Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሓት በግዳጅ ወደ ጦርነት በአፋር ፈንቲ ረሱ ግንባር ያሰለፋቸው ህፃናትና ወጣቶች እጅ መስጠታቸውን ቀጥለዋል

አሸባሪው የህውሀት ጁንታ በግዳጅ ወደ ጦርነት በአፋር ፈንቲ ረሱ/ዞን ግንባር ያሰለፋቸው ህፃናትና ወጣቶች እየጠፉ እጅ መሰጠታቸውን ቀጥለዋል ።

“በቀላሉ አዲስ አበባ እንገባለን አፋር ሰመራ ለመድረሰ 77 ኪሎ ሜትር ነው የቀረን ብለው ዋሽተውን ሶስት ቀን አሰልጥነውን አሰገድደው ወደ ጦርነት ማገዱን” በማለት ምርኮኞቹ ተናግረዋል።

ምርኮኞቹ አክለውም “ይሄው እኛም ለአፋር ልዩ ሀይል እጃችንን ሰጥተን የቆሰልነውን አሳክመውናል። እነሱ ባሉት መንገድም ባይሆን አፋር ሰመራ እጃችንን በፍላጎታችን ሰጥተን ገብተናል በጥሩ ሁኔታ ላይም እንገኛለን” ሲሉ ገልፀዋል።

ምርኮኞቹ ለትግራይ ወጣት ባስተላለፉት መልእክት ወጣቱ ወደ ጦርነት መግባት እንደሌለበትና የገቡም ካሉ እንደነሱ እጃቸውም በሰላም እንዲሰጡ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ምርኮኞቹ የህወሀት አሸባሪ ወደ ጦርነት እንዲገቡ የሚቀሰቅሱት ነገር ሁሉ ውሸት መሆኑን ገልፀው “የራሳቸውን ልጆች ውጭ ሀገር እያሰተማሩ እኛን ትርጉም ለሌለው ጦርነት ህይወታችንን እንዲያልፍ እያደረጉን ነው” በማለት መግለፃቸውን የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

Exit mobile version