Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ሲዘጋ፤ ኢትዮጵያ ትወቀሳለች- እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?

ኢትዮጵያዊያን ላለፉት 50 ዓመታት ስለምን በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ይሰቃያሉ? በረሃ ሆኖ ስቃይ፣ መንግስት ሆኖ መከራ፣ ሲባረር ደግሞ ” እኔ የማልመራት አገር ትፍረስ” ብሎ ዘመቻ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የድሮው ሳይቆጠር ስለምን ግማሽ መዕተ ዓመት በትህነግ ሲጠበስ ይኖራል? መቼ ነው ይህን ሕዝብ ትህነግ የሚተወው? የሰሞኑ ክተት የሳምንቱ ኩርፊያ ውጤት አይደለም። የተጠራቀመ እንጂ!! በሁዋላ የከፋው እንዳይመጣ አቅም ያላቸው ይምክሩ።

በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ግረጎርይ ሜክስ ” የዓለም የምግብ ድርጅት በትግራይ ከአርብ ጀምሮ ምግብ የለውም። ለመመገብ ላሰብናቸው ሰዎች ሁሉ ለመድረስ በየቀኑ 100 መኪናዎችን ያስፈልጋሉ። ወደ ትግራይ ምግብና ሌሎች አቅርቦቶች ጭነው እየተጓዙ ያሉ 170 የጭነት መኪኖች በአሁኑ ሰዓት በአፋር ታግደው መሄድ አልቻሉም። ሰዎች ተርበዋል። እነዚህ የጭነት መኪናዎች አሁን እንዲንቀሳቀሱ ሊፈቀድላቸው ይገባል” ሲሉ የኢትዮጵያን መንግስት በስም ጠርተው አውግዘዋል።

የአፋርና የኢትዮጵያ መንግስት መኪኖቹ በረሃብ ለተጎዱት የትግራይ ሕዝብ እንዲጓጓዝ እንዲያደርጉ የሚያሳበው መግለጫ ትህነግን በስም እንኳን አያነሳውም። አፋር ሲወጋ፣ የአፋር ዜጎች ሲፈናቀሉ፣ የአፋር ሰላማዊ ዜጎች ሲገደሉ እኚህ ግለሰብም ሆኑ አሜሪካ ወይም አውሮፓ ኮሚሽን ወይም አገራት ወይም ሚዲያዎች፣ ወይም የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ነን የሚሉ ያሉት ነገር የለም።

መኪኖቹን አናአልፍም በሚል ጌታቸው ረዳ በአፋር ክልል ጦርነት መክፈታቸውን፣ ዓላማቸው መንግስትን ማስጨነቅና የጅቡቲን መንገድ ማስተጓጎል መሆኑንን በይፋ በሮይተርስ መናገሩ እየታወቀ፣ የአፋር ክልል” ድንበሬ ተጥሶ ተወጋሁ፣ በአስር ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉብኝ” እያለ እየጮኸ የዓለም የምግብ ድርጅትም ሆነ አሜሪካ ጸጥ ነው ያሉት። ይህ እንግዲህ የሚያመላክተው በግልጽ ኢትዮጵያ እንድትበተን ተባባሪ ሆነውና በድርጅት እየሰሩ መሆኑንን ነው።

ኢትዮጵያ ጡሯ ተኩስ እንዲያቆም፣ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ፣ በትግራይ የተፈጸመ ህገ ወጥ ድርጊት እንዲጣራ በሚል ፍትህን ረግጠው ጫና ሲያደርጉ ቆይተው ኢትዮጵያ ሁሉንም እሺ አለች። ትህነግ ወደ ነበረበት ሲመለስ ” ባንዳ” እያለ ባደባባይ ሕዝብ ሲረሽን የተነፈሰ የለም። የኤርትራ ስደተኞችን ሲረሽንና ሲዘርፍ፣ ሲበትናቸው ከተራ ” ሰጋን” ጩኸት ሌላ ማንም አልተነፈሰም። ዛሬ የኤርትራ ስደተኞች ” ዓለም ረሳን” እያሉ

እየጮሁ ነው። ሰሚ የለም።

ትህነግ ከክልሉ በመውጣት ጦርነት ከፍቶ ሳለ ሃይ የሚለው የለም። ትህነግ ከክልሉ በመውጣት ዝርፊያ ሲፈጽም ለመገሰጽ የሚፈልግ አካል የለም። ዛሬም መንገዱን ዘግቶ ሳለ መንግስትን የሚኮንኑት በየት በኩል ሄዶ መንገዱን እንዲከፍት አስበው እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ሌላው ቀርቶ ሕጻናት በገሃድ ጦር ሜዳ ውለው ሲገኙና በአንደበታቸው ምስክርነት እየሰጡ ትንፍሽ የሚል የለም። በሆነውም ባልሆነውም የምትወቀጠው ኢትዮጵያ ናት።

