“ፓርቲዎቹ ” ይላል ኔድ ፕሪስ ሲጀመር። መንግስትንና “አሸባሪ” ተብሎ የተሰየመውን ትህነግን ማታቸው ነው። ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ፣ በአፋጣኝ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙና ሁሉን አቀፍ ወደሆነ የፖለቲካ ንግግር እንዲያደርጉ ያሳስባል። ሁለቱም የንግግሩን ዓላማ የሚያስት ምልልስ እንዲቆጠቡ ያሳባል።

ላለፉት 50 አመታት በትህነግ አማካይነት መሰቃየታቸውን፣ በረሃ እያለ፣ መንግስት ሆኖ፣ ከመንግስትነት ከተወገደ በሁውላ ሽብርን በየክልሉ እየፈለፈለና የልዩነት ፖለቲካን እያዘራ ሰላም የነሳው ትህንግ ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ እንዲፋቅ ዘመቻ ክተት መታወጁ አይዘነጋም።

በሚሊዮኖች ከዳር እስከዳር ንቅናቄ ፈጥረው የአገር መከላከያን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበውና፣ ሌሎችም በወዶ ዘማችነትና በክተት ወደ ግዳጅ እያመሩ ባሉበት ወቅት አሜሪካ ይህን አስገዳጅ መግለጫ ማውጣቷ አስገራሚ ሆኗል።

በቲውተር መልዕክቱ ስር ” አፋራና አማራ ክልል ሲወጋ የት ነበራችሁ?” ከሚለው ምጸት ጀምሮ አሜሪካኖችን ” አሁን ትህነግ ዙሪያው ተከቦ መደቆስ ሲጀምር ተኩስ አቁም የምትሉ … በሚል ክፉኛ ዘለፋ ተገጥግጧል።

ከትናንት በስቲያ ጌታቸው ረዳ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንን አስታውቆ፣ ትናንት ደግሞ ትህነግ ከቀድሞው ስምንት ቅድመ ሁኔታዎች ተቀንሶ በስድት ቅድመ ሁኔታዎች የተጀበ የሰላማዊ የንግግር መግለጫ አሰራጭቶ ነበር።

በጀት፣ አገልግሎት፣ ነጻ ትራንስፖርት፣ የመሳሰሉት ባስቸኳይ እንዲፈቀዱለት ትህነግ መጠየቁን ተከትሎ ” አንድ በሽብርተኛ ቡድን የምትወጋ አገር ለሚወጋት ድርጅት እንዴት በጀትና አገልግሎት ታቀርባለች?” የሚል የመርህ ጥያቄ ለአቶ ጌታቸው ቀርቦ ነበር።

አዲስ አበባ ለመግባት መንገድ ሲያማርጡ የነበሩት ትህነጎች በምን ዓይነት ተዓምር በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ የሰላማዊ ድርድር ሃሳብ ለማቀንቀን እንደተነሱ በግልጽ ባይነገርም፣ በጅቡቲ መስመር መንገድ ዘግቶና፣ በወልደያ በኩል እስከ ደሴ በመዝለቅ የመደራደሪያ ሃይላቸውን ለመጨመር ያደረጉት ጥረት በኪሳራ ስለከሸፈ እንደሆነ ግምት አለ።

በተለይም በአፋር ግንባር ሶስት ክፍለጦር የተደመሰሰበት ትህነግ፣ የኪሳራው መጠን በመከላከያና በአፋር ልዩ ሃይል ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ በማይጸብሪ የሱዳንን ኮሪዶር ለማስከፈት በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ እጅግ ሰፊ ዋጋ አስከፍሎት ባለመሳካቱ እርቅን አማራጩ ለማድረግ እንዲገደድ እንዳደረገው ዜናውን ተከትሎ መረጃ እየወጣ ነው።

