሉ እየበዙ የመጡት!!


Exit mobile version