ፍትህ እየተዛባ ያለው በየዘርፉ ነው። ኢትዮጵያ በታላላቅ ባንኮች ያላትን ሃብት እንዳትጠቀም ተደርጋለች። ትህነግ በተቀጣሪነቱ አሜሪካ ድጋፍ አሰባስባለትና በቀጥታ እየረዳቸው አገር እያተራመሰ ነው። መንግስት ምላሽ ሲሰጥ ” ጂኖሳይድ፣ የጅምላ ጭፍጨፋ” እየተባለ መግለጫ ይንጋጋል።

መንግስት ዝም ሲል ትህነግ ሽብሩን እያሰፋ፣ ሲያሻው የድል ዜና ያሰማል። መንግስት መከላከያው አዞ በአየርና በምድር ዋጋ ሲሰጠ ዓለም ይጮሃል። አሜሪካ በነደፈቸው ” ሕሳጻናትን ከፊት አሰልፉ” ስልት ሲገሉ ” ጅግና” ሲገደሉ ” አልቃሽ” እየሆኑ ግራ አጋብተዋል።

ከስር ያለው ቪዲዮ አፋር ላይ ትህነግ መኪና አቃጥሎ ሲዘርፍ ነው። ይህና ይህን መስል መረጃ የዓለም የምግብ ድርጅት ደርሶታል። ግን ሊሰማ አይፈቅድም። ኢትዮጵያና የአፋር ክልል ተሽከርካሪዎቹን ይልቀቁ ሲሉ፤ ዞረው በትግራይ በኩል ሄደው ነው የሚከፍቱት ወይስ ምንድን ነው የሚያደርጉት? ይህ ግራ የገባ መመሪያቸው መጨረሻው ምን እንደሆነና ይህን ሁሉ የሚሉት ምን እንዲሆን ፈልገው እንደሆነ ታውቋል።

ዛሬን ጨምሮ ወደ ማሰልጠኛና ወደ ግንባር የሚከተው ሕዝብ፣ ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይል፣ ተቀድሞ ሰራዊት አባላት፣ በጥቅሉ ድፍን ኢትዮጵያ ሲተም፣ እናት ልጇን መርቃ ስትሸኝ አሜሪካ ማየት አትችልም። ይህ ህዝብ እንዴት ካሁን በሁዋላ በትህነግ ይገዛል ተብሎ ይታሰባል? ትህነግስ ይህን እያየ እንደገና ሌላ ” ብአዴንና አሮጌውን ኦህዴድ ” ይዞ ስለመምጣት እንዴት ይመኛል?

በለውጡ ማግስት ክልሉን እየመራ፣ ባለው ውክልና በሰላም መኖር ሲችል አጉል እብሪት ውስጥ ገብቶ የትግራይን ሕዝብ ለመከራ ዳረገ። ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት ተከናነበ። ህዝቡን በችጋር አስፈጀ። ይህ ካለፈው የማይማር ድርጅት ሊመራው ወደማይችለው አካባቢ ለመምጣት እየቋመጠ፣ የተሸጠበትን ዋጋ ለመለስ ለምን ንጹሃንን ያስጨርሳል? የትግራይን ሕዝብስ ከሁሉም ጋር እሳትና ጭድ አድርጎ ይኖራል?

ኢትዮጵያዊያን ላለፉት 50 ዓመታት ስለምን በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ይሰቃያሉ? በረሃ ሆኖ ስቃይ፣ መንግስት ሆኖ መከራ፣ ሲባረር ደግሞ ” እኔ የማልመራት አገር ትፍረስ” ብሎ ዘመቻ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የድሮው ሳይቆጠር ስለምን ግማሽ መዕተ ዓመት በትህነግ ሲጠበስ ይኖራል? መቼ ነው ይህን ሕዝብ ትህነግ የሚተወው? የሰሞኑ ክተት የሳምንቱ ኩርፊያ ውጤት አይደለም። የተጠራቀመ እንጂ!! በሁዋላ የከፋው እንዳይመጣ አቅም ያላቸው ይምክሩ። ነጮቹ ፈልገው የተከለከሉት የባርነት ጥያቄ ስለሆነና እሱ ደግሞ ከቶውንም ስለማይፈቀድ የውስጥ መግባባቱ ቢቀድም የተሻለ ይሆናል። ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ ሁሉም ሃይሉን መጠቀም ይቀጥላል። ሁሉም ራሱን መከላከል ይጀምራል። ነብሳቸው ይማረውና ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት ጥፍር ሁሉ መሳሪያ ይሆናል። ያን ጊዜ “የሰው ማእበል” የሚባለው ጉድ ይታያል!! ቢቀር ግን መልካም ነው።

ሰለሞን አስቻለው

ማስታወሻ – ሃሳቡ የጸሃፊው እንጂ የአዘጋጁን አቋም አይወክልም


Exit mobile version