ETHIO12.COM

የሳማንታ ፓዎር አጀንዳ፣ “ቀይ መስመር” በመሆኑ ሳይጀመር ተቋጭቷል

ጨዋታው በሁለቱም ወገን የህልውና ነው። ጉዳዩ የተቸገሩትን መርዳት ሳይሆን ትህነግን የማዳን ነው። ሲጀመር ጉዞው ወደ ሱዳን የሆነበት ምክንያትና ከዛ ሆነው የሚያሰራጩት ትዊተርና አዲስ አበባ ከመግባታቸው በፊት የሚያቀነቅኑት ጉዳይ ዓላማቸው አንድና አንድ መሆኑንን የሚያሳይ ነው። ” በትግራይ ቀውስ ሳይሆን ጥፋት ነው ያለው። በርካታ ወሳኝ ስብሰባዎች አሉኝ። እርዳታ እንዳይታገድና ቀውሱ እንዲቆም ጫና አደርጋለሁ” ያሉት ሳማንታ ፖወር ከሱዳን የሽግግር ካውንስል ሊቀመንበር ጋር ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ ምቹ ሁኔታ በሚፈጠርበት አግባብ መነጋገራቸውን በስኬት ገልጸዋል። ሱዳን ጦርነት ከፍታ ኮሪዶሩን እንድታስከፍት ተስማምተው ይሁን ሌላ ግልጽ አይድለም። ግን ይሸታል። መንግስት ጥያቂያቸው ተቀባይነት እንደሌለው ጠቅሶ መግለጫ ሰጥቷል።

ሴትየዋ ሱዳን ሆነው እያሰራጩ ያሉት የአንድ ወገን መረጃ፣ የአንድ ወገን አቤቱታና፣ አንድ ወገን ያለበት ካምፕ ጉብኝታቸው ላይ የተነገራቸውን ነው። መንግስትን እያበሻቀጡና ስሜት በሚነካ አገላለጽ ዓለምን እየሰበኩ ናቸው። መተደጋጋሚ የሚያሰራጩት መልዕክት ምን አልባትም በቀጣይ ሊወሰድ ለታሰበ እርምጃ ማመቻቺያ “ሱዳንም ነበርኩ፣ ኢትዮጵያም ነበርኩ” በሚል የታማኝነት ገበያ ላምከማቸት ይመስላል። ቸግሩ ቢኖርም አንድ መፍትሄ ለመፈለግ እንደመጣ ባለስልጣን ሚዛናቸውን መጠበቅ አይታይባቸውም።

የሳማንታ ፓዎር ቁልፍ ጥያቄ ” በሱዳን በኩል በር ክፈቱ፣ ክፈቱና ክፈቱ …” ነው። ሌሎቹ ንግግሮች ማዳመቂያ ናቸው። እሳቸው ይህን ባሉ ቅጽበት ልክ እንደ በፊት መንግስት በሱዳን በኩል ኮሪዶር መክፈት እንደማይቻል ይፋ አድርጓል። እንዲህ ዓይነት ፈቃድ ሰጥቶ ራሱን በራሱ አያንቅም።

ንግግሩ ከመጀመሩ በፊት እሳቸውም መንግስትም የማይታለፍ መስመር አስመረዋል። የሱዳን ኮሪዶር እንዲከፈት ግፊት ማድረጊያው “የዕርዳታ ቁሳቁስ በቀጥታ ከሱዳን ወደ ትግራይ እንዲገባ ነው” መንግት “ይሄ ሌላ ያ ሌላ” የሚል የቆቅ ፖለቲካ እየተጫወተ ነው። “ሕዝብም የፈለገው ቢመጣ እንችለዋለን” ሲል የመንግስትን ውሳኔ ድጋፉን ስፍራና አመለካከት ሳይለይ አሳውቋል። ደጀንነቱና ፍልሚያውን ተካፍሎ በተግባርም እየሰራ ነው።

