Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው የትህነግ በአማራ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመቀልበስ ዝግጁ መሆናቸውን የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማኅበር አባላት ገለጹ

አሸባሪው ትህነግ የአማራን ሕዝብ ቁጥር አንድ ጠላቱ አድርጎ የሽብር ጥቃቱን በግልጽ ቢጀምርም አቅሙ ከፈቀደለት ኢትዮጵያን ከማፈራረስ ወደኋላ ስለማይል ኢትዮጵያዊያን ጉዳዩን ነገም ለእኔ ብለው ምላሽ መሰጠት እንዳለባቸዉም ነው የገለጹት፡፡

የቀድሞ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ማኅበር ፕሬዚዳንት አስር አለቃ ደጀኔ ሽዋረጋ እና የማኅበሩ አባል አምሳ አለቃ ቸኮል ዓለሙ ከአሚኮ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

የትህነግ ማፍያ ቡድን ገና ሲጠነሰስ ጀምሮ ጸረ አማራ እንደነበር ይታወቃል፤ ምክንያቱ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን እህት ወንድሞቹ ጋር ተከባብሮ የሚኖር በመሆኑ ትህነግ ሀገር የማፍረስ ተልኮን ያከሽፍብኛል ብሎ በማሰቡ ነው ብለዋል፡፡

አሸባው ትህነግ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በአማራ ሕዝብ ላይ ለከት የሌለዉ የጭካኔ ደርጊት ፈጽሟል፤ ተበዳይ ዝም ሲል በዳዩ ይጮሃል እንዲሉ ሒሳብ ማወራረድ ያለበት የአማራ ህዝብ ነዉ እንጂ ትህነግ አይደለም ነው ያሉት፡፡

ተስፋ የቆረጠ የማይሞክረዉ ነገር እንደሌለ የሚናገሩት የቀድሞ ሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላቱ ምንም እንኳ ትህነግ የአማራን ሕዝብ ቁጥር አንድ ጠላቱ አድርጎ የሽብር ጥቃቱን በግልጽ ቢጀምርም አቅሙ ከፈቀደለት ኢትዮጵያን ማፈራረስ ዓላማው ነው ብለዋል፡፡ ይህን በመገንዘብ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሊታገሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የቀድሞ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ድሮም የኖርነዉ ለሀገር ነው፤ አሁንም ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመቀልበስ ብቃቱም ዝግጅቱም አለን ነው ያሉት፡፡

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አስር አለቃ ደጀኔ የቀድሞ ሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ለኢትዮጵያ ህይወታችን ሰጥተን ሉዓላዊነቷን አስከበረን ኖረናል፤ አሁን በትህነግ በኩል የተቃጣዉን የጥፋት ድርጊት ለማክሸፍ መዘጋጀት እንዳለባቸዉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ. (አሚኮ)

Exit mobile version