Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ እንደገና አንድ ሆና ተሰፋች፤ ደስም አለን!

ዛሬ ሁሉም ዜጋ ” አገሬ” አለ። ያለ ልዩነት ” ማን እንደ አገር” ብሎ ጮኸ። በራሱ ተነስቶ ” እኔም ወታደር ነኝ ” አለ። ከባህር ማዶ ያሉ ከሃጂዎች አገር ለማፍረስ ሲማማሉ፣ የስልጣን ክፍፍል ሲያደርጉ፣ ግማሾቹ በስተርጅና ሲቀሉ፣ ትርፍራፊ የሚጣልላቸው ሚድያዎች አገራቸው ላይ አድማ ሲጠሩ፣ አንዳንድ ባለሃብት ነን ባዮች ቀን ቀን ቤተ ክርስቲያን፣ ማታ ማታ የትርምስ ቲሌቪዥን ስፖንሰር እያደረጉ ለውድቀታችን ሲተጉ … የአገር ቤቱ ህዝብ ” ዞር በሉ” ብሎ አንድ ሆኖ ጎመራ። “ካሃጂ” ብሏቸው አንድ ሆነ። አንዳንዶቹ ቅሌትና ውርደት አልጠግብ ብለው እየወጋን ባለው ድርጅት ሚዲያ ቀርበው ሲተፉ ” እንሞታለን ላገራችን” የሚል ምላሽ ተሰጣቸው። ኢትዮጵያ አበበች። በልጆቿ ደመቀች። ድሮም ትልቅ ነበርን፣ ድሮም ባንዳን የሚቀጣ ክንድ ነብረንል፤ ድሮም ከተነካን መቸረስ እናውቃለን። ዛሬም ያ እንደሚደገም ማረጋገጫው ታይቷል።

ግብጽ ዝግጁ የሆነ ጦሯ 500 ሺህ ይልቃል። ኢትዮጵያ የሰሜን እዝ ከመመታቱ በፊት 140 ሺህ የሚገመት ሰራዊት ነበራት። የሚገርመው ኢትዮጵያን እየመራ የነበረው ትህነግ 250 ሺህ ወታደር አዘጋጅቶ ነበር። አሁን ላይ ሕዝብ የአገር ጥሪን ተቀብሎ የመከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ወደ ማስልጠኛ ካምፕ እየከተተ ሲሆን በአጭር ጊዜ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን ጦር ትገነባለች።

ትህነግ በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ሲፈራርስ ጎን ለጎን የከባድ መሳሪያ ሙያተኞችንና አዋጊ መኮንኖችን ጨምሮ ጉደለቱን ለመሙላት ጥረት ተደርጓል። ቀደም ሲል በነበረው አደረጃጀት የከባድ መሳሪያ ምድብተኛ ሙሉ በሙሉ የትህነግ ሃይሎች ነበሩ። ሜካናይዝድ ሃይሉን የሚመሩት የትህነግ ሰዎች ነበሩ። የመስመርና የመቶ አዋጊዎች የትህነግ ሰዎች ነበሩ።

ከከፍተኛ መኮንኖች ጀምሮ ከላይ የተዘረዘሩት ባለሙያ ወታደሮች የትህነግ አባላት ስለነበሩ ሰራዊቱ ሲመታና የትህነግ አባል የሆኑት ሲከዱ መከላከያ የባለሙያ እጥረት፣ የሃይል ጉድለት ገጥሞት ነበር። በዚህ ችግር ላይ ይባስ ተብሎ ደግሞ ጦርነቱን በወኪሎቻቸው አማካይነት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመለጠጥ ያለውን ሃይል የማሳሳትና የማዳከም ስትራቴጂ ይከተሉ ነበር።

