Site icon ETHIO12.COM

በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ቡና ተያዘ

በህገወጥ መንገድ በሶስት ተሽከርካሪዎች ሲጓጓዝ የነበረ 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ቡና ተያዘ

በባሌ ዞን ሲናና ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ በሶስት የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲጓጓዝ የነበረ 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ቡና መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የሲናና ወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ሙክታር ሻሌ ለኢዜአ እንደገለጹት በህገወጥ መንገድ በሶስት ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ 364 ኩንታል ቡና ተይዟል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ በሮቤ ከተማ መያዙን ተናግረዋል ።

ቡናው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 85759 ኢት ፣ ኮድ 3-07616 ኢት እና ኮድ 3- 07617 ኢት በሆኑ ሶስት ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ከደሎ መና ወደ አደማ በመጓጓዝ ላይ እንዳለ መያዙን አመልክተዋል።

ኤሮ ትራከር ተብለው የሚጠሩ ሶስት ተሸከርካሪዎች ከስንዴ ጭነት ስር ቡናን በመጫን ወደ አዳማ በመጓዝ ላይ እንዳሉ በሮቤ ከተማ መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ መያዛቸውን ተናግረዋል ።

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተያዘው ቡና 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው መሆኑን ጠቁመው ሁለት ኩንታል ማዳበሪያ የተለያዩ አይነት መድኃኒቶችም አብረው መያዛቸውን አመልክተዋል።

አሽከርካሪዎቹ ለጊዜው በመሰወራቸው ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ለማቅረብ ክትትል እያደረገ መሆኑን ኮማንደር ሙክታር አስታውቀዋል(ኢዜአ)

Exit mobile version