Site icon ETHIO12.COM

«ሀ ሁ ኢትዮጵያ ትቅደም…»ልጅ ግሩም

ኢትዮጵያ ትቅደም
ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት
በከንቱ ፈሰዋል ለብዙ ሺህ አመታት
ይውጡ ማእድናት ላገራችን ጥቅም
ህዝቧም ታጥቆ ይስራ በተቻለው አቅም

ኢትዮጵያ 123 ቢሊዮን ሜትር ኪዬብ የሚገመት የውሃ ኃብት ሲኖራት ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ድርሻ ያላቸው ከባሮ አኮቦ፣ አባይ፣ ተከዜ፣ ኦሞና ጊቤ ወንዞች ናቸው፡፡ አትባራ ወንዝ፣ መረብ ወንዝ እንዲሁም ኦቤል ወንዝ ገባሮች ናቸው፡፡
የተከዜ ወይም ሰቲት ወንዝ የሚቀላቀሉ አነስተኛ ገባር ጅረቶች ውስጥ ዘሪማ፣ አጽባ፣ ዋሪ ወንዝ እና ባላጋስ ወንዝ፣ አንገርብ ወንዝ፣ ሽንፋ ወንዝ ጋሪ ወንዞች ናቸው፡፡
የጥቁር አባይ ወንዝ ገባር ወንዞች አነስተኛ ገባር ጅረቶች ውስጥ ራሃድ ወንዝ፣ ዲንድር ወንዝ፣ በለስ ወንዝ፣ ዳቡስ ወንዝ፣ ዴዴሳ ወንዝ (ገባሪ ሃንገር ወይም አንጋር ወንዝ፣ ገባሪ ዋጃ ወንዝ ) ናቸው፡፡
ጉላ ወንዝ፣ ጉደር ወንዝ፣ ሙገር ወንዝ፣ ጀማ ወንዝ (ገባር ውጭት ወንዝ፣ ገባር ቀጨኔ ወንዝ)፣ ሮቤ ወንዝ (ገባር ደንቢ ወንዝ)፣ ዋላቃ ወንዝ፣ ባሺሎ (ገባር ጨጨሆ ወንዝ) ወደ ጣና ሃይቅ የሚፈስው ትንሹ አባይ፣ መገጭ ወንዝ (ገባር ትንሹ አንገርብ ወንዝ )፣ ርብ ወንዝ፣ ጉማራ ወንዝ ናቸው፡፡ የአዳራ ወንዝ ወደ ደቡብ ሱዳን ድንበርና ወሰን ሰብሮ ቤት ለንቦሳ ይሉታል፡፡ ያቡስ ወንዝና ጋጋ ወንዝ ወይም ደቅ ሶንካ ስት ገባር ወንዞች ናቸው፡፡
ወደ ደቡብ ሱዳን ባሮ ወንዝ፣ (አነስተኛ ገባር ጅረቶች ውስጥ ጅካዎ ወንዝ፣ አሌሮ ወይም አልዌሮ ወንዝ)፣ ለብርብር ወንዝ (ዲፓ ወንዝ ሲገብር) (ኮባራ ወንዝን ያስገብራል) (ኮርሳ ወንዝ ይገብራል)፣ ገባ ወንዝ (ሱር ወንዝ ይገብራል) ፒቡር ወንዝ፣ (ጊሎ ወንዝና አኮቦ ወንዞች) ይገብራሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ወንዞች በስምንት የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ድንበር አቋራጭ ወንዞች ወደ ሜዲትራንያ ባህር ይገባሉ፡፡