ትህነግ ተንኮታኩቶ ወደ በረሃ ሲበተን የትህራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተባባሪ ሆኖ ሎጅስቲክ በማቅረብና ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በሰጠው ድጋፍ፣ በተካሄደው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይል አሰባሰበ። አሁን አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት በወጉ ያልሰለጠኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠር ሃይል ይዞ በየግንባሩ በሰው ጎርፍ “ሆ” ብሎ በመግባት ዘመን ያለፈበትን የጥንታዊ ጋርዮሽ ውጊያ እያካሄደ ነው።

ከየግንባሩ እንደሚሰማው ትህነግ የመረጠው የውጊያ ስልት የሰው ጎርፍ በማሰማራት መሆኑ እልቂቱ እጅግ የከፋና ለመናገር የሚዘገንን አድርጎታል። የትህነግ አመራሮች በጦር ሜዳ ውሎ ድል እንዳገኙ ቢናገሩም ሃቁ ግን ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እንደገጠማቸው ነው።

ኢትዮጵያዊያንን ዳግም አንድ ያደርገው ወረራ ሰፈርና ክልል ሳይመርጥ፣ ዘርና ቋንቋ ሳይለየው ” ኢትዮጵያን አትንኩ” በሚል ወጣቱ ወደ ማስለጠኛ እየተመመ ነው። ይህ ሃይል የአገር መከላከያን ሙሉ ያደርጋል። ከሁሉም በላይ ግን ትህነግ የተረተረውን የኢትዮጵያን አንድነት ዳግም እንዲሰፋ አድርጎታል። ለዚህም ነው ” ኢትዮጵያያ በመከራ ውስጥ ዳግም ተወለደች” የተባለው።

እናትና አባት ልጁን እየመረቀ ወደ ግንባር ሲል፣ ስንቅ ሲጎርፍ፣ ደጀኑ አለሁ ሲል፣ ሚሊሻና አርበኛው ሲነሳ፣ ክልሎች ቀልድ የለም በአገር ብለው ሲተሙ ላየ ስሜት ይነካል። ያቺ በብሄርና በጎጥ ተበልታ ስትቃትት የነበረች አገር ዳግም ልጆቿ በፍቅርና በወኔ ” ባባቶቻችን ደም” ሲሉ መመለከት ላለፉት 27 ዓመታት ላነቡና ላዘኑ ዜጎች ሃሴት ሆኗል። ምንም እንኳ ጦርነት የሚደገፍ ባይሆንም ኢትዮጵያ ዳግም ስትወለድ ታይቷል።

ሰላማዊው፣ ጨዋውና በዚህ ዓይነት አገር የማፍረስ ተግባር የሌሉበት አብዛኛውን የትግራይ ህዝብ ጨምሮ ጠቅላላ አገሪቱን በተቀናበረ ዘመቻ ከተላት ነጻ ለማድረግ እየተመመ ያለው ኢትዮጵያዊ ፊቱ ላይ የሚነበበው ቁጣና ቁጭት ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ” መክረናል፣ አስመክረናል፣ ለምነናል፣ አስለምነናል፣ አልሆነም። ዛሬም የትግራይ አባቶች፣ ምሁራን፣ እናቶች ምከሩ። ልጆቻቸሁን ከአሸባሪው ትህነግ ለዩ” በማለት ጥሪ ሲያስተላለፉ፣ ” ኢትዮጵያ ኮርታለች። አነሳሳቹህ ድል አድራጊነታችሁን ያሳያል። ጉንበስ ብዬ በኩራት ምስጋና አቀርባለሁ” ብለዋል።

የጀኖች ተወካዮች ” ብናረጅም እንሞታለን” ሲሉ አገር በድጋፍ ተንቀጥቅጧል። ትህነግ ጦርነቱን ” ከአማራ ጋር ሂሳብ የማወራረድ ነው” በሚል የከሸፈበትን የመለያየት ስልት ዛሬም ሊያናፍስ ቢሞክር መስሚያ ጥጥ ሆኖበታል። በሳምንት ጅቡቲ መስመርን፣ በሁለት ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገባ የቡፌ ግብዣ አይነት አማርጦ ሲደሰኩር ፣ ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ትህነግን ከታሪክ ውስጥ ጭምር አራግፎ ለማውጣት ሆ ብሎ በመነሳት ” ና” እያለው ነው።

