Site icon ETHIO12.COM

የሽብር ተልእኮን ለመፈፀም ቦንቦችን ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በሁመራ ከተማ የሽብር ተልእኮን ለመፈፀም ቦንቦችን ታጥቆ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሰቲት ሁመራ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል። ግለሰቡን በቁጥጥር ስር በማዋል ሌሎች የሽብርተኛው ተልእኮ አስፈፃሚዎችን በማጣራት ላይ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽሕፈ ቤት አስታውቋል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን መንግሥት ያስቀመጠውን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት አልቀበልም በማለት የትግራይ አርሶ አደር የዘር ወቅትን ተጠቅሞ እንዳያለማ ይህ የእናት ጡት ነካሽ አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የባንዳነት ሥራውን እያከናወነ ይገኛል።

በሁሉም የጦር ግንባር ድባቅ እየተመታ የሚገኘው የአሸባሪው ቡድን ሽንፈቱን ባለመቀበል ሰርጎ ገቦችን ወደ ተለያዩ ከተሞች እያሰማራ ይገኛል።

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በሁመራ ከተማ በኅብረተሰቡ ጥቆማ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም የ እብድ መስሎ በቆሻሻ ማስወገጃ አካባቢ በመግባት ሶስት የጭስ ቦንብ አንድ ኤፍ ዋን (F1) ቦንብ ይዞ ወደ ከተማ በመግባት የሽብር ተልእኮን ሊፈፅም የነበረ ግለሰብ በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋሉን የሁመራ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈ ቤት ኀላፊ ዋና ሳጅን ሀብቴ እንየው ገልጸዋል።

ዋና ሳጅን ሀብቴ ኅብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት እየሰጠ ያለው መረጃ የሚያስመሰግን እንደሆነ ጠቅሰው ከሰሞኑ በኅብረተሰቡ ጥቆማ 56 ኩንታል አደንዛዥ እፅ መያዙንም ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ነዳያን፣ እብድ እና ሌላም መስለው ስለሚመጡ ኅብረተሰቡ በንቃት ከጸጥታ አካላት ጋር ተጠናክሮ እንዲሠራ ዋና ሳጅን ሀብቴ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሁመራ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ኀላፊ በሪሁን እያሱ በዚህ የህልውና ዘመቻ ኅብረተረቡ እያሳየ ያለው ተሳትፎ አንድነታችንን ጥንካሬያችንን የሚያሳይ ነው ይህ ዘመቻ የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ስለሆነ ሁላችንም አካባቢያችንን በንቃት ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ:– ያየህ ፈንቴ–ከሁመራ – (አሚኮ)

Exit mobile version