አቃቤ ህግ አሁን በህይወት ባሉት አመራሮች ላይ ሰፊ መረጃ አዘጋጅቶ ክስ ከመጀመሩና የክስ ሂደቱን እያጣደፈ ባለበት ውቅት አሜሪካ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቋ “ድርድር እንዴት” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።ትህነግ የማጥቃት ሂደት ላይ በነበረበት ወቅት ማርቲን ፕላውት የሚባለው የትህነግ ተከፋይ የህዝብ ግንኙነት፣ ዶ/ር ደብረጽዮንን እንደነገሩት ተቅሶ “ትህነግ የጅቡቲን መስመር ተቆጥጥሮ እርዳታውን በቀጥታ ወደ ጅቡቲ ያስገባል” በሚልበት ወቅትና እነ ጌታቸው ወደ ደብረብረሃን፣ አዲስ አበባ፣ ወልቃይት ጎንደር … አራት ኪሎ እያሉ መነገድ ሲያማርጡ አሜሪካ ጸጥ ብላ እንደነበር ይታወሳል። ከሁሉም በላይ ዓለም በሚከለክለው ሕጻናትን በጦርነት የመማገድ ወንጀል ትህነግ በሚታክት ማስረጃ ሲከሰስ አሁንም አሜሪካ ተለጉማ ነበር።

የአሜሪካንን ጥሪ አስመልክቶ ከትህነግ በኩል ይቃወማሉ የሚል ግምት ባይኖርም ይህ እስከተሳፈ ድረስ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

ይህ መግለጫ ከመውታቱ በፊት የ ሳማታን ፓወር መንግስት ለማሰገደድና ለመጫን በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ በይፋ ተገልጾ ነበር። ሴትየዋ ጥሩ የሚባሉ የትህነግ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ናቸው።


Donate Button with Credit Cards
 • በ”ገዳዩ” የትህነግ የትምህርት ፖሊሲ “ትውልድ ላሽቋል”፤ ብርሃኑ ነጋ ታዩ
  በጦርነት እንዳይሆን ሆኖ ከተቀጠቀጠ በሁዋላ ትዕቢቱን በውርደትና ተዘርዝሮ በማይጠቃለል ኪሳራ ዘግቶ የፍርድ ቀኑንን የሚጠብቀው ትህነግ፣ ዛሬ በድጋሚ ድል መደረጉ ይፋ ሆኗል። “ኢትዮጵያ ትህነግን በገሃድ ድል አደረች። ልጆቿንም ከመንጋጋው ነጠቀች” ሲሉ የገለጹ ” ለምን ድንጋይ ወርዋሪና በመንጋ የሚነዳ ትውልድ እንድተፈጠረ አሁን ገባን” ሲሉም ተደምጠዋል። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ውጤት ይፋContinue Reading
 • “የወደቁት ተማሪዎቻችን  ብቻ ሳይሆኑ የወደቅነው እንደሃገር ነው”
  ከ50 በመቶ በታች ያመጣ ማንኛውም ተማሪ ዩንቨርስቲ አይገባም ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ በቀጣይ በቀረበው የመፍትሄ አቅጣጫ የተዳከውሙባቸውን ትምህርቶች በዩንቨርስቲ ዳግም እንዲማሩ ተደርጎ በአመቱ መጨረሻ እንዲፈተኑ በማድርረግ ያለፉት የዩንቨርስቲ ስርዓቱን እንዲቀላቀሉም ይደረጋልም ብለዋል ። ሚኒስትሩ ጨምረው የወደቁት ተማሪዎቻችን  ብቻ ሳይሆኑ የወደቅነው እንደሃገር ነው ያሉ ሲሆን ተማሪዎች በሚገባው ስነ ምግባር ትምህርታቸውን አለመከታተላቸው Continue Reading
 • ዓለም ባንክ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረ
  የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ745 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ745 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ዑስማን ዳዮኔ ፈርመዋል። በድጋፍ የተገኘው ገንዘብም ለጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ለጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ተግባር የሚውልContinue Reading
 • “በትግራይ ክልል ከኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ውጭ በግዳጅ ላይ ያለ ሌላ የፀጥታ ሀይል የለም”
  በትግራይ ክልል ከኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ውጭ በግዳጅ ላይ ያለ ሌላ የፀጥታ ሀይል የለም፦ ሜጄር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ለተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ፤ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ፤ ከቀይ መስቀልና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለተውጣጡ አመራሮች በሰላም ስምምነቱ ትግበራ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ማብራሪያውን የሰጡት የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊContinue Reading
 • History Will Always Remember Positive Roles of Ethiopian Diaspora
  DPM and FM Demeke Mekonnen: History Will Always Remember Positive Roles of Ethiopian Diaspora The Government of Ethiopia recognized 52 Ethiopian diaspora associations from 25 countries that actively support their homeland in times of need. According to H.E. President Sahle-Work Zewde, the recognition is for all Ethiopians in the diasporaContinue Reading

Leave a Reply