ETHIO12.COM

ወደ ደብረ ብርሃን፣ ጎንደርና አዲስ አበባ እንደሚያኮበኩብ የገለጸው ትህነግ በርካታ ሰራዊት ተማረከበት፤ ቆቦን ተነጠቀ

አቶ ጌታቸው ረዳ ” ወደ ደብረብርሃን ወይስ ጎንደር” ሲሉ ወዳሻቸው የሽር ሽር ያህል እንደሚያቀኑ ባስታወቁ በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ ቆቦን መነተቃቸው ተሰማ። በአፋር ግንባር ከፈተኛ ቁጥር ያላቸው ምልምሎች መማረካቸው ታወቀ።

ስያተኩሱና ከመኪና ሳይወርዱ የተያዙት የትንገ ሃይሎች

የአሸባሪው ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው እንዳሉት እሳቸው የሚወክሉት ጦር ወደ ፈለገው አቅጣጫ ለመሄድ የሚገድበው አንዳች ሃይል የለም። መደራደር እንደሚፈልጉ የሚነገርላቸው ጄነራል ጻድቃንም ” ወደ አዲስ አበባ ለመገስገስ የምያግድ አንዳችም ነገር የለም” የሚል ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

ዛሬ ረፋዱ ላይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለቱት ትህነግ ቆቦን ከሙሉ ኪሳራ ጋር ተነጥቋል። በአፋር ግንባር ሰፊ ቦታ የሚሸፍን ጦርነት ለመክፈት ሲያጋግዛቸው የነበሩ ምልምል ወታደሮች ከመኪና ሳይወርዱ ተይዘዋል። ከአካባቢው ምስክሮች መረዳት እንደተቻለው የተያዙት ከመኪና ሳይወርዱ በመሆኑ ” ተማረኩ” ሊባል አይችልም።

ከተማረኩት በተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ መደምሰሳቸውን በስፍራው ያሉ ምስክሮች ገልጸዋል። የጅቡቲ ባቡርና የየብስ መንገድ እንደሚቆርጡ ከሳምንት በፊት የተነገረላቸው የትግነግ ተዋጊዎች እስካሁን በአፋር ግንባር ይህ ነው የሚባል ማስመዝገባቸውን አልተቆሙም።

የጦርነት መረጃ ሁሉ እንደማይነገር የሚገልጸው መንግስት የመከላከያ ሃይል ከድካምና ከባይተዋርነት አገግሞ ሰንጋ እየበላ ደጀን መካከል ሆኖ መዋጋት ከጀመረ አንስቶ በትህነግ ላይ ከፈተኛ የሚባል ሰባዊ ቀውስ እያደረሰ ነው።

ለደጋፊዎቻቸው ብርታት ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ድል ዘመቻ የሚያስተጋቡት የትህነግ ደጋፊዎች በተመሳሳይ ” ትግራይ እያለቅች ነው” የሚል የማህበራዊ ዘመቻ ጀምረዋል። በተመሳሳይ ትህነግ አሸባሪ መሆኑንን የሚያበስር ሎጎ ኢትዮጵያን የሚወዱ ዜጎች እያሰራጩ ነው።

ትህነግ ቆቦን መያዙን ሲያስታውቅ ካሰራጨው ፎቶ በተለይ ቆቦን ስለመነጠቁ ለደጋፊዎቹ ያለው ነገር የለም። በግንኙነት መረጃውን ከመስማት ውጪ መንግስት ቆቦ ስለመያዟም ሆነ ስለመለቀቋ ያለው ነገር የለም። አቶ ተሻገር ዛሬ ባሰሙት የክተት ጥሪ ‘ ስለወታደራዊ ውሎ በዚህ ገባን ወጣን እያልን መናገር አያስፈልግም። ይህን አሸባሪ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እናተፋዋለን ” ማለታቸው ይታወሳል።

መከላከያ አሁን ላይ በትግራይ ክልል ውስጥ ገብቶ መዋጋት ያቆመ ሲሆን የትህነግ ሃይል ሊያተቃ ሲመጣ አፈግፍጎ አመቺ ቦታ ላይ ሲደርሱ በሂሊኮፕተር እያሳደዱ እንደሚመታቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።


Exit mobile version