መንግስት ድሮ ደርግ እንደተታለለው ከቶውንም እንደማይታለል በግልጽ ቋንቋ ሲያስቀምጥ ” ህልውና ላይ ድርድር የለም” በሚል ነው። ትህነግ በማይጸብሪ በኩል ጥቃት በመፈጸም ወደ ተዘጋው ኮሪዶር ለማምራት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳልተሳካ ታውቋል። አሁን አሁን የሚሰማው ደግሞ ትህነግ የመሳሪያና ተተኳሽ ጥይት፣ እንዲሁም ሎጂስቲክ በከፍተኛ ደረጃ እንዳጠረው ነው።

በዚህ ላይ ሰሞኑንን የኢትዮጵያ አየር ሃይል በተመረጡ የሎጂስቲክ ማከማቻና ማስልጠኛ ተቋሞች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። እናም የአሜሪካ ሩጫ የሱዳንን ኮሪዶር አስከፍቶ ትህነግ ግብጽ ኮልኩላ የምትጠብቀውን መሳሪያና ማይካድራ ጭፍጨፋ ፈጽሞ የሸሸውን ታጣቂ ሃይል ለማስገባት ነው።

ፋይናሻል ታይም የትህነግን ሃላፊዎች ጠቅሶ አሁን ቀሪው ዘመቻ ጠላትን ከምዕራብ ትግራይ ( ወልቃይት ማለቱ ነው) በማስወጣት ከሱዳን ጋር የሚያገናኝ ኮሪዶር ማግኘት፣ ይህ ሲሆን ሱዳን ሰለጥነው በዝግጅት ላይ ያሉ ሰላሳ ሺህ ወታደሮችም ጦርነቱን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ እንዳሉ አስነብቧል።

ከአፍታ በሁዋላ ” ሰላሳ ሺህ ወታደሮች” የሚለው ” ሰላሳ ሺህ ያልታጠቁ ንጹሃን” በሚል መቀየሩ ታየ። መረጃውን አስመልክቶ ከላይ የጠቀስናቸው ” ይህ የሚያሳየው ዘገባውን ዋናው ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚሰራው የማዘዣ ቢሮ ካየው በሁዋላ ሚስጢር መውጣቱን አይቶ አስቸኳይ መመሪያ በመስጠቱ የተወሰደ ማስተካከያ ነው። የማይካድራ ጨፍጫፊዎች ተመልሰው ሊያርዱ ወደ ነበሩበት ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ኢትዮጵያ ስትወተውት የሰማ አልነበረም። አሁን ራሳቸው አጋለጡ። የአምላክ ስራ ነው” ብለዋል። አክለውም “በማያካድራ ጉዳይ ሃቁን ይፋ አድርጎ ሳይገፋበት ሆን ብሎ የተኛውና፣ በመጨረሻ ጭፍጨፋውን የትህነግ አለቆች ስለማዘዛቸው ማረጋገጫ የለም ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ ኮሞሽን እርቃኑንን ቀርቷል። ይህን ሲመከለት ሊያፍር ይገባዋል” ሲል ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

“ባልታጠቁ ታማኞች” እና በ“ወታደሮች” መካከል ጥልቅ ልዩነት አለ። በእውነቱ የዚህ ዘገባ ጥራት እና ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል ” ሲሉ የአቶ ኮኮብን መረጃ ደግመው ያሰራጨቸው ብራውኒ ብሩቶን የአትላንቲክ ካውንስል አጥኚ ናቸው። ሙሉውን እዚህ ላይ ይንብቡ

የሳማታን ጉብኝት አስመልክቶ መንግስት በቂ ዝግጅት አድርጎ እንዲያነጋግራቸው ሰፊ ምክረ ሃሳብ እየቀረበ ቢሆንም ገና እግራቸው አዲስ አበባን ሳይረግጥ እያሰራጩት ያለው የቲውተር ዘመቻ ለውይይት የመጡ እንዳልሆነ የሚያመላክት ነው።

