Site icon ETHIO12.COM

ጥብቅ ማሳሰቢያ!

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር የአማራና የአፋር ክክልሎችን ለቅቆ እንዲወጣ አሜሪካ ላቀረበችው ጥሪ ጌታቸው ረዳ «የተጣለብን እገዳ እስካልተነሳ ድረስ ያንን ማድረግ አንችልም» ሲል በግልጽ ወረራውን እነደሚቀጥል ተናግሯል።

«ላሊበላን መቆጣጠራችን በሰሜን አማራ የሚገኙ መንገዶችን የመቆጣጠር አካል ሆኖ የመንግስት ኃይሎች በድጋሚ እንዳይደራጁ ለመከላከል ይረዳናል » ሲል ጌታቸው ሌላ ተጨማሪ ዕቅድ እንዳላ አስታውቋል። የትህነግ አሸባሪ ሃይል ላሊበላ የገባው ያለ አንዳች ውጊያ መሆኑ በበርካቶች ዘንድ ” ነገሩ ምንድን ነው” የሚል ጥያቄ እያስነሳ ነው። ትክክልም ነው።

በማንኛውም መስፈርት ይትህነግ ሃይል የአማራ ክልልን ሃይልና ሕዝ ሊረታ አይችልም። ቢችል ኖሮ በዋናው መስመር በጎንደር በኩል ሞክሮ ወደ ሱዳን መውጪያ ያበጅ ነበር። በዛ በኩል ያልሆነው ለምንድን ነው? ሕዝቡ አንድ ሆኖ ተንኮልን፣ሴራንና የውስጥ አስተኳሾችን ስለማይቀበል ነው።

ላለፉት 50 ዓመታት ኢትዮጵያዊያንን ሲያሰቃይ፣ መከራ ሲያበላ፣ የአገር ኢኮኖሚ ሲያደቅ የኖረው ትህነግ በከተማ ሰላማዊ መስለው በየቀበሌ በሚኖሩ አባላቱ ጭምር እይሰለለ፣ ዝምድናን ተገን አድርጎ እያጠቃ፣ ጓደናነትን ለስለላ እየተጠቀም፣ ቀን ሰላማዊ፣ ማታ የከተማ ውስጥ ሽፍታ የሆኑ አዘጋጅቶ ምን ሲሰራን እንደነበር አዲስ አበባ ሲገቡ አይተነዋል። ተዛዝበናል። በቅንጅት ምርጫ ጊዜ በየሰፈሩ ያሉትን ዋና ዋና የለውጥ አስተባባሪዎችን ነጥለው በመጠቆም ምን እንዳደረጉ አይረሳም።

በየቀበሌው የስለላና ” እከሌ እንዴት ዋለ” የሚለውን መረጃ ከመሰብሰብ ጀምሮ ንግዱን ስራውን፣ ብድሩን፣ ኢንቨስትመንቱን፣ አስመጪነቱን፣ ላኪነቱን፣ ድለላውን፣ ሰዎችን ወደ ውጭ በህገወጥ መላክን … ተቆጣጥረው በኔት ዎርክ አገሪቱን ሲያጥቡ ኖረዋል። ድርጅቱ በገሃድ አገር እየመራ፣ የአገር ሃብት ወደ ግል ካዝናው በፕራይቬታይዜሽን ስም አግበስብሷል። የሚቀናቀኑትን ገሏል። አስሯል። ቶርቸር አድርጓል። ሰውሯል። ጥፍር ነቅሏል። ደፍሯል። ተዘርዝሮ አያልቅም።

ያ ዛሬ የለም። “ለምን ይህ ቀረብኝ” ብሎ አገራችንን ሊያፈርስ መንጋ አሰማርቶ ወረራ እየፈጸመ ነው። ይህ ሃይል ለኢትዮጵያ ፈተና ሊሆን አይችልም። ግን እየሆነ ነው። ለምን? ምንድን ነው ችግሩ።

በደርግ ጊዜ በተመሳሳይ አገር እያስረከቡ የሚኮበልሉ አዋጊዎች ነበሩ። ብር ተቀብለው የካዱና ያስካዱ ነበሩ። አምቦ ላይ ወታደሩን እይስጨፈጨፈ ዋና ሲዋኝና ሲዳራ የነበረ አዋጊ ምን እርምጃ እንደተወሰደበት የአምቦ ጀግናው ህዝብ ያውቃል። ተመጣጣኝ ቅጣት ሰጥቷል።

ጀግናው የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ አወጣጥ ጀምሮ የቆመሩበት አሉ። ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ክብራቸን ነው። በዚህ ሰራዊት ደም መነገድ ጸቡ ከሕዝብ ነው። ነገ የሚደረገው የመጨረሻ ሰልፍ የሚናገረው ይህንን ነው። እናም የምትልከሰከሱ አቁሙ። ትህነግ ” የአብይ ሰራዊት” እያለ የሚጠራውን የመከላከያ ሃይል ለማፍረስ ተዘግጅቷል። ቢሳካለት ዛሬ የሚልከሰከሱለትን ነገ አፍንጫቸውን ይዞ ሂሳቡን ያወራርዳል። ይህ ባለፈው ጊዜ ታይቷል። ሕዝብም አይለቅም።

አሁን ያለንበት ወቅት ባለ አገርና አገር አልባ በመሆን መካከል ነው። ውጊያው የህልውና ነው። ውጊያው የልጅ ልጅ መቀመጫ የማኖር ጉዳይ ነው። እስከሚገባኝ በዚህ ጉዳይ መፋዘዝ ብሎ ነገር የለም። ይህን ሽፍታ በጫካ ብቻ ሳይሆን በሁሉም አቅጣጫ፣ የከተማ ሴሎቹን ሳይቀር መዋጋት ይገባል። ጊዜው ለጊዜያዊ ከርስ የሚታሰብበት አይደለም። እንንቃ!!

ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ትናንሽ አገር ለማድረግ እንቅልፍ ያጡ አገራት በውክልና ያስነሱብን ይህ ነቀርሳ በምንም መልኩ ከኢትዮጵያ በላይ አይደለምና ክንዳችንን እናደራርብ።አስተማማኝ ደጀን አለ፣ ሕዝብ ተነስቷል። አሁን ጠላትን በሚፈለገው ደረጃ ለማውደም ከበቂ በላይ ምክንያት አለ። ራሱ አሸባሪውም ይህን ስለሚረዳ ነው ጥድፊያ የመረጠው። የተዘጋውን ማስከፈት አለመቻሉ ውድቀቱን ያሳያል። በቅርቡ ድል ይሆናል።

ነጻ አስተያየት – አሸብር ከኬንያ መንደር አንድ

Exit mobile version