Site icon ETHIO12.COM

”አይጥ ከጉድጓድ ወጣች ብላችሁ ብዙ አትገረሙ” የኤርትራ ኢታማጆር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ

የኤርትራ ጦር ኤታማጆር ሹም ጄኔሬል ፊሊጶስ ወ/ዮሐንስ የወያኔ ሰራዊት ከትግራይ ወደ አማራ እና አፋር ክልል እየመሸጉ ነው ሰለሚለው ነገር አስተያየት ሰጠ።

የወያኔ ጉዞ በወታደራዊ መነፅር ሲታይ አይጥ ከጉድጓዷ በራቀች ቁጥር በድመት የመበላት እድሏ እንደሚጨምረው ከመሆን ውጪ ሌላ ምንም ጠቀሜታ ያለው አደለም ብሎዋል።

ችሎ እንኳ ከትግራይ አልፎ ወደ አማራ እና አፋር መሬት ቢገፋ ተቀጥቅጦ ወደ ነበረበት ጉድጓድ እንኳ መመለስ በማይችልበት ሁኔታ አየር ላይ ይመታል ብሎዋል።

በአንድ በኩል እያሸነፈ እንደሆነ ያወራል በሌላ በኩል ድረሱልኝ አስታርቁኝ እያለ በአለማቀፍ መድረክ ኡኡ ይላል። እያሸነፈ ከሆነ አስታርቁኝ ማለቱን የሶሻል ሚዲያ ዘመቻውን እና ኡኡታውን ምን አመጣው? ለምን ዝም ብሎ አያሸንፍም?? በማለት ጠይቆዋል።

አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በሶሻል ሚዲያ በሚያዩት ነገር እንዳይሸበሩ እመክራለሁ እኛ ኤርትራውን ወያኔን አብጠርጥረን እናውቀዋለን የውሻን ያህል ትኩረት እንደማንሰጠውም እራሱ የሚያውቀው ጉዳይ ነው ብሎዋል። nathnael

Exit mobile version