Site icon ETHIO12.COM

የሰው ማእበል በመስራት ጠላትን የመዋጋት ስትራቴጂና የህወሃት ጦርነት !

Human_wave_war_tactic !

የሰው ማእበል በመስራት ጠላትን የመዋጋት ስትራቴጂና የህወሃት ጦርነት !

ይህ የጦርነት ስልት አጅግ መአት ህዝብን በመጠቀም ከፋፍሎ ከፋፍሎ እያግተለተሉ ወደ ጦርነቱ በመማገድ የሚደረግ ጦርነት ነው ። ፈረንጆቹ Human wave ይሉታል ። መነሻው ከጥንታዊው ቻይናዊ የጦር ጠበብት Sun Tzu ሀሳብ ይመዘዛል ። Sun Tzu እንድህ ይላል ” Attack like water ” እንደ ውሃ ማእበል ሆናችሁ አጥቁ እንደማለት ነው ።

ራሱን ” የትግራይ መከላከያ ሀይል ” TDF ብሎ የሚጠራው የህወሃት ጦር አሁን እየተጠቀመ ያለው የጦር ስልት ይህን Human wave የተሰኘውን እጅግ አውዳማ የጦር ስልት ነው ።

ሀገራት ወይንም ቡድኖች ይህንን የጦር ስልት ለመጠቀም የሚገደዱት በጦር ትጥቅ ደካማ ከሆኑ ፣ በቴክኖሎጂ ከጠላቶቻቸው ያነሱ በፋይናንስና ሎጀስቲክም ደካማ ከሆኑና በመደበኛ ጦርነት እንደማያሸንፉ እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው ። ያኔ ህዝባቸውን ከህፃን እስከ አዛውንት ፤ ከሴት እስከ ዘንድ አሰልፈው ወደ ጦርነቱ ይሞጅሩታል ። ” ሙተህ አሸንፍ ” ይሉታል ።

ይህን የጦር ታክቲክ የሚከተሉ ሀይሎች በርካታ ህዝብ ስላለቀባቸው ተሸነፍን ብለው አያውጁም ወይንም እጅ አይሰጡም ! ይልቁንስ የተቀረውን ህዝባቸውን እየሰበሰቡ ይሞጅሩታል እንጅ !

በዚህ ጦርነት በሚገባ ያልታጠቁቱ እና ያልሰለጠኑት ሰራዊቶች በረድፍ በረድፍ ይከፈሉና ይዘጋጃሉ ። ከዚያ የጠላት ጠንካራው ግንባር ይመረጥና ያ የህዝብ ማእበል ወደዚያ ግንባር ብቻ እንዲተም ይደረጋል። የመጀመሪያ ሰድፍ በጠላት ሲያልቅ ሁለተኛው ረድፍ ይከተላል። ሁለተኛው ሲያልቅ ሶስተኛው ሶስተኛው ሲያልቅ አራተኛው እያለ እስከመጨረሻው ድረስ ይጓዛል ። ምናልባትም መዋጋት የሚችል ሰው ሁሉ እስኪያልቅ ድረስ ! እጅግ የሚሰቀጥጥ ጦርነት !!

ይህ የጦር ስልት እየተግተለተሉ ጠላት ላይ መከመር ብቻ ነው -ውጤቱ ምንም ይሁን ምን! በዚህ ጦርነት ከእንደ ህወሃት አይነቱ ጦር በሚሞት ሰው ብዛት ከመከላከያ በ 100 እጥፍ ሁሉ ሊበልጥ ይችላል ግና ህወሃት ጦሩን ማጋፈጡን አያቆምም ማለት ነው ። ከፊሉ የጦር መሪ ከፊት አሰልፎ እየማገደ ከፊሉ ደግሞ ከህዝቡ ውስጥ ጠብመንጃ መያዝ የሚችሉ ህፃናትን ሁሉ ሳይቀር እየመለመለ ያቀርባል ። እናም ጦርነቱ ላይ ያለው ሃይል በሙሉ ቢደመሰስ እንኳ ከሗላ የመጣው አዲስ ህዝብ ይተካና ይማገዳል ። መተላለቅ ብቻ !!

