Site icon ETHIO12.COM

መንግስት ነጭ ወያኔዎችን ሊያባርር፣ የተኩስ አቁም ውሳኔውን ሊቀይርና የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ጫፍ መድረሱን ይፋ አደረገ

ይህ ጊዜ አደገኛ ጊዜ ነው። ምንም መደባበቅ የለም ይህ ጊዜ አስጨናቂ ነው። ይህ ጊዜ ባንዳ ሚዲያዎች፣ አገራችንን ለማፍረስ በተቋቋሙ ሚዲያዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ሎሌዎች፣ ባንዳ ተቃዋሚዎች፣ ባንዳ አክቲቪስት ነን ባዮች በአገር ክህደት የቆሙበት ጊዜ ነው። ይህ ጊዜ ኢትዮጵያን ለመበተን የውስጥ ባንዶችን በመጠቀም፣ የዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች፣ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ዋና ዋና የሚባሉት የዓለም አገራት ተባብረው መንግስትን እያካለቡ ነው።

“አንድነታችንን ጠብቀን፣ እንደ አገር እንዳንቆም ሸብረክ ሊያደርጉን እየተረባረቡን ነው” ብሏል መንግስት። ችግሩ ብዙ ወቃሹ ግዙፍ ሆኖ መቀጠል አይቻልም ብሏል። እጅግ ስሜትን በሚነካና ሞራልን በሚፈታተን ስሜት መንግስት ይፋ ያደረገው ወቅታዊ ሁኔታ ለሰላም ሲባል የተዘረጋውን እጅ የሚያሳጥፍ፣ አገር ስትፈርስ ዝም የማይባልበት በመሆኑ ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ሊወሰድ እንደሚችል አመልክቷል።

የሰፈርና የግል ጉዳይን በማቆም በመተሳሰብ የተቃጣብንን ይህን አደገኛ አዝማሚያ ለማለፍ ህብረት እንደሚያስፈልግ መንግስት አሳስቧል። ሕጻናትን ለጦርነት እያዘጋጀና እየማገድ ያለውን አሸባሪ የሚቆታ፣ የሚያወግዝ፣ ተው የሚል አንድም አካል በሌለበት ሁኔታ የሰላም እጅ እስከመጨረሻ ተዘርግቶ አይቆይም። ትህነግ በአፋርና በጎንደር ውጊያውን ለማስፋት እየሰራ ነው። በዚህ መልኩ መቀጠል አይቻልምና ዛሬ መንግስት ይፋ እንዳደረገው ከአንዳንዶቹ ጋር መስራት የማይችልበት ደረጃ ተደርሷል።

ይህ ቪዲዮ እጅግ ወሳኝ መልዕክት አለውና ሌሎች የዩቲዩብ ነጋዴዎች ” ሰበር” ምናምን እያሉ ስይነካክኩት እንዳለ እንደወረደ በምትችሉት መድረክ በሙሉ ሺር ማድረግ ይኖርብናል።

Exit mobile version