ETHIO12.COM

መንግስት “ያልኩት ደረሰ” አለ፤ ትህነግ በጦርነት ያጣውን ድል ወደ ሚዲያ ዘመቻ ቀየረ

“ገና ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለ” በሚል ስልጣን ሲያዝ ” መዕራብ ትግራይ” ብሎ የከለለውን መሬትና የሱዳን መገናኛ ኮሪደሩን በሃይል እንደሚያስመልስ ያስታወቀው ትህነግ በጦርነት ያሰበውን ማድረግ ባለመቻሉ ዘመቻውን እንደቀድሞው ወደ ሚዲያ እንዳዞረው ተገለጸ።

በማይጸብሪ፣ በሁመራና በወልቃይት ለሳምንታት ከፍተኛ ሰራዊት አሰልፎ ሲዋጋ የነበረው ትህነግ በተደጋጋሚ ” በሃይል ደርምሼ የሱዳን መገናኛ ኮሪዶሩን አስከፍታለሁ” ባለው መሰረት ስላልተሳካ፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ስላጋጠመውና ስለተመታ ሌላ ስልት እንደሚቀይር የመንግስት የውቀታዊ መረጃ ማጣሪያ አስታውቆ ነበር።

የውቅታዊ መረጃ ማጣሪያ እንዳስታወቀው የትህነግ ሃይል በጦርነት የተገደሉበትን አስከሬን በማሰብሰብና በጅምላ በመቅበር “የጅምላ መቃብር ተገኘ፣ ነጹሃን በጅምላ ተጨፈጨፉ” እንደሚል፣ በሁመራ አንዳችም ችግር በሌለበት በአሁኑ ወቅት የጅምላ ግድያ እንደተፈጸመ አድርጎ መረጃ ለማሰራጨት እየሰራ መሆኑንን ” ማስጠንቀቂያ” ሲል ሁሉ በተደጋጋሚ አመልክቶ ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ በአፋር ግንባር ክፉኛ የተጎዳውና በርካታ ሰራዊቱን ያጣው አሸባሪው ሃይል አስከሬን ወደ መቀለ በሲኖ ትራክ በማመላለስ በተመሳሳይ ለፈጠራ ቅስቀሳ ሊጠቀምበት እየሰራ መሆኑን ተዘግቦ ነበር።

ዛሬ የመንግስት ሚዲያዎች ተቋሙን ጠቅሰው እንዳሉት ከሳምንት በፊት አሸባሪው ህወሓት በሁመራ ከተማ የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጸመ የሚል ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀ መሆኑን መንግስት በደህንነት ምንጮቹ አማካኝነት የደረሰበትን መረጃ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ሀምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም መንግስት በወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ በኩል “ማስጠንቀቂያ በሚል በለቀቀው መረጃ መሰረት፤ “ጁንታው ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል” ሲል አስቀድሞ አስጠንቅቆ ነበር።

በወቅቱም የመረጃ ማጣሪያው፤ ጁንታው የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ እንዳፈተለከበትና በዕቅዱ መሠረትም ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርጎ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጾ ነበር። ይህ መረጃ በተለቀቀ ማግስትም የአሸባሪው ደጋፊና ተመጽዋች ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን በሁመራ ንጹሀን ተገድለው ወንዝ ውስጥ ተጥለዋል የሚል አስቀድሞ የተቀናበረውን የሀሰት ዘመቻ መቀባበል ጀምረዋል።

የወቅታዊ መረጃ ማጣሪያው በዚያው ቀን በለቀቀው ሁለተኛ ማስጠንቀቂያም፤ ቡድኑ በአፋር ግንባር በፈጠረው ትንኮሳ ከአፋር ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት ምላሽ የተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ ከአካባቢው ሲሸሽ ከ300 በላይ አስከሬኖች በሲኖ ትራክ ጭኖ ወደ መቀሌ መፈርጠጡን አስታውቆ ነበር።በወቅቱ እንደተገለጸውም፤ በዚህ መልክ የሚያሸሻቸውን የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖች በአንድ መቃብር በመቅበር የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው መቃብሮች አስመስሎ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑን የደኅንነት ምንጮችን ጠቅሶ መረጃ ማጣሪያው መግለጹ ይታወሳል።

መንግስት ደጋግሞ እንዳለው ኒውዮርክ ታይምስና ሮይተርስ፣ እንዲሁም የጀርመን የአማርኛ ድምጽ ይህንኑ ዜና ተቀባብለውታል። ዜናው የተሰማው ደግሞ ሳማታን ፓወር ሱዳን ባሉበትና ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት አንድ ቀን በፊት ነው።

የሱዳን ባለሥልጣን በከሰላ ግዛት ከወንዝ ውስጥ ከ40 የሚበጥ አስከሬን መገኘቱን አሶሲየትድ ፕሬስ አስታውቋል። የዩኤስ ኢ አይ ድ ዋና መሪ እግራቸው ሱዳን መንካቱን ተከትሎ ከናይሮቢ የተሰራጨው ዜና “ሟቾች ከትግራይ ክልል ጦርነት የሸሹ ይመስላሉ” ሲል የሱዳን ሃላፊዎችን ጠቅሶ ነው የዘገበው።

በጥይት የተመቱ እንዳሉበትም ዜናው አስፍሯል። ልክ መንግስት በጦርነት የተገደሉ እንዳለው ጥያት ህይወታቸውን የነጠቃቸው እንዳሉበት በዜናው ተጠቋሟል። ይኸው ውሃ ላይ ተንሳፎ የታየው አስከሬን በህክምናም ሆነ በማናቸውም ዓይነት የምርመራ ዘዴ ማጣራት እንዳልተደረገበት ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት የሱዳን ባለሥልጣን አመልክተዋል።

“ምክንያቱን ለማወቅ በባለሙያዎች ምርመራ መጣራት ይኖርበታል” ሲሉ ባለስልጣኑ ማስታወቃቸውን ዜናው ከጉዳዩ ራሱን ለማሸሽ ያህል አመልክቷል። መታውቂያ፣ የተለየ ማንነትን የሚገልጽ ወይም በመልክ የሚታወቅ ወይ፣ም አንድ ማጣሪያ ባልተካሄደበት ” የትግራይ ሰዎች ናቸው” ያለው አሶሲየትድ ፕሬስ ዜናውን መልሶ ” አስከሬኖቹ ማጣራት እንደሚደረግባቸው አስነብቧል።


Exit mobile version