የተለያዩ አገራት በኢትዮጵያ ዉስጣዊ ጉዳይ ላይ የሚያሳዩ ትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም “መርከባችን አትሰምጥም” በሚል መሪ ቃል መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰልፉ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ምክትል አስተባባሪ ጋዜጠኛ ፍሬዘር ነጋሽ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራት ቆይታ እንዳስታወቀችዉ፤ የተለያዩ አገራት እና አለም አቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ዉስጣዊ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጫና ሊያቆሙ ይገባል ብላለች፡፡
ለዚህ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያዉያን በአገራችን ጉዳይ በተለይም በህዳሴ ግድብና በዉስጣዊ ችግሮቻችን ላይ የተዛባ የሚዲያ ዘመቻን ለመቃወም መርከባችን አትሰምጥም በሚል ሰልፉ እንደሚካሄድም ታዉቋል፡፡ከተቃዉሞ ሰልፉ በተጨማሪም ከኢትዮጰያ ጎን የቆሙ አገራትንም በሰልፉ ላይ ለማመስገን እንደታሰበምአስተባባሪዋ ተናግራለች፡፡
በመስቀል አደባባይ በሚካሄደዉ የተቃዉሞ ሰልፉ ላይ ሁሉም ዜጋ እንዲገኝና በመንግስት በኩል አስፈላጊዉን ትብብር በተለይም ፀጥታዉን እንዲያስከብርም የሰልፉ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አስተባባሪዎቹ ምንም አይነት የፖለቲካ አላማ እንደሌላቸዉና የድጋፍ ሰልፉ በአገር ዉዳድ ዜጎች የሚደረግ እንደሆነም ተነስቷል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ አገራት በተለይም አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ የአዉሮፓ አገራት በኢትዮጵያ ዉስጣዊ ችግር እጃቸዉን እያስገቡ እንደሚገኙ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጰያዉያን ይህን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ VIA – ኢትዮ ኤፍ ኤም
ቤተሰቦቻችንን በሻሪያ ህግ ማስተዳደር የእስላም ኢትዮጵያኖች መብት እንደሆነ ህገመንግስቱ ደንግግዋል። ይህ መብት እስልምና በተስፋፉባቸው የኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ ነዋሪዎች ዘንድ ንፅህናን መታጠብን ባህል በማድረጉ ኮሮና እንዳይስፋፋ ቢያግዝም አሁን ላይ ግን ኮሮና ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ አውሮፕላኖች ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ከተከለከሉ ሌሎች በርካታ ሀገራትም የአሜሪካንን ፈለግ ተከትለው አውሮፕላን ከኢትዮጵያ ወደ ግዛቶቻቸው እንዳይገቡ መከልከላቸው አይቀርም። በዕዳ የተገዙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖቻችን በርረው ሥራ ላይ ካልዋሉ ኢኮኖሚው ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ቀላል ባለመሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በከፊል በሀራጅ ከተሽጠ የሚያስከትለውን የሉዓላዊነት እና የህገወጥ ገንዘብን ከሀገር ማሸሽ ዝውውር ጥያቄ ከአሁኑ በጥልቅ አጥንቶ ማገናዘብ ያሻል። ይህ ጥናት ሳይካሄድ ኢኮኖሚው ቢያድግም የሀገሬው ህዝብን የኑሮ ጥራት ደረጃን ማሻሻል ይከብዳል።