Site icon ETHIO12.COM

የጁንታዉ የተበላሸ ሂሳብ!

አንድ ወቅት ግራዝማች ግሪሳ የመደመርን ካልኩሌተር እንደሰራ አዉስቷል! በኋላ ግን ሂሳቡ በድንገት ተበላሽቶበታል! ካልኩሌተሩ በአማርኛ የኦሮሞን የበላይነት እያሰፈነ በኦሮምኛ ደግሞ ኦሮሞን የሚያጠፋ ሆኖ ተገኝቷል! በመጨረሻም ስሌቱ ግራዝማቹንና ግብረአበሮቹን ቀንሶ አርፏል! ይህ አንድ የአፋን ኦሮሞ ምሳሌን አስታውሶኛል። ምሳሌዉ “ሳይጠግቡ አይዘሉም፥ ሳይዘሉ አይሰበሩም” ይላል! የተበላሸ ሂሳብ ይጎዳል!

የጁንታዉ ካልኩሌተር ደግሞ ከግራዝማቹም የበለጠ ብትንትኑ ወጥቷል! ጁንታዉ ሲፈጠር ጀምሮ አሸባሪና ሴረኛ ኖሯል! በኢትዮጵያ ላይ ይቅር ሊባል የማይችል እጅግ አሰቃቂ ወንጀል እየፈፀመ ለ27 ዓመታት ነግሷል! በህዝብ ትግል ከወደቀ በኋላ ደግሞ የለዉጡ መንግስት የሰጠዉን ፈፅሞ የማይገኝ የይቅርታ እድል አምክኖ የፉከራ ከበሮ መቷል! ለሠላም ተብሎ የተደረገዉ ሁሉ ፍርሃት መስሎት የኢትዮጵያን መከላከያ ከጀርባ በመጥቃት የተኛዉን አንበሳ ቀስቅሷል! አንበሳዉ ጁንታዉን ከበታተነ በኋላ በቅንነት የትግራይን ህዝብ ሲረዳ ቆይቷል! ህዝቡ ግን ለተበታተነዉ ጁንታ ወግኖ በጀበና ቡና ሳይቀር መረዝ እየጨመረ እየሞቱ የሚረዱትን የመከላከያ አባላት ገድሏል! ከህዝብ ጋር መጋጨት አስፈላጊ ባለመሆኑ በስሜት ሳይሆን በስሌት ትግራይ ተለቆ የጫዋታዉ ሜዳ ተቀይሯል!

ትግራይ ሲለቀቅ ፈንጠዝያዉ ጧፏል! ጁንታዉ “ኢትዮጵያን አሸንፈያለሁ” ብሎ ሲፎክር አባላቱና ደጋፊዎቹ በያሉበት “ኩራት” ብሏል! በመቀሌ ደግሞ የኢትዮጵያውያንን ሞራል ለመግደል የምርኮ ተዉኔት ተሰርቷል! በሸገርና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ የጁንታዉ ርዝራዦችም በጌታቸዉ ዉሸት መርቅነዉ ራቁታቸዉን እየጨፈሩ ውስኪ ተራጭቷል! ጁንታዉ በሁለት ቀናት አራት ኪሎን የሚቆጣጠር መስሏቸዉ ሌሎችን እየተሳደቡ ለመደብደብ ሞክሯል! ግን የተወራዉና የተፈጠረዉ ለየቅል ሆኗል! አሁን ሁሉም ነገር ረግቧል! የጁንታዉ ርዝራዦች ጩኸት ለስለስ እያለ መጥቷል! ትግራይ የተለቀቀበት ትክክለኛዉ ስሌት ሲታወቅ ደግሞ የጁንታዉ ሰፈር በከባድ የፀፀት ማዕበል ይመታል! በርግጥ የጁንታዉ ጌቶች ሁኔታዉን በከፊል ተረድተዉ ደንግጧል! ተኩስ ማቆሙ በስምምነት እንዲሆንም መወትወት ይዟል! ከጁንታዉ ጋር የመስማማት ጉዳይ ግን ጀግናዉ የኢትዮጵያ መከታ በክህደት ከመጠቃቱ በፊት አልፏል! ጊዜዉ ሄዶ ሄዶ አሁን የጥሞና ሆኗል! ጥሞናዉ ሲያልቅ የከበሮና የፉከራ ድምፅ ሳይሆን ለሆሳስ የልመና ድምፅ ይጠበቃል! ያኔ ሂሳቡ ተመርምሮ ፋይል ይዘጋል!

Via Taye dendea Aredo

Exit mobile version