ETHIO12.COM

አብነት ጥይት የማይበሳው መኪና ለማስገባት መንግስትን ጠየቁ

አቶ አብነት ገብረመስቀል ጥይት የማይበሳው መኪና ማስገባት እንዲችሉ ለመንግስት ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። ጥያቄውን ያቀረቡት ከስልጣንና ከከፍተኛ ሃላፊነት ከተነሱ በሁዋላ ልህይወታቸው እንደሚፈሩ በመግለጽ ነው። የመንግስት ምላሽ አልታወቀም።

ለሶስት አስርተ አመታት የሼኸ መሀመደ ሁሴን አሊ አላሙዱ ወኪልና ” እንደራሴ” ሆነው የኖሩት አቶ አብነት፣ ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ጠቅሰው ጥይት የማይበሳው አውቶሞቢል ለማስገባት ጥያቄ እንዳቀረቡ ኢትዮ 12 ጥያቄው ከቀረበላቸው ወገኖች ሰምታለች። ይሁንና መንግስት አቋሙ ምን እንደሆነ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ውስት፡አዋቂዎች እንደሚሉት ጥያቄው ተቀባይነት አያገኝም።

በባለሃብቱ ዙሪያ ከበው የነበሩ አሁን ጎራ ለይተው መታኮስ በመጀመራቸው ከወዲሁ በርካታ ሚስጥሮች ከዛም ከዚህም እየተሰሙ ነው። ሪፖርተር ጋዜጣ ከ12 ዓመት በፊት በድርጅቱ ባለሃብቱ ድርጅቶቻቸውን አስመልከቶ ዘመናዊ አስተዳደር እንዲመሰረቱ፣ ሁሉም እንብላው እንደሆኑ፣ ነየቦታው እጅግ አሳፋሪ ተጋባር እንደሚፈጸም፣ ከጥጋባቸው ብዛት ” የውሽሞች ቀን” እያሉ የሰው ሚስት እንደሚያማግጡና እንደሚነግጡ፣ በኢትዮጵያ ዝርፊያንና ክህደትን እያስተማሩ እንደሆነ፣ በጊዜ ማስተካከያ ካልተደረገ መስመጥ እንደሚመጣ በማስረጃና መረጃ ላይ ተንተርሶ ሲዘገብ እንደነበር ይታወሳል። በዚህም በአዘጋጁ ላይ የግድያ፣ የዚህ ዌብሳይት ባለቤት ላይ ይፋ ያለወጣ ግድያና ሙከራና በድህንነት አስገድዶ ከስራ የማስወጣት ወንጀል መፈጸሙ የሚታወስ ነው።

በሌላ ዜና አቶ አብነት ገብረመስቀል ኦዳ ከመሬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ጉዳያቸውን የሚከታተሉ ለኢትዮ 12 አስታወቁ። የገንዘብ ብክነትና ህግን ያልተከተሉ ክፍያዎች የፈጸሙባቸውና አክሲዮን ያስተላለፉባቸው አግባቦች እየተመረመሩ መሆኑም ታውቋል።

ከሼኽ መሐመድ አላሙዲያ ጋር ለሶስት አስርት ዓመታት እንደዘለቁ የሚነገርላቸው አቶ አብነት የተጠራቀመ መዝገብ የተከፈተባቸው የድንጋይ ከሰል ለማስገባት ከኖክ ሃላፊ ጋር በመሆን በልጃቸው ስም በተከፈተ ድርጅት ለማስጀመር በዝግጅት ላይ እንዳሉ እዲያቆሙ ቢነገራቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ የጉዳዩን መነሻ የሚያውቁ ይናገራሉ።

በዚሁ መነሻ ጉዳዩ ባለሃብቱ ዘንድ ደርሶ ሌሎች ጉዳዮችም እንዲነሱባቸው ምክንያት በመሆኑ ውላቸው እንዲቋረጥ ሲደረግ፣ ጎን ለጎን አስቀድሞ በተከናወነ ስራ ክስ እንዲመሰረትባቸው ሲመቻች መቆየቱን ነው መረጃ የሰጡን የጠቆሙት።

ስምና አካባቢ ተጠቅሶ በተገለጸ ቦታ ተሽጠዋል የተባሉት ቦታዎች በምን ያህል እንደተሸጡና ለማን እንደተላለፉ የጠቆሙት ክፍሎች፣ ደላላ ሆነውና ገዢ መስለው አስፈላጊውን ሰነድና መረጃ ዛሬ የሚከሷቸው ክፍሎች ሲያደራጁ እንደነበር አስረድተዋል።

ለበርካታ ዓመታት የሚድሮክን ወንበር ሲመኙት የነበሩት አቶ አብነት፣ በአዲሱ ሹመታቸው ብዙም ሳይቆዩበት እንዲለቁት ሆነዋል። አቶ አብነት ሸራተንን ሙሉ በሙሉ በማክሰርና ህጋዊ ያልሆኑ በርካታ ክፍያዎችን ሲያከናውኑ መቆየታቸው ተመልክቷል። በአክሲዮን ንብረት ለሶስተኛ ወገን አስተላልፈዋል። ይህንን ያጠኑት ክፍሎች በየትኛው ዘርፍ ክስ እንደሚመሰርቱ መክረው በቅድሚያ በመሬት ሽያጭና ከአግባብ ውጪ ተከፈሉ በተባሉ ክፍያዎች ዙሪያ እንደሚያደርጉት ኢትዮ12 ሰምታለች። አቶ አብነት ከሚድሮክ በፈቃደኛነት ወደው መልቀቃቸውን በፎርቹን ጋዜጣ አማካይነት መናገራቸው አይዘነጋም።

Exit mobile version