ባሮ ወንዝ፣ (ገባር ጅካዎ ወንዝ፣ አሌሮ ወይም አልዌሮ ወንዝ)፣ ለብርብር ወንዝ (ዲፓ ወንዝ ሲገብር) (ኮባራ ወንዝን ያስገብራል) (ኮርሳ ወንዝ ይገብራል)፣ ገባ ወንዝ (ሱር ወንዝ ይገብራል) ፒቡር ወንዝ፣ (ጊሎ ወንዝና አኮቦ ወንዞች) ይገብራሉ፡፡
ወደ ህንድ ውቅያኖስ የሚገቡ፣ ጁባ ወንዝ እና የሸበሌ ወንዝ ታፋሰስ ሸለቆ አንዱ ነው፡፡ ጁባ ወንዝ፣ ገባር ሸበሌ ወንዝ (ገባሩ ፋፈን ወንዝ ሸበሌ የሚደርሰው ውሃ በሞላ ጊዜ ነው፣ ገባሩ ጀረር ወንዝ)፣ ኤረር ወንዝ፣ ራሚስ ወንዝ(ገባር ጋለቲ ወንዝ)፣ዱንጌታ ወንዝ (ገባሩ ጎሎልቻ ወንዝ ) ናቸው፡፡ ገናሌ ዶርያ ወንዝ ገባሮቹ መና ወንዝ፣ ወይብ ወይም ጌስትሮ ወንዝ እንዲሁም ወልመልና ዳዋ ወንዝ ናቸው፡፡
ወደ በርሃው አፋር ሰምጥ ሸለቆ የሚሰምጡ፣ አዋሽ ወንዝ ገባሮቹ ሎጊያ ወንዝ፣ ሚሌ ወንዝ (አላና ጎሊማ ወንዞች ገባሮቹ ናቸው፡፡) እንዲሁም ቦርከና ወንዝ፣ አጣዬ ወንዝ፣ ሃዋዲ፣ ቀቤና ወንዝ፣ ገርማማ ወይም ቀስም ወንዝ፣ ዱርክሃም ወንዝ፣ ከለታ ወንዝ፣ ሞጆ ወንዝ፣ አቃቂ ወንዝ እንዲሁም ደቻቱ ወንዞች ናቸው፡፡
ድንበር አቋራጭ ወንዞች ወደ ሃይቆች ውስጥ የሚቀላቀሉ፣ ዘዋይ ሃይቅ ውስጥ የሚገቡ መቂና ካታር ወንዞች ናቸው፡፡ አባያ ሃይቅ የሚገቡ ደግሞ ቢላቴ ወንዝና ጊዳቦ ወንዞች ናቸው፡፡ ጫሞ ሃይቅ ውስጥ ኩልፎ ወንዝ ይገባል፡፡ ጨው ባህር ሃይቅ ውስጥ ወይጦ ወንዝ ገባሩን ሳጋን ወንዝን አስከትሎ ይገባል፡፡ ቱርካና ሃይቅ ውስጥ የሚቀላቀሉ ትልልቅ ወንዞች ክቢሽ ወንዝና ኦሞ ወንዞች ናቸው፡፡ ኦሞ ወንዝ የሚቀላቀለው ኡስኖ ወንዝ ገባሮቹን ማንጎ ወንዝና ነሪ ወንዞችን ይዞ፣ ሙይ ወንዝ፣ ማንትሳ ወንዝ፣ ዚጂና ወንዝ፣ ዲንቺያ ወንዝ፣ ጎጀብ ወንዝ፣ ጊቤ ወንዝ ገባሮቹን ግልገል ጊቤ ወንዞች ይዞ እንዲሁም ዋቢ ወንዞች በቱርካና ሃይቅ ውስጥ ይገባሉ፡፡
ኢትዮጵያ ድሃ አለመሆኗን ያወቁት ጠላቶቻችን ነጮች እና ተላላኪዎቻቸው ብቻ ናቸው።ግን እነዚህ ሁሉ ወንዞች ኖረውም ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን አልቻለችም፡፡
ከዚህ በኋላ ግን ወንዞቻችንን እና የአባይ ገባሮች እንጠልፋለን፣ እንገድባለን። የውሃ ሃብታችንን ለኤሌትሪክ ኃይል ብቻ ሳይሆን ለመስኖ ልማትነት እንጠቀምበታለን። ተስፋ አለን።

ልጅ ግሩም ( phd)

Exit mobile version