ይህንን ጦርነት ቻይና በኮሪያ ጦርነት ወቅት ተጠቅማ ውጤታማ ሁናበታልች ። እንደውም ይህን የጦር ታክቲክ ” የቻይና ታክቲክ ” በማለት ይጠሩታል የዘርፉ ጠበብቶች ። በዚያ ጦርነት የቻይናው መሪ ማኦ ዚዶንግ ሰሜን ኮሪያ በጦር ቴክኖሎጂ ከተራቀቀው የእነ አሜሪካ ግምባር ለመከላከል በሚሊዮን የሚቆጠር ጦሩን ወደ ኮሪያ ላከ።

በኮሪያ ጦርነት የተላከው የቻይና ጦር ቁጥሩ ከ 1.2 ሚሊዮን ይልቅ ነበር ይባላል ። እናም ቻይና ወታደሯን በቡድን በቡድን እየከፈለች በጣም ጠንካራ ባለቺው በአሜሪካ ግንባር ላይ ለቀቀቺው ። የቻይና ጦር ሲያልቅ ሌላው ይተካል ። የተተካው ሲያልቅም ሌላው ይተካል እንደዚህ እያለ በዚያ ግንባር ብቻ 197,000 የቻይና ሰራዊት ረገፈ ። ከአሜሪካ በብዙ እጥፍ የሚልቅ ውድመት ! ግና የአሜሪካን ግስጋሴ በመግታት ጦሯን በመበታተን ተሳካለት። የ Human wave ጦርነት ይህ ነው !

ይህን የጦር ታክቲክ ኢራንም በኢራቅ-ኢራን ጦርነት ጊዜ ተጠቅማው ነበረ። በዚያ ጦርነት ኢራቅ በፋይናንስ ሎጀስቲክና የጦር ትጥቅ ከኢራን ቡብዙ የላቀች በመሆኗ ኢራን ኢራቅን በመደበኛ ውጊያ ማሸነፍ እንደማትችል ተገንዝባዋለች። እናም የህዝብ ማእበልን መረጠች። ህዝቦቿን ከ 12 አመት ህፃን እስከ 70 አመት አዛውንት ወደ ኢራቅ አዘመተቻቸው። የሳዳሟ ኢራቅ ብትፈጃቸው ብትፈጃቸው እንዴት ይለቁ።

በመጨረሻም ሳዳም ኢራናዊያንን በኬሚካል መርዝ ያረግፋቸው ያዘ። ይህ የኢራንን ጦር ሀይል ሽምድምድ አደረገው። ግና ለአስገደሏቸው ሰወች ግድ ያልነበራቸው ኢራናዊያን መቶ ሺዎችን እያፈሱ ወደ ጦሩ አፈሰሱት። ከዚያ መተላለቅ ብቻ ! መቶ ሺዎች በተደመሰሱ በሳምን 180,000 ኢራናዊ ጦሪን እንዲቀላቀል ይደረጋል ። እንደ ውሃ ማጥቃት ! እያለቁ ለማሸነፍ መዋጋት ! እየወደሙ ለድል መዋደቅ !!
የኢራን-ኢራቅ ጦርነት ሲጠናቀቅ በሟች ቁጥር የኢራን ከኢራቅ ቢያንስ በአራት እጥፍ ይልቅ ነበር ።

በHuman wave የጦር ታክቲክ ማሸነፍ የሚቻልባቸው አጋጣሚዎች አሉ። በተለይ በዚህ ጦርነት ላይ የሚሳተፈው ጦር በሚገባ የሰለጠነና ጥሩ ትጥቅ ያለው ከሆነ የሚያሸንፍበት እድል ሰፊ ነው !

ነገር ግን !

ይህንን ታክቲክ የሚከተለው ጦር የመረጠው የጠላትን ጠንካራ ግንባር ካልሆነ ወይንም ደግሞ ጠላት ዋና ሃይሉን ደብቆ ወደ ውስጥ አየሳበ ወጥመድ አዘጋጅቶ የሚጨርሰው ከሆነ ያ ጦር መቼም ራሱን መተካት እንዳይችል ሆኖ ይጠፋል!!!

ህወሃት ይህንን የጦር ታክቲክ መርጦ በብዛት ሰራዊቱ እያለቀ መሆኑ የማይታበይ ነው። ይህ ጦርነት ህፃናትንም እንድትጠቀም የሚያስገድድህ በመሆኑ ህወሃትም ያን እያደረገና ህፃናትን አዛንቶችን በገፍ እየማገደ ነው። ግና ወደፊት መግፋቱን አላቆመም።

የHuman wave ጦር በብዛት በጠላት ይዞታ ላይ በመከመር የሚደረግ ጦርነት እንደመሆኑ ህወሃትም ያን እያደረገ ነው። ግና እንዳልኳችሁ መንግስት ይህንን የህወሃት ታክቲክ ለማበላሸት ወደ ሗላ እየሳበ እና ወጥመድ ውስጥ እያስገባ የሚፈጫቸው ከሆነ የትግራይ ህዝብ ወጣት አልባው ህዝብ ሆኖ ህወሃትም መልሶ ማንራራት እንዳይችል ሆኖ ይደመሰሳል ! የትኛው ይፈፀማል ጊዜ ሁሉንም ያሳየናል !!!

By – Seid_Mohammed_Alhabeshiy

Exit mobile version