ETHIO12.COM

“አሸባሪው ህወሃት ቡድን ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም”

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም ሲሉ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ተናገሩ።

የሶማሌ ክልል በብርቆድ ወረዳ ሻለቃ ከደር መሀሙድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ሚሊሺያዎችን አስመርቋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አሸባሪው የህወሀት ቡድን የሶማሌ ክልልን ለማተራመስ የተለያዩ ሴራዎችን እየሸረበ ቢሆንም አሸባሪው ቡድን ሀገር የማፍረስ አቅምና ብቃት የለውም ብለዋል። የለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሁሉም ዜጋ መታገል አለበት ገልጸዋል።

ለምረቃ የበቃቹት የሀገሪቱና የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ ስለሆነ በጎሳ ስም ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ስራን የሚሰሩ ሰዎች መታገል አለባችሁ ብለዋል።

በምርቃው ስነስርዓቱ ላይ የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሁሴን ሃሺ፣ የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ፣የክልል ልዩ ሀይል አዛዥ ም/ኮ መሀመድ አህመድ፣ የፖሊስ ኮ/ኮምሽነርና የዞን አስተዳደሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በስነስርዓቱ ላይ የሶማሊ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሁሴን ሃሺ እንደገለፁት የክልሉን ሰላም ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ብለዋል።

የሶማሌ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ በበኩላቸው ከለውጡ በኋላ እንደ ክልል ትላልቅ ድሎች እንደተመዘገቡ ገልፀው፣ ከድሎቹ መካከልም በክልሉ የሰፈነው አስተማማኝ ሰላም አንዱ እንደሆነገልጸዋለ።

ሰልጣኞቹ በስልጠና ወቅት የሀገርቱንና የክልሉን ህገመንግስት፣ የሰበአዊ መብት አያያዝ፣ የመሣሪያ አጠቃቀምና ሌሎች ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን በክልሉ ወረዳዎች እንደሚመደቡ መገለጹን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

Exit mobile version