Site icon ETHIO12.COM

ከሁለት ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች ግድያ ሸሽተው ኤርትራ ጥገኝነት ጠየቁ

ከሁለት ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች ወደ ኤርትራ በማቅናት ጥገኝነት መጠየቃቸው ተነገረ። የኤርትሪያን ፕረስ እንደዘገበው እስከ ዛሬ ድረስ የተመዘገቡ ከሁለት ሺህ በላይ ስደተኞችን ኤርትራ ተቀብላለች።

ዜናው ” አሸባሪው ትህነግ ” ሲል የጠራውን የትግራይ አስተዳደር በመፍራት የተሰደዱት የትግራይ ተወላጆች የኤርትራን ድንበር አቋርጠው ከገቡ በሁዋላ ሰብአዊ ድጋፍና መጠለያ እንደተሰታቸው አመልክቷል።

ንጹሃን ዜጎችን “የጊዚያዊ አስተዳደሩን ደግፋችኋል” በሚል የአገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ ከወጣ በሁዋላ ትህነግ መግደሉን ዜናው አስታውቋል። ባለፉት ቀናት ይኸው ሚዲያ በርካታ የኤርትራ ዜጎች በስደት ካምፕ ውስጥ መገደላቸውን መዘገቡ አይዘነጋም። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትርም በገሃድ ይህንኑ ዜና ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አምናስቲ ስጋቱን የገለጸ ሲሆን ቢቢሲ አፍሪካ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤርትራ ዜጎች በስደተና ካምፕ ውስጥ መገደላቸው የዓለሙን የስደተኞች ድርጅት በመጠቀስ ይፋ አድርጓል። የቢቢሲ እንግሊዘኛ ዜናዎችን ወደ አማርኛ እየመለስ የሚያቀርበው ቢቢሲ አማርኛ ግን ዝምታን መርጧል።

ቪኦኤ፣ ጀርመን ራዲዮ፣ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች፣ እርዳታ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸው ትግራይ የከተሙና በየደቂቃው ሪፖርት ሲያደርጉ የነበሩ ድርጅቶች፣ በጥቅሉ የኤርትራዊያንን መጭፍጨፍና በተለያዩ አውራጃዎች “ከሃጂዎች” በሚል እየተገደሉ ስላሉ የትግራይ ተወላጆችና የራያ አማራዎች ዝምታ መመረጣቸው አስገራሚ ሆኗል።

በራያ፣ እንደርታና መቀለ ብቻ በርካታ ንጹሃን በግፍ መገደላቸው ስምና አድራሻ እየተጠቀሰ ይፋ ቢሆንም መንግስትን በትንሹም በጥቂቱም ሲወቅሱ የነበሩ ሚዲያዎች፣ አገራትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ዝምታ መምረጣቸው ጉዳዩን እንቆቅልሽ አድርጎታል። ለትህነግ በዚህ ደረጃ ልብና ቀልባቸውን የሰጡበት ምክንያት ለበርካቶች ሊገባ ያልቻለ እንቆቅልሽም ነው።

እስካሁን ትህነግ ይህን አስመልክቶ የተየቀው ስለመኖሩ ማስረጃ የለም። እሱም ያላው ነገር አልተሰማም


Exit mobile version