Site icon ETHIO12.COM

የደብረ ጽዮንና የጻድቃን ትንቅንቅ

እንደ ሁኔታዎች አመችነት በማይጨው የሚገኘውን የዞኑን የፀጥታ አስተዳደርን ቢሮ በቢሮነት የሚጠቀመው የወታደራዊው ክንፍ አመራር የሆነው የጻድቃን ገብረትንሣኤ ቡድን እንዲሁም የፖለቲካው ክንፍ አመራር የደብረ ጽዩን ገ/ሚካኤል ቡድን በመሃከላቸው የነበረው የትግል ስልት ልዩነት ተባብሶ በአሁኑ ወቅት ወደ እርስ በእርስ ወደ መፈላለግና መጠቃቃት ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ለመረጃው ቅርበት ያላቸውየውስጥ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

የደ/ጽዮን ቡድን እስከ አሁን የተደረገው ጦርነት ለትግራይ ህዝብና እናቶች ከሞት፣ስቃይና እንግልት የዘለለ ያመጣለት ፋይዳ አለመኖሩንና በፖለቲካውም ቢሆን ከህዝባችንና ከሌሎች እትዮጵያዊያን ወገኖቻችን እየለያየንና በጣላትነት እንድንተያይ ሲያደርገን፤ በአጋርነት አብረውን ይቆሙ የነበሩ በውስጥ የሚገኙ ሀይሎች በምንፈልገው መልኩ ሊደግፉን አልቻሉም የሚል መከራከሪያ በማንሳት አሁን ላይ ለህወሃትም ሆነ ለትግራይ ህዝብ የሚበጀው እየተፈጠረ ያለውን የሽምግልና አማራጭ በመጠቀም ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ማድረግ ብቻ ነው የሚል አቋም ማራመዱ በጻድቃን ለሚመራው ቡድን አልተዋጠለትም፡፡

ይህን ተከትሎም መሃል ሰፋሪው ጌታቸው ረዳ ፥ ደ/ጽዮን ሃሳቡን እንዲለውጥና በጋር እንዲቆም የማግባባት ስራ ከጻድቃን በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለመስራት እየሞከረ ነው፡፡

ደብረ ጽዩንና የቡድኑ አባላት የሆኑት ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) እና አለም ገ/ዋህድን ጨምሮ ሌሎችም አባላት ግን ህወሃት ጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመው የተሳሳተ ትንኮሳ እንደ አባይ ፀሐይ፣ስዩም መስፍንና አስመላሽ ወልደ ስላሴ የመሳሰሉትን፣ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖችንና ህዝባችንን ለችግርና ለአላስፈላጊ መሰዋዕትነት የዳረገ ነው በሚል ተቀናቃኙ የጻድቃን ቡድን ሀሳባቸውን እንዲቀበል ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ደብረ ጽዩን በጦርነቱ ወቅት ቀኝ እጁን ክፉኛ መመታቱና ፍንጥርጣሪውም ሌላ የሰውነቱን አካል ጎድቶት የነበረ ቢሆንም አፅቢ አካባቢ በሚገኘ ቤተክርስቲያን ህክምና ተደርጎለት ማገገሙ፤ እንደልቡ እንዳይሆንና ያሻውን በጻድቃን ቡድን ላይ እንዳያደርግ የስነ-ልቦና ጫና ስለፈጠረበት በቡድኑ ውስጥ ወታደራዊ አመራሩ የበላይነት የያዘ ይመስላል፡፡

ለመንግስት ቅድም ሁኔታዎችን ለመደራደሪያነት ያስቀመጠው የጻድቃን ቡድን በይፋ የሀይል አማራጭን በመምረጡ ትግራይንና ህዝቧን ወደ ከፋ ህይወትና ምስቅልቅ ውስጥ ለመክተት የወሰነ ይመስላል ይላሉ ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን፡፡ via FBC

Exit mobile version