ETHIO12.COM

ትህነግ ሲገረፍ አሜሪካ “ተኩስ አቁም ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ” አለች

“ፓርቲዎቹ ” ይላል ኔድ ፕሪስ ሲጀመር። መንግስትንና “አሸባሪ” ተብሎ የተሰየመውን ትህነግን ማታቸው ነው። ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ፣ በአፋጣኝ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙና ሁሉን አቀፍ ወደሆነ የፖለቲካ ንግግር እንዲያደርጉ ያሳስባል። ሁለቱም የንግግሩን ዓላማ የሚያስት ምልልስ እንዲቆጠቡ ያሳባል።

ላለፉት 50 አመታት በትህነግ አማካይነት መሰቃየታቸውን፣ በረሃ እያለ፣ መንግስት ሆኖ፣ ከመንግስትነት ከተወገደ በሁውላ ሽብርን በየክልሉ እየፈለፈለና የልዩነት ፖለቲካን እያዘራ ሰላም የነሳው ትህንግ ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ እንዲፋቅ ዘመቻ ክተት መታወጁ አይዘነጋም።

በሚሊዮኖች ከዳር እስከዳር ንቅናቄ ፈጥረው የአገር መከላከያን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበውና፣ ሌሎችም በወዶ ዘማችነትና በክተት ወደ ግዳጅ እያመሩ ባሉበት ወቅት አሜሪካ ይህን አስገዳጅ መግለጫ ማውጣቷ አስገራሚ ሆኗል።

በቲውተር መልዕክቱ ስር ” አፋራና አማራ ክልል ሲወጋ የት ነበራችሁ?” ከሚለው ምጸት ጀምሮ አሜሪካኖችን ” አሁን ትህነግ ዙሪያው ተከቦ መደቆስ ሲጀምር ተኩስ አቁም የምትሉ … በሚል ክፉኛ ዘለፋ ተገጥግጧል።

ከትናንት በስቲያ ጌታቸው ረዳ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑንን አስታውቆ፣ ትናንት ደግሞ ትህነግ ከቀድሞው ስምንት ቅድመ ሁኔታዎች ተቀንሶ በስድት ቅድመ ሁኔታዎች የተጀበ የሰላማዊ የንግግር መግለጫ አሰራጭቶ ነበር።

በጀት፣ አገልግሎት፣ ነጻ ትራንስፖርት፣ የመሳሰሉት ባስቸኳይ እንዲፈቀዱለት ትህነግ መጠየቁን ተከትሎ ” አንድ በሽብርተኛ ቡድን የምትወጋ አገር ለሚወጋት ድርጅት እንዴት በጀትና አገልግሎት ታቀርባለች?” የሚል የመርህ ጥያቄ ለአቶ ጌታቸው ቀርቦ ነበር።

አዲስ አበባ ለመግባት መንገድ ሲያማርጡ የነበሩት ትህነጎች በምን ዓይነት ተዓምር በዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ የሰላማዊ ድርድር ሃሳብ ለማቀንቀን እንደተነሱ በግልጽ ባይነገርም፣ በጅቡቲ መስመር መንገድ ዘግቶና፣ በወልደያ በኩል እስከ ደሴ በመዝለቅ የመደራደሪያ ሃይላቸውን ለመጨመር ያደረጉት ጥረት በኪሳራ ስለከሸፈ እንደሆነ ግምት አለ።

በተለይም በአፋር ግንባር ሶስት ክፍለጦር የተደመሰሰበት ትህነግ፣ የኪሳራው መጠን በመከላከያና በአፋር ልዩ ሃይል ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ በማይጸብሪ የሱዳንን ኮሪዶር ለማስከፈት በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ እጅግ ሰፊ ዋጋ አስከፍሎት ባለመሳካቱ እርቅን አማራጩ ለማድረግ እንዲገደድ እንዳደረገው ዜናውን ተከትሎ መረጃ እየወጣ ነው።

አቃቤ ህግ አሁን በህይወት ባሉት አመራሮች ላይ ሰፊ መረጃ አዘጋጅቶ ክስ ከመጀመሩና የክስ ሂደቱን እያጣደፈ ባለበት ውቅት አሜሪካ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቋ “ድርድር እንዴት” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።



ትህነግ የማጥቃት ሂደት ላይ በነበረበት ወቅት ማርቲን ፕላውት የሚባለው የትህነግ ተከፋይ የህዝብ ግንኙነት፣ ዶ/ር ደብረጽዮንን እንደነገሩት ተቅሶ “ትህነግ የጅቡቲን መስመር ተቆጥጥሮ እርዳታውን በቀጥታ ወደ ጅቡቲ ያስገባል” በሚልበት ወቅትና እነ ጌታቸው ወደ ደብረብረሃን፣ አዲስ አበባ፣ ወልቃይት ጎንደር … አራት ኪሎ እያሉ መነገድ ሲያማርጡ አሜሪካ ጸጥ ብላ እንደነበር ይታወሳል። ከሁሉም በላይ ዓለም በሚከለክለው ሕጻናትን በጦርነት የመማገድ ወንጀል ትህነግ በሚታክት ማስረጃ ሲከሰስ አሁንም አሜሪካ ተለጉማ ነበር።

የአሜሪካንን ጥሪ አስመልክቶ ከትህነግ በኩል ይቃወማሉ የሚል ግምት ባይኖርም ይህ እስከተሳፈ ድረስ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

ይህ መግለጫ ከመውታቱ በፊት የ ሳማታን ፓወር መንግስት ለማሰገደድና ለመጫን በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ በይፋ ተገልጾ ነበር። ሴትየዋ ጥሩ የሚባሉ የትህነግ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ናቸው።


Exit mobile version