Site icon ETHIO12.COM

የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲፈጥር አብን ለአማራ ህዝብ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፦ መላው የአማራ ህዝብ አሁን እያጋጠመው ያለው አደጋ የታሪክና የማህበራዊ ክብር እንዲሁም የማንነት ጉዳይ በመሆኑ አጠቃላይ ጥቃቱን ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።

አብን ትናንት ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ፣መላው የአማራ ህዝብ አሁን እያጋጠመው ያለው አደጋ የታሪክና የማህበራዊ ክብር እንዲሁም የማንነት ጉዳይ መሆኑን በመረዳት አጠቃላይ ጥቃቱን ለመመከት አስቸኳይ ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

የአማራ ወጣቶች በየአካባቢያችሁ በመምከርና በመደራጀት፣ ራሳችሁን በማስታጠቅ ለሁለንተናዊ ዘመቻ ራሳችሁን እንድታዘጋጁ፣በሁሉም አካባቢዎች ያላችሁ የአማራ ፋኖዎች በአሁኑ ሰዓት ህዝባችን ያጋጠመውን የህልውና ትግል ለመቀልበስ በግንባር ለመንቀሳቀስ ፈጣን ዝግጅት እንድታደርጉ ብሏል።

መላው የአማራ ህዝብ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና በተለይም በመካከላችን ሆነው ሴራና ጥቃት የሚያቀናብሩ፣ በሰርጎ ገብነት መረጃ ለጠላት የሚያቀብሉ አካላትን በንቃት በመከታተል የማክሸፍና የመቆጣጠር ሥራ እንዲያከናውን ጥሪ አቅርቧል።

በተለያየ የአመራር ጥፋትና ጥሰት ያላግባብ ተገፍታችሁ ከፀጥታና ከወታደራዊ አመራ ርነታችሁና ሙያችሁ ውጭ የተደረጋችሁ የአ ማራ ልጆች በሙሉ ህዝባችሁን ለመታደግ የሚደረገውን ታሪካዊ እንቅስቃሴ ለመቀላቀል እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳስቧል።

አብን በመግለጫው ፣ሂደቶችን በአስተ ውሎት እየተከታተልንና መረጃ እየሰበሰብን በመቆየት ነገሮች ይሻሻላሉ በማለት ብንጠብቅም ችግሮቹ በፍጥነት ሲወሳሰቡ በማየታችን ለህዝባችን ህልውና ይህንን ጥሪ ለማድረግ ተገደናል ብሏል።

መላው የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የህል ውና አደጋ ለመቀልበስ ለሚደረገው ሁለንተናዊ ዘመቻ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በደጀንነት ርብርብ እንዲደረግ የጠየቀው አብን ፣ የህልውና ዘመቻውን በሙሉ እንዲቀላቀሉ እና እንዲያስተባብሩ ለሁሉም የንቅናቄው አባላትና አመራሮች ትዕዛዝ ማስተላለፉንም አስታውቋል።

በጋዜጣው ሪፖርተር

አዲስ ዘመን ሐምሌ 7/2013

Exit mobile version