Site icon ETHIO12.COM

የሶማሊ ክልል ልዩ ሃይል ወደ ግዳጅ ቀጠና እንደሚያቀኑ ሙስጣፌ አስታወቁ፣” አሸባሪን ከመታገል ውጭ አማራጭ የለም”

ሰሞኑንን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ” አሸባሪ” ድርጅት ተብሎ መፈረጁን በማይቀበሉና ለጊዜው ወዳጅ በሆኑት አገራት በሚተዳደሩ የአማርኛ ሚዲያዎች ” የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ብሄር ብሄረሰቦች” እያለ ተማጽኖ ቢያቀርብም ክልሎች በተቃራኒው ” አሸባሪን ከማጥፋት ሌላ አማራጭ የለም” በሚል ግብረ ምላሽ እየሰጡ ነው።

ኦሮሚያ በክልሉና በመላው ኢትዮጵያ ትህነግ የተሰኘው አሸባሪ ድርጅት የፈጸመውን ወንጀል ዘርዝሮ አጥብቆ እንደሚታገለው በይፋ በመግለጫ አመልክቷል። በተግባርም ሃይል ልኳል። ሲዳማ ” አሸባሪን እንታገላለን” በሚል አቋም መያዙን አስታውሶ የልዩ ሃይል አባላቶቹን ወደ ግዳጅ ቀጣና አሰማርቷል።

ቢኒሻንጉልና ጋምቤላ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በክልላቸው ሲፈጸም የነበረውን አመልክተው ” የትህነግን አሸባሪ ቡድን እንፋለማለን” ሲሉ የሶማሌ ክልል መሪ አቶ ሙስጠፌ በበኩላቸው “ሀገር ለማፍረስ የመጣን ኃይል በሕብረት ከመታገል ውጪ ምንም አማራጭ የለም” ሲሉ የመጨረሻውን የክልሉን አቋም አስታውቀዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ሀገር ለማፍረስ የመጣን ኃይል በጋራ ከመታገል ውጪ ምንም አማራጭ እንደሌለ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የገለጹት በይፋ ወቅቱን አስመልክተው ሲናገሩ ነው። ቀደም ሲል አሸባሪው ቡድን ” የማወራርደው ሂሳብ አለ” በሚል አማራ ላይ ሲፎክር ” እኛም እንጠብቃለን። ናና ሶማሌ ክልልም አወራርድ” ማለታቸው ይታወሳል።

የሽብር ቡድኑን ጥቃት ለማምከን በሚደረገው እንቅስቃሴ የሱማሌ ክልል የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የጸጥታ ኃይል ወደ ቦታው ለማሰመራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሙስጣፊ አረጋግጠዋል።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ እንደገለጹት፤ አሸባሪው ትህነግ በሀገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተጀመረው የሕግ የማስከበር ዘመቻ የተለያዩ ምዕራፎችን አልፏል፡፡ በዚህ ሂደት የአሸባሪው የትህነግ ቡድን ከመጀመሪያው ጀምሮ የሚሰጣቸው ምክንያቶች ይለዋወጡ፣ ሐሳቦቹ ይቀያየሩ እንጂ የሚከተለው ሀገር የማፍረስ አጀንዳ በመሆኑ ሀገር ለማፍረስ የመጣን ኃይል በሕብረት ከመታገል ውጪ ምንም አማራጭ የለም ነው ያሉት፡፡

የሽብር ቡድኑ የሚከተለው አጀንዳ እሱ ከሚያነሳቸው ሰብዓዊ መብትና ራስን በራስ ከማስተዳደር አጀንዳዎች ጋር በፍጹም የሚገናኝ አይደለም ያሉት አቶ ሙስጠፌ ፤ እነዚህን አጀንዳዎች የሚያነሳቸው ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማወናበድ እንጂ የእሱ ዓላማ ሀገርን ማፍረስ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ የተናጠል የተኩስ አቁሙ ውሳኔ ለትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ ድጋፍና ለአርሶ አደሮች እርሻ ሥራ ሲባል በመንግሥት የተደረገ ውሳኔ መሆኑን እያወቀ ውሳኔውን እንደ ፍርሐት በመቁጠር ተደፋፍሮ ክልሎችን ለማጥቃትና ሀገሪቱን ለማፍረስ እየሞከረ ነው ብለዋል፡፡

“የሽብር ቡድኑ ለትግራይ ሕዝብ ክብርና ሐዘኔታ ቢኖረው ኖሮ በሌሎች ክልሎች ላይ ዳግመኛ ትንኮሳ ማሄድ የለበትም ነበር” ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በአፋርና በአማራ ክልሎች ትንኮሳ ማካሄዱ አጀንዳው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀሰውን ይህንን ኃይል በሕብረት መታገል እንደሚያስፈልግ ማስገንዘባቸውን የኢፕድ ዘገባ ያመለክታል።

አሸባሪው ትህነግ በሶማሌ ክልል አስገድዶ በቡድን በመድፈር፣ በክልሉን ኦጋዴንን ዘገቶ በመያዝና የውጭ ድርጅቶችም ሆኑ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ ከልክሎ በረሃብ ህዝብ በመጨረስ፣ ሰዎችን ከአውሬ ጋር በማሳደርና በማስበላት፣ በጅምላ ግድያ፣ በጄል ኦጋዴን ልዩ ማሰቃያ ቶርቸርና አሰቃቂ ግድያ በመፈጸሙ ” ድብቁ የኢትዮጵያ ሃፍረቷ በኦጋዴን” በሚል በመጨረሻ ሂውማን ራይትስ ዎች በፊልም ዘገባ ማቅረቡ አይዘነጋም።

ይህ ዶክመንታሪ ያማል
Exit mobile version