ከነቅጥፈቱ መቀመቅ እየወረደ ያለ የሽብር ቡድን…


ህወሃት በውሸት ትርክት ለሶስት አስርት አመታት ህዝቡን ሲከፋፍል የኖረ፤ በዚህም ወደ ፍጻሜው እየተንደረደረ ያለ የሽብር ቡድን መሆኑን ለትግራይ ክልል ህዝብ በተናጠል፤ ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አለፍ ሲልም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች ብዙ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ዙሪያ ተከታታይ ማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻም ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በአብዲ ኬ

የህወሃት አሸባሪ ቡድን ትልቁ የውጊያ ስትራቴጂውና አቅም በውሸት ፕሮፓጋንዳ ሁሉን ግራ ማጋባት ነው፡፡ ይህንን ስልት የሚጠቀመው ሁሉም ላይ ነው፤ እታገልለታለው ከሚለው የትግራይ ህዝብ ጀምሮ እስከ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድረስ፡፡

እስከአሁን ድረስ ከሚነዛቸው ሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎች ብዙዎችን ለማሳሳት እረድቶታል፡፡ የትግራይ ህዝብ ለምን፣ እንዴት፣ እስከመቼ ብሎ ሳይጠይቅ በበዶ እጁ ህይወቱን አደጋ ላይ ጥሎ ወደ ጦር ግንባር እንዲዘምት በሃሰት ፕሮፓጋንዳቸው፤ በጥላቻ ትርክታቸው ጠልፈው አሳምነውታል፡፡

ለትግራይ ህዝብ አዲስ አበባን ልንቆጣጠር ትንሽ ቀረን በሚል የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ከህፃን እስከ አዛውንት ለጦር ሲያሰልፉ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ደግሞ ይህን ቀልብሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጸመብኝ፤ ተደበደብኩ በሚል ቅጥፈት የአዞ እንባ በማንባት የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲደረግ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡

የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በህወሓት የሽብር ቡድን ፕሮፓጋንዳ በመሳሳት ተጽእኖችን ለማሳደር እየጣረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የህወሓትን የበሬ ወለደ ወሬ ተከትሎ የሚሸበርበት ሁኔታ እየመነመነ ሄዷል ማለት ይቻላል፡፡ ቢሆንም አሁንም የሽብር ቡድኑ በወረራቸው ለመውረር ባሰፈሰፈባቸው አካባቢዎች ላይ ይህን አካሄድ እንደ ትልቅ የማሸነፊያ መሳሪያ ለመጠቀም ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ለዚህ ህዝቡ ይህን ባህሪውን ተረድቶ ጥንቃቄ ቢያደርግ የቡድኑ ግብዓተ መሬት እንዲፋጠን በብዙ ይረዳል፡፡

ህወሃት በውሸት ትርክት ለሶስት አስርት አመታት ህዝቡን ሲከፋፍል የኖረ፤ በዚህም ወደ ፍጻሜው እየተንደረደረ ያለ የሽብር ቡድን መሆኑን ለትግራይ ክልል ህዝብ በተናጠል፤ ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ አለፍ ሲልም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች ብዙ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ዙሪያ ተከታታይ ማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻም ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ህወሓት ከውሸት ባህሪው በቀላሉ የሚላቀቅ ባለመሆኑና ይህን ባህሪው በአለም አቀፉ ማህበረስብ ዘንድ በሚገባ ስለተጠቀመው በለመደው መንገድ ቅጠፈቱን አጠናክሮ ቢቀጥልበትም አሁን ግን እውነታው እየተገለጠ የመጣ ይመስላል፡፡

ህወሓት በአንዴ ከፍ ብሎ ቢደመጥም እንኳን በፍጥነት እየጠወለገ ይገኛል፡፡ የሽብር ቡድኑ የቁልቁለት ጉዞና ሰሞኑን ከተለያዩ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የሚታየው ወደ ሚዛኑ የመምጣት አዝማሚያ ሲታይ፤ ህወሓት የቅጥፈት መንገዱ ከዚህ በኋላ የሚያዋጣው አለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡

አሁን ጊዜው የኢትዮጵያን እውነት የምናስተጋባበት፤ በህብረት የምንቆምበት በመሆኑ ለአሉባልታዎች ቦታ ሳንሰጥ የኢትዮጵያን የጋራ ጠላት በጋራ ልንቀብረው ይገባል፡፡

Leave a Reply