Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ቡድን የትግራይ ሴቶች እና ህፃናትን ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ለጦርነት እየማገደ ነው – ምርኮኞች

አሸባሪው የህወሃት ቡድን የትግራይ ሴቶች እና ህፃናትን ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ለጦርነት እየማገደ መሆኑን በአፋር በኩል በመከላከያ ሰራዊታችን የተማረኩ የቡድኑ ታጣቂዎች ተናገሩ።

የሽብር ቡድኑ እድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት ብቁ ያልሆኑ ህፃናት እና ሴቶችን ከቀዬአቸው በተሳሳተ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማስገደድ ለእንግልት እና ለጦርነት አደማገደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ያለምንም ወታደራዊ ስልጠና ወደ አፋር ክልል ሰርገው በመግባት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥፋት ሊያደርሱ ሲሉ በጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ሽብርተኛ ቡድኑ አስገድዶ ላሰማራቸው ታጣቂዎቹ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ ስ፤ልሃገር መከላከያ ሰራዊት ፍፁም የሆነ ጥላቻ እና የተዛባ ትርክት እንደተነገራቸው የገለፁ ሲሆን÷ ስለሚዋጉበት ዓላማም ሆነ ሌላ ጉዳይ ጥያቄ ማንሳት የማይቻል መሆኑን ተናግረዋል።

ሰራዊቱ በመንግስት ውሳኔ መሰረት ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ አሸባሪው ትህነግ ወደ ክልሉ በመግባት ሰራዊቱን እንደደመሰሰ በማስመሰል ለቅስቀሳ የሚጠቀምበት መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አሸባሪው ቡድን በሚሰጣቸው አደንዛዥ እፆች አማካኝነት በጦርነቱ የቆሰሉ ምርኮኞች የደረሰባቸውን ጉዳት መገንዘብ አለመቻላቸውንም ነው የገለጹት።

ሽብርተኛው ህወሃት በአሁኑ ሰዓት አስገድዶ ላሰማራቸው ታጣቂዎች አንድ መሳሪያ ለስድስት ሰው እያስታጠቀ በመሆኑና ምንም አይነት ሎጀስቲካዊ ድጋፍ ማቅረብ የማይችል በመሆኑ ታጣቂዎቹ በርሃብና በእንግልት ምክንያት ምንም አይነት የመዋጋት አቅም እንደሌላቸው አብራርተዋል።via FBC

Exit mobile version