የሚመሩት የዕርዳታ ተቋም ” የፖለቲካ ሹመት ሰጠዎት እንዴ” በሚል ከሱዳኑ ሉአላዊ ካውንስል ጋር በተለያዩ እሳቸው በዘረዘሩዋቸው ጉዳዮች መወያየታቸውን በገለጹበት ስር

ክፉኛ የትወረፉት የአሜሪካ ባለስልጣን ” ጫና አደርጋለሁ” ሲሉ እየዛቱ ነው።

ልክ ትህነግ “በሳምንት ውስጥ የጅቡቲን መንገድ ቆርጬ ቅድመ ሁኔታ ያለውን የድርድር ሃሳብ በማስገደድ ተጋባራዊ አደርገዋለሁ፤ ወልቃይትንም በሃይል ጠራርጌ እወስዳለሁ” ሁሉ ” የእርዳታ ማስተላለፊያ ኮሪደር እንዲከፈት ጫና አደርጋለሁ” የሚሉት ባለስልጣን የንግግር ቅርጽ እንጂ የዓላማ ልዩነት የማይታይበት አቋም ይዘው ለንግግር መምጣታቸው አስቀድሞ በመረጋገጡ አዲስ ነገር እንደማይጠበቅ ከወዲሁ እየተሰማ ነው።

በ 2014 ከኦባማ ጋር በነበረዎት የስልጣን ዘመን ምን ተማሩ? ሲል የኒውዮርክ ታይም ሲጠይቃቸው ” Don’t trust the press” ሲሉ ያስታወቁት ሳማንታ ፖወር ዛሬ ላይ በሃስተና በፈጠራ ዘገባ. አለያም ይህንኑ በማመቻቸት የተጠለፉ መሆናቸው እየታየ ብዙ መጠበቅ ሞኝነት እንደሆነ ከወዲሁ የሚናገሩ በርካቶች ናቸው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ሁሉም ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ይህንኑ ጥሪ ለአፍታ እንኳን የማያነሱት ሳማንታ ፓዎር፣ በሱዳን የስደተኞች ጣቢያ ሲጎበኙ ወደ አገራቸው መመልስ የሚፈልጉ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን እንዳገኙ ጠቁመው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ከማምራታቸው በፊት “ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁም ሊያደርጉ ይገባ” ሲሉ ጽፈዋል። በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዎችን የጎዳው ይህ ግጭት ” ሊቆም ይገባል” ብለዋል።

ሰሞኑንን በወታደራዊ ሃይል ከፍተኛ ሽንፈትና ሰብአዊ ቀውስ የደረሰበት ትህነግ በአዋጊው ጀነራል ጻድቃን አማካይነት የአማራና አፋር ክልልን ዘልቆ በመግባት ጥቃት የፈጸሙት መንግስት ቅድመ ሁኔታ ተቀብሎ እንዲደራደር ለማስገደድ ታልሞ መሆኑንን ለቢቢሲ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

እሳቸው ይህን ባሉ ማግስት በጦር ሜዳ ነገሮች መልካቸውን መቀየራቸውን የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየወጡ ነው። ጀነራሉ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሚስጢር እንደራደር ማለታቸውን ከታማኝ ምንጭ ሰምቻለሁ” ሲሉ ወታደራዊ ሽንፈቱን ለማስተባበል በቃለ ምልልሳቸው አስታውቀዋል።

እሳቸው ይህን ይበሉ ቢሉምም መንግስት ከቶውንም ከትህነግ ጋር እንደማይደራደር ለቢቢሲ ዛሬ ይፋ አድርጓል። የመንግስት ትዕግስት ካለቀ በሳምንት ጊዜ ውስጥ የሚሆነውን ማየት ነው ሲል መንግስት ዝቷል። ሙሉ ዜናውን ለብቻው እዚህ ላይ ያንብቡ

በዚህ ሁለት የህልውና ጉዳይ የተወጠረው ንግግር ተጅመሯል።


Exit mobile version