ትህነግ በታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች እየተደገፈ ስልጣን ላይ ወጣ፣ መሪ ካልሆንኩና እንዳሻኝ ኢትዮጵያን ብቻዬን ካልጋለብኩ አይሆንልኝም ብሎ ወደ ትግራይ አመራ። ከዛም ቀድሞ ካደራጁት የክህደት ባልደረቦቹ ጋር ሲዶልት ኖረ። ከዛም እንደ አያቶቹ ተሸጠና ባንዳ ሆነ። በባንዳነት የአገር መከላከያን አረደ። የሴት ወታደሮችን ጡት ቆረጠ። ይህ ኢትዮጵያን የጣባ ” ትል” በውክልና ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው። ይህን የተረዳው ህዝብ ” አገር ከሌለ በማን ይለቀሳል” ሲል ሲጋት የነበረውን የልዩነት መርዝ ነቅሎ በመጣል ተነሳ።

ዛሬ ሁሉም ዜጋ ” አገሬ” አለ። ያለ ልዩነት ” ማን እንደ አገር” ብሎ ጮኸ። በራሱ ተነስቶ ” እኔም ወታደር ነኝ ” አለ። ከባህር ማዶ ያሉ ከሃጂዎች አገር ለማፍረስ ሲማማሉ፣ የስልጣን ክፍፍል ሲያደርጉ፣ ግማሾቹ በስተርጅና ሲቀሉ፣ ትርፍራፊ የሚጣልላቸው ሚድያዎች አገራቸው ላይ አድማ ሲጠሩ፣ አንዳንድ ባለሃብት ነን ባዮች ቀን ቀን ቤተ ክርስቲያን፣ ማታ ማታ የትርምስ ቲሌቪዥን ስፖንሰር እያደረጉ ለውድቀታችን ሲተጉ … የአገር ቤቱ ህዝብ ” ዞር በሉ” ብሎ አንድ ሆኖ ጎመራ። “ካሃጂ” ብሏቸው አንድ ሆነ። አንዳንዶቹ ቅሌትና ውርደት አልጠግብ ብለው እየወጋን ባለው ድርጅት ሚዲያ ቀርበው ሲተፉ ” እንሞታለን ላገራችን” የሚል ምላሽ ተሰጣቸው። ኢትዮጵያ አበበች። በልጆቿ ደመቀች። ድሮም ትልቅ ነበርን፣ ድሮም ባንዳን የሚቀጣ ክንድ ነብረንል፤ ድሮም ከተነካን መቸረስ እናውቃለን። ዛሬም ያ እንደሚደገም ማረጋገጫው ታይቷል።

ጦርነት ክፉ፣ አውዳሚ፣ አንዳችም መልክም የለውም። ዛሬም ለማሰብና ለሰላም መገዛት ይቻላል። ለህጻናት፣ ለናቶችና አባቶች እንዲሁም ለአገር ውድመት ሲባል የውክልና ጦርነቱን አቁሞ ለህዝብ የሚመች ሃሳብ ላይ መስማማቱ ይበጃል። በተራ ቀረቶና በሃሰት ጋጋታ የሚመጣ አንዳችም ጉዳይ የለም። ህዝብ ሊራብ፣ ሊጠማ፣ ማናቸውንም ዓይነት ማዕቀብ ሊሸከም ተዘጋጅቷል። ይህ በሆነበት ጉንጭ አልፋ ፕሮፓጋንዳ ከሁሉም ወገን ዋጋ አያመጣምና ሳያቃጥል በቅጠል!! ኢትዮጵያ እንደገና አንድ ሆና ተሰፍታለች። ደስም ብሎናል!!


Exit mobile version