Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሀት በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል

የአሸባሪውን ትህነግ የመጨረሻ እስትንፋስ ለማቋረጥ ሁሉም በጋራ እንዲቆም የአፋር ክልል መንግሥት ጥሪ አቀረበ፡፡

የአፋር ክልል የሽብር ቡድኑ በአፋር ሕዝብ ላይ ጦርነት መክፈቱን አስታውቋል፡፡ አሸባሪው ትህነግ አድማሱን ወደ አፋር ክልል በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ሕዝብ ላይ ጦርነት መክፈቱን የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

ይህ እኩይ ቡድን በዳር ድንበር አስከባሪው፣ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ጀግናው የአፋር አርብቶ አደር ሕዝብ ላይ በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል የከፈተውን ጦርነት መንግሥት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ይመክታል ብሏል።

ሰላማዊ ክልላችንን ለማተራመስ ሽብርተኛው ትህነግ የለኮሰውን ጦርነት በአጭሩ እንዲገታ ከሕዝቡ አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ የሚጠበቅ እንደሆነ እና አካባቢውንም በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ ሚሊሻ እና አጠቃላይ የጸጥታ ኃይሉ በሕዝብ ላይ የተሠነዘረውን ጥቃት የመከላከል ሥራ በቁርጠኝነት የሚተገብር ይሆናል ብሏል።

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም እንደ አበደ ውሻ እዚያና እዚህ ለመንከስ የእብደት ሥራ እየሠራ ያለውን እኩይ ቡድን በፍጥነት ግብአተ መሬቱ እንዲፈፀም እንደወትሮው ሁሉ እጅ ለእጅ በመያያዝ በጋራ በመታገል እስትንፋሱ እንዲቋረጥ ማድረግ ይጠበቅብናል ብሏል።

ሕዝቡም ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ሽብርተኛው ቡድን በፈንቲ ረሱ ያሎ ወረዳ በኩል የተከፈተውን ጦርነት እንዲመክት ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሕዝቡ በንቃት አካባቢውን በመቃኘት ከአካባቢው የጸጥታ ኃይል ጋር በትብብር እንዲሠራ ጥሪ ቀርቧል።

Exit mobile version