Site icon ETHIO12.COM

የመጨረሻው ” ዓለም ስማ” ሰልፍ በአዲስ አበባ

ፖሊስ እንዳስታወቀው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማውገዝ፣ ለመከላከያ ሰራዊትና የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ይካሄዳል። በመግለጫው ላይ ባይገለጽም ሰልፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የትህነግን ወረራ አስመክቶ መንግስት ማጥቃት እንደሚጀምር ባሳወቀው መሰረት ለሚወሰደው ጥብቅ እርምጃ “ዓለም ስማ፣ ራስን ለመከላከል የሚወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ጩኸት አትስማ። ተገደን እንጂ ወደን አይደለም” የሚለውን ለማስተላለፍ ይመስላል።

በከፍተኛ ቁጥር ሰራዊት እያደራጀ ያለው መንግስት ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ ዱላው የከረረና በአየር፣ በምድር፣ እንዲሁም እስከመጨረሻ የሚዘልቅ በመሆኑ፣ ዓለም የጦርነቱን ፍትሃዊነት እንዲቀበል፣ ባይቀበልም ሕዝብ አምኖና ተቀብሎ የሚካሄድ መሆኑን ለማመልከት የተዘጋጀ ሰልፍ እንደሆን ሁኔታዎች ያስረዳሉ።፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማውገዝ፣ ለመከላከያ ሰራዊትና የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ የአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ያሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል።በዕለቱ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ነዋሪዎቹ ለፀጥታ ሃይሉ ደጀን መሆናቸውን ለማሳየት የሚያደርጉት ይህ የድጋፍ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ፈረሰኞችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በነገው ዕለት በሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ተገንዝበው ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በዕለቱ በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች


Exit mobile version